2014-05-07 16:13:42

አገረ ቫቲካን፦ አዲስ ሰላሣ የስዊዘርላንድ ጳጳሳዊ የጸጥታ ኃይል አባላት ቃለ መሓላ ፈጸሙ


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. ግንቦት 6 ቀን 2014 ዓ.ም. የስዊዘርላንድ ጳጳሳዊ የጸጥታ ኃይል ምሥረታ በአገረ ቫቲካን በአጸደ ሳን ዳማሶ የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፍ ተኪ ብፁዕ አቡነ ጆቫኒ አንጀሎ በቺዩ በተገኙበት በደመቀ ሁኔታ ተከብሮ መዋሉ ሲገለጥ፣ ይኽ በዓል ግንቦት 6 ቀን 1527 ዓ.ም. ር.ሊ.ጳ. ቀለመንጦስ ሰባተኛ ከላንድዚከኖክ ወረራ ለመከላከል የደም መሥዋዕትነት የከፈሉት 147 ጳጳሳዊ የስዊዘርላንድ የጸጥታ ኃይል አባላት ከሚዘከሩበት ቀን ጋር ተያይዞ የሚከበር ሲሆን፣ የስፐይን ቅጥረኞች የቶሪዮነ በር በበረገዱበትና የክላንድዚከኖክ ኃይል ቦርጎ ሳንቶ ስፒሪቶ በወረሩበት ወቅት ጳጳሳዊ የስዊዘርላንድ የጸጥታ ኃይል አባላት የደም መሥዋዕት ከፍለው ከጠቅላላ ብዛት ውስጥ የቀሩት 42 የዚሁ ጳጳሳዊ የስዊዘርላንድ የጸጥታ ኃይል አባላት ር.ሊ.ጳ. ቀለምንጦስ ሰባተኛ ከሞት በማዳን ካስተል ሳንት አንጀሎ ሕንፃ ድረስ ሸኝተው ከሞት አደጋ በማትረፍ የከፈሉት መሥዋዕት ብፁዕ አቡነ በቺዩ በበዓሉ ቀን ተገኝተው የአዲስ ሰላሣ የስዊዘርላንድ ጳጳሳዊ የጸጥታ ኃይል አባላት ቃለ መሓላ ሥነ ሥርዓት ወቅት ባሰሙት ንግግር ማስታወሳቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በዓሉን ምክንያት ቀደም በማድረግ እ.ኤ.አ. ግንቦት 5 ቀን 2014 ዓ.ም. ጳጳሳዊ የስዊዘርላንድ የጸጥታ ኃይል አባላት በአገረ ቫቲካን ቀለመንጦስ የጉባኤ አዳራሽ ተቀብለው፦ እናንተ የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ታማኝ ቅን አገልጋዮች መላ አቅማችሁ ሕይወታችሁንም ጭምር ሳትሳሱ ለአደጋ በማጋለጥ የምታገለግሉ ናችሁ፣ ለዚህ አገልግሎት የሚያነቃቃችሁ ሕይወታችሁ ለመሰዋት የሚገፋፋችሁ ገንዘብ ለእኔ ባይነት የመዘናጋትና የፍጆታዊነት መንፈስ ሳይሆን ለቤተ ክርስቲያን ለቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ያላችሁ ፍቅር ነው” እንዳሉ ያስታወሰው የቅድስት መንበር መግለጫ አክሎ ጳጳሳዊ የስዊዘርላንድ የጸጥታ ኃይል አባላት አበ ነፍስና ቆሞስ አባ ማርኩስ ሃይንዝ በበኩላቸውም፦ የተወደዳችሁ ጳጳሳዊ የስዊዘርላንድ የጸጥታ ኃይል አባላት፣ የአገልግሎታችሁ መርሆ ‘Acriter et fideliter ጽናትና ታማኝነት’ የሚል ነው፣ ታማኝነት አማራጭ በሌለበት ፈታኝ ወቅት ብቻ ሳይሆን በዕለታዊ ሕይወታችሁ የምትመሰክሩት አገልግሎት መሆኑ ነው የሚያመለክተው፣ ስለዚህ ዕለታዊ አገልግሎታችህ ፈታኝ ወቅት የሚጠይቀው ጽናት በተስተካከለ ሁኔታ የሚጠይቅ ነው። ችግሮችን ተቋቁሞ ፈተናዎችን አሸንፎ በጽናት መልካም ማድረግ በሚለው ምርጫ ተመርታችሁ ቤተ ክርስቲያናችሁን የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ለማገልገል የተጠራችሁ ናችሁ” እንዳሉ ገልጦ በዚህ ጳጳሳዊ የስዊዘርላንድ ጸጥታ አስከባሪ ኃይል በዓል በተከበረበት ዕለት አዲስ ሰላሣ የዚህ የጸጥታ ኃይል አባላት እጃቸውን ከፍ በምድረግ የቅድስት ስላሤ ምልክት ሦስት ጣቶቻቸውን ቀጥ በምድረግና ሌሎች ሁለት በማጠፍ ጽናትና ታማኝነት ለቅዱስ ጴጥሮስ ተክታይ በማለት ብጋራ በተስተጋባ ቃለ መኃላ መፈጸማቸው ጠቅሶ፣ በመጨረሻም የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ፒየትሪ ፓሮሊን ቅዱስ ጴጥሮስ በባዚሊካ ለጳጳሳዊ የስዊዘርላንድ የጸጥታ ኃይል አባላት በዓል ምክንያት መሥዋዕተ ቅዳሴ እንደመሩና ከቀትር በኋላ በአገረ ቫቲካን ጳውሎስ ስድስተኛ የጉባኤ አዳራሽ ለጳጳሳዊ የስዊዘርላንድ የጸጥታ ኃይል ክብር በሽውይዝር ካንቶናለ ዡኡገንድ ብላሶርክሰትራ የሙዚቃ ቡድን አማካኝነት የውሁድ ጥዑም ሙዚቃ ትርኢት መቅረቡ አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.