2014-04-28 17:11:50

የብፁዓን ዮሐንስ 23ኛ እና ዮሐስ ጳውሎስ ዳግማዊ የቅድስና አዋጅ፣


RealAudioMP3 ብፁዕ ዮሐንስ 23ኛ እና ብጹዕ ዮሐስ ጳውሎስ ዳግማዊ ትናትና የቅድስት ካቲሊካዊት ቤተ ክርስትያን ቅዱሳን ሁነዋል፣ ናትና የሁለቱ የቀድሞ አርእስስተ ሊቃነ ጳጳሳት የቅድስና ሥርዓት ከፍ ባለ ክብር ተፈጽመዋል፣ ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በየቀድሞ አርእስተ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክት በ150 ካርዲናሎች በ100 ጳጳሳት ተሸንተው የቅድስና ሥርዓተ ቅድስና መርተዋል፣
ወቅታዊ እና የቀድሞ አርእስተ ሊቃነ ጳጳስ በሁባሬ ሲቀድሱ ሁለት በጋራ ቅዱሳን ሲሰየሙ ይህ የመጅመርያ ግዜ ነው፣ የቅድስና ሥርዓተ ቅዳሴ በተካሄደበት ግዜ የሁለቱ አዲስ ቅዱሳን ቅሪቶች በመንበረ ታቦት ተቀምጠዋል፣ ከሀገር ውስጥ እና ከውጭ ሀገራት የመጡ ከአንድ ሚልዮን የሚበልጡ ምእመናን የእምነት እና የቅድስና ክበረ በዓሉ ተሳታፊ ሁነዋል፣
ከዚህ ባሻገር የአንገሊካዊት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የይሁዲ የእስላም ተወካዮች የ28 ሀገራት መሪዎች ንጉሳውያን ቤተ ሰቦች በቅድስት መንበር እና ጣልያን የተመደቡ አምባሳደሮች የ93 ሀገራት አቀፍ ድርጅቶች ተወካዮች በዚሁ የቅድስና ሥርዓተ ቅዳሴ ተሳታፊ ሁነዋል፣ የተለያዩ ሀገራት የዜና አውታሮች የቅድስና ሥርዓቱን ዘግበውታል፣
ይሁን እና ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በዚሁ ዕለተ ቅድስና ዮሐንስ 23ኛ እና ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ የቅድስና ቅዳሴ ባሰሙት ስብከት ሁለቱ ቅዱሳን በኢየሱስ ክርስቶስ ቁስል ፊት ለመምበርከክ ያልፈሩ ናቸው ቁስሎቹ ለህዝበ ክርስትያን ቁዋሚ የፍቅር ምልክቶች ናቸው ሲሉ ሰብከዋል፣ ቅዱሳን ሁሉ ቤተ ክርስትያንን የሚያሳድጉ ናቸው ብለው የሰበኩት ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በቅድስት መንበር የቅዱሳን ጉዳይ ማሕበር የበላይ ሐላፊ ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ አማቶ ሶስት ግዝያት በየቅድስት ካቶሊካዊ ቤተ ክርስትያን መዝገብ እንዲቀመጡ ለፓፓ ፍራንሲስ ከጠየቅዋቸው በኋላ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ብፁዓን ዮሐንስ 23ኛ እና ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ቅዱሳን መሆናቸውና በቤተ ክርስትያን የቅዱሳን መዘገብ እንዲሰፍሩ እናውጃለን ብለዋል፣
በሁለቱ ቅዱሳን አማላጅነት ከከባድ ሕመም የዳኑ ቤተ ሰቦች የዚሁ መስዋዕተ ቅዳስና ተሳታፊ ሁነዋል፣ ፓፓ ፍራንቸስኮ በማያያዝ ካህናት ጳጳሳት ካርዲናላት ጳጳሳት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት የነበሩ ቅዱሳን ዮሐንስ ጳውሎስ 23ኛ እና ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ሁለንትናቸው ለእግዚአብሔር እና ለቤተ ክርስትያን የሰጡ ናቸው ብለዋል፣
