2014-04-30 18:13:44

የር.ሊ.ጳ ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ!


RealAudioMP3 ውድ ወንድሞችና እኅቶች! እንደምን አደራችሁ!
ከሰሙነ ሕማማት በፊት ባደረግነው ሳምንታዊ አጠቃልይ ትምህርትክርስቶስ ከሰባቱ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች ስለ ጥበብ አስተንትነን ነበር፣ በዛሬው ዕለት ደግሞ ዕውቀት በሚለው ሁለተኛ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ለማትኰር እወዳለሁ፣ እንደችሎታችን ለመማርና ለማጥናት ስለሚያስችለን ስለ አእምሮአዊ ስለ የሰው ልጅ ዕውቀት አይደለም የሚናገረው፣ ስለ መንፈስ ቅዱስ ብቻ በልባችን ሊያኖረው ስለሚችለው የጸጋ ስጦታና ክርስትያን የሆነ ሁሉ ከውጫዊ የነገሮች ዕውቀት ለመሻገር የሚያስችለውና የእግዚአብሔር የሃሳብ ጥልቀትንና የደህንነት ዓላማውን ለመመርመር የሚያስችለው መንፈሳዊ ዕውቀት ነው፣
ሐዋርያ ጳውሎስ በቆሮንጦስ ለምትገኝ ማኅበረ ክርስትያን የዚሁ ስጦታ ማለት ይህ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ የሆነ ዕውቀት ሥራዎች ምን ምን መሆናቸውን እንዲህ ይዘረዝራቸዋል፣ “ነገር ግን። ዓይን ያላየችው ጆሮም ያልሰማው በሰውም ልብ ያልታሰበው እግዚአብሔር ለሚወዱት ያዘጋጀው ተብሎ እንድተጻፈ፥ እንዲህ እንናገራለን። መንፈስም የእግዚአብሔርን ጥልቅ ነገር ስንኳ ሳይቀር ሁሉን ይመረምራልና ለእኛ እግዚአብሔር በመንፈሱ በኩል ገለጠው።”(1ቆሮ 2፤9-10) እንዲህ ማለቱ ግን እያንዳንዱ ክርስትያን ስለ እግዚአብሔር ዕቅድና ዓላማ አሟልቶ ያውቃል ማለት አይደለም፣ እነኚህን ነገሮች ጥርት ባለ መንገድ የምናውቀው ከእግዚአብሔር ጋር በፍጹም አንድ ሆነን በእርሱ እቅፍ በምንገኝበት ጊዜ ነው፣ ነገር ግን ቅዱስ ጳውሎስ እንደሚያመልክተው አእምሮአችን የላቲኑ ሥርወ ቃል እንድሚለው ኢንቱስ ለጀረ ውሳጣዊና ምሥጢራዊውን ነገር ለማንበብ ይችላል፣ ስለዚህ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ የሆነው ዕውቀት ነገሮችን እግዚብሔር እንድሚረዳቸው እንድንረዳቸው ይረዳናል እንዲሁም የእግዚአብሔር አ እምሮ እንዴት እንድሚያስባቸው እንድናስብ ይረዳናል፣ አንድ ሰው አንድን ነገር በሰው ልጅ ዕውቀት ብቻ በብዙ ብልኃትና ጥንቃቄ ሊረዳቸው ይችላል፣ ይህ ጥሩ ነገር ነው ሆኖም ግን አንድን ነገር እግዚአብሔር እንደሚረዳው ጠለቅ ባለ መንገድ ለመረዳት የዚህ ስጦታ ሥራ ነው፣ ለዚህም ነው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መንፈስ ቅዱስን ሊልክን የፈለገው ምክንያቱም እኛ ሁላችን ነገሮችን የእግዚአብሔር ዕውቀት እንድሚረዳቸው አድርገን ለመረዳት ስለፈለገ ነው፣ ይህ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ከእግዚአብሔር ጋር ጥልቅ ግኑኝነት እንዲኖረንና እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ያለውን የፍቅር ዕቅድ ለመረዳት ያግባበናል፣
