2014-04-09 16:06:08

የፖለቲካ ጥገኝነት ጠያቂ ብዛት በቁጥር ማደግ


RealAudioMP3 በኢጣሊያ በ 2013 ዓ.ም. የፖለቲካ ጥገኝነት ጠያቂ ስደተኛ ብዛት 27, 830 እንደነበርና ከ 2012 ዓ.ም. ጋር ሲነጻጸር 60 በመቶ እድገት ማሳየቱ በኢጣሊያ ሮማ ከተማ የሚገኘው በኢየሱሳውያን ማኅበር የተመሠረተውና በዚሁ ማኅበር ሥር የሚተዳደረው አስታሊ የስደተኞች መርጃ ማእከል ካወጣው ሰነድ ለመረዳት ሲቻል፣ በሮማ ከተማ ብቻ 21 ሺሕ ከተለያዩ አገሮች የተወጣጡ ስደተኞች የፖለቲካ ጥገኝነት ጥያቄ ማቅረባቸው ሰነዱ ለንባብ ለማብቃት በተካሄደው ጉባኤ የተገኙት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ደቦራ ዶኒኒ አስታውቀዋል።
የአስታሊ ማእከል አስተዳዳሪ የኢየሱሳውያን ማኅበር አባል አባ ጆቫኒ ማና ከቫቲካን ረድዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ የፖሊቲካ ጥገኛነት ጠይቂ ብዛት ከፍ እያለ መምጣቱና የዓለም ወቅታዊው ሁኔታ ግምት በመሰጠትም እያደገ እንደሚሄድ ነው ብለዋል። በመቀጥልም የዚያኑ ማእከል የመርሃ ግብር ጉዳይ የሚከታተለው ቢሮ ተጠሪ በራርዲኖ ጒሪኖ በበኩላቸውም ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ስደተኛው ኢጣሊያ ይገባል ከገባ በኋላ ግን የሚያገኘው ምንድር ነው? ከሚለው ጥያቂ በመንደርደር በተለያዩ አገሮች የሚታዩት ውጥረቶችና አለ መረጋጋት እስካልተወገደ ድረስ የስደተኛ ጸአት አይኖርም ብሎ መናገሩ ከእውነት የራቀ ነው። ስደተኛው እንዳይገባ ማገድ የስደተኛው ሕይወት ለአደጋ ማጋለጥና ሰዎችን ከቦታ ቦታ በሕገ ወጥ ተግባር ለሚያንቀሳቅሱ የወንጀል ቡድኖች አሳልፎ መስጠት ይሆናል፣ በኢጣሊያ ያለው ስደተኛ የማስተናገጃ ስልት መታደስና መሟላት አለበት ብለዋል። ሰነዱን ለንባብ ለማብቃት በተካሄደው ጉብኤ ተገኝተው ንግግር ያስደመጡት የቅድስት መንበር የዜናን ኅትመት ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረድዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ፦ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. መስከረም 10 ቀን 2013 ዓ.ም. ማእከሉን ጎብኝተው በማእከሉ ከሚተዳደሩት ስደተኞች ጋር በመገናኘት እዛው ባሰሙት ንግግር አለ ጥሪና ተኪ በማጣት ባዶአውቸውን የሚገኙት የተለያዩ የሃይማኖትና ማኅበራት ገዳማት ወደ እግዳ ቤት ከመቀየር ይልቅ ቤት ለሌለው ለስደተኛው ማስተናገጃ አገልግሎት ማዋል ብለው፣ በእውነቱ የክርስቶስ አካል ለሆኑት ቅርብ መሆን ያስፈልጋል ያሉትን ሃሳብ አባ ሎምባርዲ አስታውሰው፣ ቤተ ክርስቲያን ከ ጥንት ጀምራ በተለይ ደግሞ ከር.ሊ.ጳ. ፒዮስ አስረኛ እስከ ቅዱስነታቸው ልሂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ድረስ የስደተኛና ተፈናቃይ ጉዳይ በቤተ ክርስቲያን ሥልጣናዊ ትምህርት ሥር በመዳሰስ ስልጣናዊ መመሪያና ትምህርት በማቅረቡ ረገድ እቢይ አስተዋጽኦ እየሰጠች ነው፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በእውነቱ ለድኻው ለተናቀው ቅርብ ሳይኮን ለጌታ ቅርብ መሆን አዳጋችና የገንዘብ የሃብት አምልኮ የብኩንነት ያባካኝነት የተጠቅሞ መጣል ባህሎች በመገናኘት በመቀራረብ ባህል ተተክቶ ወንድማማችነት እንዲስፋፋ በቃልና በሕይወት ምስክር ናቸው እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ዶኒኒ ገለጡ።








All the contents on this site are copyrighted ©.