ዛሬ ጥዋት በርካታ ምእመናን በተገኙበት በብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ኮማስትሪ የምስጋና ስርዓተ ቅዳሴ መርተዋል፣ እንኚህ ትናትና ዕለት ሥርዓተ ቅድስና የተፈጸመላቸው እና በየቤተክርስትያን የቅዱሳን መዝገብ የሰፈሩ የቀድሞ አርእስተ ሊቃነ ጳጳሳት ዮሐንስ 23ኛ እኤአ ብ1881 በሰሜናዊ ጣልያን በርጋሞ ላይ የተወለዱ ከ1958 እስከ 1963 ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት የነበሩ ሲሆኑ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ እኤአ ብ1929 በፖላንድ ቫዳቪች የተወለዱ ከ1978 እስከ 2005 ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት የነበሩ ናቸው፣
ቅዱስ ዮሐንስ 23ኛ እኤአ በ1962 ሁለተኛ የቫቲካን ጉባኤ የከፈቱ የቅድስት ካርቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን የእምነት አመለካከት አዲስ ራእይ የቀየሱ እና papa buono መልካሙ ር.ሊ.ጳጳሳት በሚል የቅጽል ስም የሚታወቁ እጂግ ተወዳጅ የነበሩ፣
ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ለረጂም ግዜ ለ27 ዓመታት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት የነበሩ ከቫቲካን ውጭ ዜና ሰናየ መጽሐፍ ቅዱስ የሰበኩ ሀገራት አቀፍ የወጣቶች ቀን መስርተው ከካቶሊካውያን እና ያልሆኑ የዓለም ወጣቶች የተገናኙ እና የመከሩ የምስራቅ ኤውሮጳ የኮሚኒዝም ርእዮተ ዓለም እንዲውድቅ አስተዋፅኦ ያደረጉ ነበሩ፣
የሚቀጥለው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን በትውልድ ሀገራቸው ፖላንድ ክራኾቪያ እንዲከናወን በእቅድ ተያዘዋል፣ ከቅዱስ ዮሐንስ ጳሎውሎስ ዳግማዊ ለ40 ዓመታት በቅርበት የሰሩ እና በርእሰ ሊቃነ ጵጵስናቸው ግዜ የግል ጽሐፊ የነበሩ በፖላንድ የክራኾቪያ ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ ካርዲናል ስታንስላው ዲቪጽ እናዳመለከቱት ፡ ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ በዚች ዓለም ላይ በነበሩበት ግዜ ግዝያቸው በጸሎት እና አስተንትኖ አሳልፈውታል፣
እኤአ በ1981 በቅዱስ ጰጥሮስ አደባባይ በአንድ አሊ አግቻ የተባለ ቱርካዊ በጥይት እንደተመቱ ወደ ሆስፒታል ሲወሰዱ አብርያቸው ነበርኩ ያሉት ብጹዕ ካርዲናል ስታንስላው ዲቪጽ ቀዶ ጥገና ከተደረገላቸው በኃላ ወድያውኑ እኔ ለተኰሰብኝ ሰው ምርያዋለሁ ብለው እንደነገርዋቸው በማያያዝ ገልጠዋል፣
ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ጨምሮ የተለያዩ የዓለም ሃይማኖቶች የሚያለያይ ግድግዳ ሳይሆን አገናኝ ድልድይ መስራት አለብን ይሉ ነበር ከቅድንግል ማርያም ወላዲተ አምልካም ልዩ ትስስር ነበራቸው ሲሉ በፖላንድ የክርኾቪያ ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ ካርዲናል ስታንስላው ዲቪጽ ገልጠዋል፣ አዲሶች የቤተ ክርስትያን ቅዱሳን በዚች ሰላም የተሰናት ዓለም ሰላም እንዲወርድ ለቅድስት ድንግል ማርያም እንድያማልዱልን እንማጸናቸው፣








All the contents on this site are copyrighted ©.