ስለዚህ የዕውቀት ስጦታ ከእምነት ጋራ ጥልቅ ግኑኝነት እንዳለው ብሩህ ነው፣ መንፈስ ቅዱስ በልባችን ውስጥ በመኖር አእምሮአችንን ካበራልን በኋላ እግዚአብሔር ያለውንና የፈጸመውን ነገራት የመረዳት ችሎታችን በየዕለቱ ይዳብራል፣ ራሱ ጌታ ኢየሱስ ከሐዋርያት ሲሰናበት እንዲህ ብለዋል “የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፣ እኔ ያስተማርህዋችሁን ሁሉ እንድትረዱም ያደርጋችኋል”፣ የኢየሱስ ትምህርትን መረዳት የእግዚአብሔር ቃልን መረዳት ወንጌልን መረዳት ለማለት ነው፣ አንድ ሰው ወንጌልን ማንበብና የሆነ ነገር መረዳት ይችላል ነገር ግን የእግዚአብሔር ጥልቀት ልንረዳው የምንችለው፣ ወንጌልን በዚሁ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ያነበብንን እንደሆነ ብቻ ነው፣ ይህም ትልቅ ስጦታ ነው ስለሆነም ደጋግመን በኅብረት “ጌታ ሆይ የዕውቀት ስጦታን ለግስልን” ብለን መለመን አለብን፣ በወንጌለ ሉቃስ የዚህ ስጦታ ጥልቀትና ኃይል የሚገልጥ አንድ ክፍል አለ፣ የኢየሱስ በመስቀል ላይ ሞትንና መቀበሩን ካዩ በኋላ ከሐዋርያቱ ሁለቱ ተስፋ ቆርጠውና አዝነው ከኢየሩሳሌም ተነስተው ኤማሁስ ወደሚባል መንደራቸው ይመለሱ ነበር፣ በዚሁ ጉዞ ሳሉም ከሙታን ተለይቶ የተነሳው ክርስቶስ በጉዞ አቸው አብራቸው ይጓዝና ስለሁኔታው ይነጋገሩ ነበር ነገር ግን አይኖቻቸው በኃዘንና ተስፋ በመቍረጥ ታፍነው ስለነበር ጌታ ኢየሱስን ሊያውቁት አልቻሉም፣ ኢየሱስ አብረዋቸው ከእርሳቸው ይጓዝ ነበር እሳቸው ግን ብዙ አዝነውና ተስፋ ቈርጠው ስለነበር ሊያውቁት አልቻሉም፣ ጌታ ኢየሱስ ሁኔታቸውን አይቶ ስለቅዱሳት መጻሕፍት ሲያስተምራቸው ኢየሱስ ሊሰቃይና ሊሞት ከሞትም መነሳት እንዳለበት ተጽፎ እንዳለ ሲነግራቸው አ እምሮ አቸው ይከፈት ልባቸው በተስፋ ሊሞቅ ይጀምራል (ሉቃ 24፡13-27 ተመልከት)፣ መንፈስ ቅዱስም በዕውቀት ስጦታው በእኛ ላይ የሚያደርገው ይህንን ነው፣ ቃለ እግዚአብሔር በበለጠ ለመረዳት የእግዚአብሔርን ነገሮች በዓይነ ኅሊና አይቶ ለመቻልና ለመረዳት እንዲሁም የሰው ልጅ ነገሮችንና ሁኔታዎችን በአጠቃላይ በበለጠ ለመረዳት አእምሮአችንን ይከፍታል፣ በክርስትያናዊ ሕይወታችንና ኑሮአችን የመንፈስ ቅዱስ የዕውቀት ስጦታ እጅግ አስፈላጊ ነው፣ እየተከናወኑ ያሉችን ነገሮች ለመረዳት በይበልጥ ደግሞ በወንጌል የሚገኘውን ቃለ እግዚአብሔር ለመረዳት ይህንን ስጦታ እንዲሰጠን ለሁላችን እንዲሰጠን ጌታን እንለምነው፣ እግዚአብሔር ይስጥልኝ፣







All the contents on this site are copyrighted ©.