2014-04-09 15:59:59

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የጸሎተ ሐሙስ መርሃ ግብር


RealAudioMP3 የአባ ካርሎ ኞኪ የተራድኦ ማኅበር ባቋቋመው “ቅድስት ማርያም የእግዚአብሔር የዋኅነት ማእከል” መደጋገፍ መተሳሰብ በማነቃቃት በሚያስፋፋው የግብረ ሠናይ ማእከል ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 17 ቀን 2014 ዓ.ም. በላቲን ሥርዓት የሚከበረው ጸሎተ ሐሙስ ምክንያት በሮማ ሰዓት አቆጣጠር ከቀትር በኋላ ልክ አምስት ሰዓት ተኵል በማእከሉ የሚደገፉትና ቤተሰቦቻቸው የማእከሉ ኃላፊዎች የሚሳተፉበት የጌታ እራት መሥዋዕተ ቅዳሴ መርተው የሕጽበተ እግር ሥነ ሥርዓት እንደሚሠሩ የቅድስት መንበር የዜናን ኅትመት ክፍል መግለጫ ይጠቁማል።
ባለፈው ዓመት በተመሳሳይ የሊጡርጊያ ባህረ ሃሳብ መሠረትም ቅዱስነታቸው ሮማ በሚገኘው በታዳጊ ወጣት የማረሚያ ወኅኒ ቤት የሕጽበተ እግር ሥነ ሥርዓት መፈጸማቸው ያስታወሰው የቅድስት መንበር የዜናን ኅትመት ክፍል መግለጫ አክሎ፦ ቅዱስ አባታችን የጌታ የመጨረሻ እራትና የሕጽበተ እግር ሊጡርጊያ የሚፈጽሙበት ማእከል እጅግ በጠና የታመሙት ረዳት የሌላቸው ተነጥለው ለሚኖሩት የተሟላ ሰብአዊ መንፈሳዊ እንክብካቤና የጤና ጥበቃ አገልግሎት የሚሰጥበት መሆኑ ገልጦ፣ በዚህ ብቻ ሳይታጠር የአእምሮና የአካል ጉዳተኞች ከኅብረተሰብ ጋር በሙላት ተቀላቅለው እራሳቸውን ችለው ለመኖር እንዲችሉ በሚለው ዓላማ ላይ የጸና የተሟላ ሕንጸት የሚሰጥበት ማእከል መሆኑ የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ ይጠቁማል።








All the contents on this site are copyrighted ©.