2014-04-22 11:31:00

ሐዋርያዊ ቡራኬ ትንሳኤ ክርስቶስ ር.ሊ.ጳ ፍራንሲስ ፡


እነሆ ትንትና ምዕራቡ እና ምስራቁ ዓለም የጌትችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይትንሳኤ በዓል ከፍ ባለ ድምቀት አክብሮት ውለዋል።በአራት ዓመታት አንድ ግዜ የላቲን እና ምብራቅ ሥርዓተ አምልኮዎች የጁልያን እና ጎረጎርያሳዊ የቀን መቁጠርያዎች እንደሚጋጠሙ እና በጋርዮሽ የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ ክብረ በዓል እንደሚያከብሩ ይታወቃል ።ይሁን እና ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ከትናትና ወድያ ለሊት ብብዙ ሺ ምእመናን በትገኙበት በቅዱስ ጰጥሮስ ካተድራል የትንሳኤ ክርስቶስ መሥዋዕተ ቅዱስ አስርገዋል።
ትናትና ዕለተ ትንሳኤ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኩለ ቀን ለያ በቅዱስ ጰጥሮስ ሰገነት ብቅ ብለው በቅዱስ ጰጥሮስ አዳባባይ እና አከባቢ ለተገኘ በብዙ ሺ ለሚቆጠር ህዝብ Urbi et Orbi ለሮም ከተማ እና ለመላ ዓለም ሐዋርያዊ ቡራኬ ችረዋል ።ንዜንውክሙ ዘኢና ሰናይ ኢየሱስ ክርስቶስ ተነስተዋል ኑ እዩ ይህ ዜና ሰናየ ክርስትያኖች ለዓለም የሚያዳርሱት ዜና ነው ብለው ያሉት ፓፓ ፍራንሲስ በማያያዝ ኢየሱስ ክርስቶስ ባይነሳ ኖሮ ክርስትና ክብሩ ያጠፋ ነበር የቤተ ክርስትያን ተልዕኮም ይቃጭ ነበር የቤተ ክርስትያን ተልዕኮ ከክርስቶስ መነሳት ስለምትነሳ ፡ በትንስኤ ክርስቶስ ፍቅር በጥላቻ ላይ ድል ሁነዋል ።ብምሕረቱ ሐጢአትን አሸንፈዋል መልካም በእኩይ ነገር ድል ሁነዋል ሐቅ ሐሰትን ሕይወት ዘለዓለማዊ ሞትን አሸንፈዋል በማለት ቅዱስ ኣአባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ለምእመናን ተናግረዋል ። እንግዲሕ የጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅር ኃያል እና ሕይወትን እንደሚሰጥ ፍቅር በምድረ በዳ ላይ እንደሚያብብ ያደርጋል ብለዋል ቅድስነታቸው ። ኦ ሁሉ የሚቻለው ኢየሱስ ክርስቶስ መድኅን ክርስቶስ እንድንፈልግህ እንድንወድህ እና እንድናመልክህ አግዘን ብለው ያሉት ፓፓ ፍራንሲስ በዚች ዓለም ላይ ሰላም አውርድልን ጸጋህ እና ምሕረትህ ስጠን በማለት ከቅዱስ ጰጥሮስ ሰገነት ተናግረዋል። በሶርያ እና ሌሎች ሀገራት የሚታየው ሁከት እና ግጭት እንዲገታ ሀገራት አቀፍ ማሕበረ ሰብ ጥረት እንድያደርግ የርዳታ ድርጅቶች የርሃብ ሰለባ ለሆነ ህዝብ ሰብአዊ ርዳታ እንዲሰጡ ፓፓ ፍራንሲስ ተማጽነዋል ። ሞትን ድል ያደርክ እና ሁሉ የሚቻልህ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰላምህ አውርድልን በማለት ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በቅዱስ ጰጥሮስ አደባባይ እና አከባቢ ለተገኙ ምእመናን ሐዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.