2014-04-09 20:03:37

የር.ሊ.ጳ ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ


ውድ ወንድሞችና እኅቶች! እንደምን አደራችሁ! በዛሬው ትምህርተ ክርስቶስ ስለ መንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች የሚመለከት አዲስ ዙር እንጀምራለን፣ መንፈስ ቅዱስ ነፍስን እንደሚያቆም ታውቃልችሁ፣ የቤተ ክርስትያን እና የእያንዳንዱ ክርስትያን የሕይወት ሥርና ነፍስ ያ ከእኛ ጋር ኅብረት በመፍጠር ማደርያውን በልባችን ያደረገ የእግዚአብሔር ፍቅር ነው፣ መንፈስ ቅዱስ ዘወትር ከእኛ ጋር አለ ሁሌ በውስጣችን በልባችን ውስጥ ይገኛል፣ ወንጌላዊው ዮሐንስ እንደሚለው ታላቁ የእግዚአብሔር ስጦታ መንፈስ ቅዱስ ነው (4፤10 ተመልከት) ራሱ መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ታላቁ ስጦታ ሆኖ ለሚቀበሉትን ሁሉ የተለያዩ ሥጦታዎች ያድላል፣ ከእነዚህ ሥጦታዎች ቤተ ክርስትያን ሰባቱን ትለያለች፣ ሰባት ሙላትና ፍጽምና የሚያመልክት ቁጥር ስለሆነም ነው፣ እነኚህ ስጦታዎች ለምሥጢሮን ሜሮን በምንዘጋጅበት በትምህርተ ክርስቶስ የምንማራቸውና በሥርዓተ ሜሮን መንፈስ ቅዱስ እንዲወርድ ለመንፈስ ቅዱስ በምናደርገው ልመና የምናገኛው ናቸው እነርሱም ጥበብ ምክር ጽናት ዕውቀት ምሕረትና የእግዚአብሔር ፍራቻ ናቸው፣
    በዚሁ ዝርዝር መሠረት የመንፈስ ቅዱስ የመጀመርያ ስጦታ ጥበብ ነው፣ ሆኖም ግን በጥናትና በተመኵሮ ስለሚገኘው ስለ የሰው ልጅ ጥበብ አይደለም የሚናገረው፣ በመጽሓፍ ቅዱስ ንጉሥ ሰሎሞን የእሥራኤል ንጉሥ ሆኖ በተሾመበት ጊዜ ከእግዚአብሔር የጥበብ ስጦታ እንደጠየቀ ይነገራል፣ (1ኛ ነገ 3፡9 ተመልከት)፣ የጥበበ ትርጉምም ይህ ነው፣ ነገሮችን ሁሉ በእግዚአብሔር ዓይኖች አይቶ መቻል ነው፣ ዓለምን ይሁን ሁኔታዎችን እንዲሁም ችግሮችንና ነገሮችን ሁሉ በእግዚአብሔር ዓይኖች አይቶ መቻል ነው፣ አንዳንድ ግዜ ነገሮችን ስንመለከት እንደፍላጎታችን ደስ በሚሉን መንገድ አልያም እንደልቦቻችን ሁኔታ በፍቅር ወይንም በጥላቻ ወይንም በምቀኝነት መንገድ እናያቸዋለን፣ ነገር ግን ይህ የእግዚብሔር ዓይን አይደለም፣ ስለዚህ የጥበብ ስጦታ ነገሮችን በእግዚአብሔር ዓይኖች ማየት እንደምንችል የሚያደርገን የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ ነው፣ የጥበብ ስጦታ የምንለውም ይህን ነው፣
    እውነት ነው ይህ ነገር ከእግዚአብሔር ጋር ካለን ጥልቅ ግኑኝነት ይፈልቃል፣ ይህ ግኑኝነት ልጆች ከወላጅ አባታቸው ጋር የሚያደርጉት ግኑንነት ነው፣ ይህ ዓይነት ግኑኝነት ሲኖረን መንፈስ ቅዱስ ደግሞ የጥበብ ስጦታን ይለግስልናል፣ ከእግዚአብሔር ጋር የተዋሃድን እንደሆነ መንፈስ ቅዱስ ልቦቻችንን በእግዚአብሔር ፍቅር እንድንቃጠልና የእርሱ ምርጥ ልጆች መሆናችንን ግልጥ ያደርገዋል፣
    መንፈስ ቅዱስ ክርስቲያን ሰውን አዋቂ (ጥበበኛ) ያደርገዋል። ይህም ማለት ለሚቀርብለት ማንኛውም አይነት ጥያቄ መልስ ወይም መፍትሄ ይሰጣል ማለት ሳይሆን ግን የእግዚአብሔርን ነገር የሚረዳና እግዚአብሔር ከሱ የሚፈልገውን የሚያውቅና እንዲሁም የእግዚአብሔር መንፈስ ያልሆነውን በልቡ ለይቶ የሚረዳና የሚገለጥለት ጥበበኛ ሰው ነው። በእግዚአብሔር እውቀት የተሞላ የሰው ልብ ትክክለኛና የእግዚአብሔር ጠረን አለው። በኛም የክርስቲያኖች ማኅበረሰብ እንዲህ አይነት ክርስቲያኖች መኖር በጣም አስፈላጊ ነው። ምክንያቱም ሁሉ መናቸው ስለ እግዚአብሔር ያወራልና ውጤቱም ያማረና የእግዚአብሔር ፍቅሩና መገኘት ከኛ ጋር እንዳለ ይገልጻል። ይህም እንዲሁ እኛ በፈለግነው አጋጣሚና ሁኔታ አዘጋጅተን ማቅረብ የምንችል ሳይሆን ግን የእግዚአብሔር ስጦታ ነው። ይህም ስጦታ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ በሆነው በልባቸው መንፈሱን ለሚያከብሩ ብቻ ነው፣፣

