2014-04-11 16:55:27

ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ጉባኤ በቫቲካን እና የር.ሊ.ጳ ፍራንሲስ ንግግር ፡



በታላቅ ብሪታንያ በየብሪታንያ እና ወይልስ ረኪበ ጳጳሳት አዘጋጅነት እና በቫቲካን በየሳይንስ ጳጳሳዊ አካዳሚ አስተናግጅነት በብሪታንያ የወሰት ሚኒስተር ሊቀ ጳጳስ በብፁዕ ካርዲናል ቪንሰንት ኒኮልስ ሊቀ መንበርነት ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ትኩረት የሰጠ ለሁለት ቀናት ሀገራት አቀፍ ጉባኤ የተካሄደ ሲሆን ጉባኤው ትናትናት ተጠቃልለዋል ። የበርካታ ሀገራት የሀገር ግዛት ሚኒስትሮች የሀገራት አቀፍ ፖሊስ የወንጀል ክትትል ባለ ሙያዎች እና የሀገራት አቀፍ ድርጅቶች ተወካዮች በዚሁ ጉባኤ ተገኝተው ነበር ። ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን በዚሁ ጉባኤ ተሳታፊ መሆንዋ ይታወቃል ። ከአሁን በፊት የዚሁ ዓይነት ጉባኤ ቫቲካን ውስጥ ተካሄዶ ነበር ። ከጉባኤ ፍጻሜ በኃላ የዚሁ ጉባኤ ተሳታፊዎች በአውላ ማኛ ሐዋርያዊ አዳራሽ ከርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ጋር ተገናኝተዋል። ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ የዚሁ ጉባኤ ተሳታፊዎች በሐዋርያዊ አዳራሽ አውላ ማኛ ተቀብለው ባነጋገሩበት ግዜ ፡ ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ተስቦ ከመሆኑ ባሻገር ጸረ ሰብአዊነት ውንጀል መሆኑ አስገንዝበዋል ። በማያያዝም በሕጻናት እና ሴቶች መነገድ ስቃዩ እና አስከፊ ተግባሩ በኢየሱስ ክርቶስ አካል ላይ የተወቀረ አስከፊ ሐዘን እና ቁስል የፈጠረ ዘገኛን ተግባር መሆኑ ገልጠዋል።ቅድስነታቸው በዚሁ ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ትኩረት የሰጠ ጉባኤ ተሳታፊዎች ተቀብለው ባነጋገሩበት ግዜ እንዳመልከቱት ፡ ጉባኤው እጂግ አፈላጊ መሆኑ ጠቅሰው የቤተ ክርስትያን እና ባለ በጎ ፈቃድ ሰዎች መልካም ምልክት እና አስከፊ ተግባሩን በመኰነን በቃ ለማለት የተካሄደ ነው ። በየሰው ፍጥረት ንግድ እንዲገታ ሁላችን ኀያላችን አስባብረን በሽርክና መስራት እና የዚሁ አስከፊ ተግባር ሰለባ የሆኑ ሰዎች ለማዳን መቻል ይጠበቅብናል ብለዋል ፓፓ ፍራንሲስ ። ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ የብሪታንያ እና ወይልስ ረኪበ ጳጳሳት ሀገራት አቀፍ ጉባኤ ማዘጋጀቱ አመስግነው አወድሰዋል ። በዚሁ ጉባኤ ለተገኙ የተለያዩ ሀገራት የሀገር ግዛት ሚኒስትሮች እና የፖሊስ የበላይ ሐላፊዎች ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውወር ለመግታት ሁነኛ ርምጃ እንዲወስዱ እና የዚሁ አስፀያፊ ተግባር ሰለባ ከሆኑ ሰብአዊ ትብብር እንድያደርጉ ተማጽነዋል። በዚሁ ሰዎች እንዳ እቃ የሚሸጡበት እና የሚለወጡበት ክስተት ትኩረት በመስጠት ቫቲካን ውስጥ የተካሄደ የሁለት ቀናት ዓለም አቀፍ ጉባኤ ቅድስት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያንን በመወከል በርካታ ካርዲናላት እና ጳጳሳት የተገኙ ሲሆን ከአፍሪቃ በናይጀርያ የርእሰ ከተማ አቡጃ ሊቀ ጳጳሳ ብጹዕ ካርዲናል ጆን እናየካን ተገኝተው ነበር ።ይሁን እና በታላቅ ብሪታንያ የላንደን ፖሊስ ኮሚሽነር ሰር በርናርድ ሆጋን ሀው ጉባኤው አበራታች መሆኑ እና ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውርር ዘመናዊ ባርነት መሆኑ ጠቅሰው ይህንኑ ለመቅጨት አንድ ሀገራት አቀፍ ፕሮዠ በመቀየስ ሁነኛ ርምጃ መውሰድ ግድ ይላል ሲሉ ገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.