በኛ በልባችን ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ይገኛል። ልናዳምጠውና ላናዳምጠው እንችላለን። እኛ መንፈስ ቅዱስን ካዳመጥነው እሱ የእውቀትና የጥበብ መንገድን ያስተምረናል ይህም ስጦታ ነገሮችን በእግዚአብሔር ዓይን እንድናይና እንድንመለከት በእግዚአብሔር ጆሮ እንድንሰማና እንድናዳምጥ በእግዚአብሔር ልብ እንድናፈቅር የምንፈርደውም ፍርድ በእግዚአብሔር ፍርድ እንድንፈርድ ያደርጋል። ይህ ነው መንፈስ ቅዱስ የሚሰጠን የእውቀትና የጥበብ ስጦታ ሁላችንም ይህንን ስጦታ መቀበል እንችላለን ይህንን ለመቀበል መንፈስ ቅዱስን መለመንና መጠየቅ አለብን።
እስቲ ለምሳሌ አንዲት እናትን በቤትዋ ውስጥ ከልጆችዋ ጋር እናስብ በቤትዋ ውስጥ ከአንዱ ቦታ ወደ ሌላ ስትንጎዳጎድ ልጆችዋ ሲያስቸግሯት ድክም ብላ ልጆችዋ ስትቆጣ ጥያቄ ላቅርብላችሁ ይህ ትክክል ነውን? የእግዚአብሔር ጥበብ ነውን? ልጆችን መቆጣት ትክክል ነው ወይስ አይደለም እስቲ መልስ ስጡኝ! ትክክል አይደለም! ግን አንዲት እናት ልጇን ተቆጥታ በፍቅርና በትዕግስት ለልጇ ለምን እንደከለከለችና አይሆንም ያለችበትን ምክንያት ብታስረዳውና ብትገልፅ ይህስ የእግዚብሔር ጥበብ ነውን? አዎን ይህ ነው መንፈስ ቅዱስ ለኛ በሕይወታችን የሚሰጠን።
ለምሳሌ በትዳር ውስጥ ብንመለከት ባልና ሚስት ተኮራፍፈው ወይም ተጣልተው አንዱ ሌላውን ዞር ብሎ አያይም ከተተያዩ ደግሞ ፊታቸውን አጣመው በክፉ አይን የሚተያዩ ከሆነ ይህ የእግዚብሔርን ጥበብ ነውን! አይደለም ግን ሁለቱም በቃ አልፋል እንታረቅ ሰላም እናድርግ ተባብለው ቢኖሩ ይህ ጥበብ ነው (በአደባባይ የነበር ሕዝብ በአንድነት አዎን) ብሎ ሲመልስ ይህ ነው የመንፈስ ቅዱስ ጥበብ ስጦታ በየቤታችን በልጆቻችንና በኛ ላይና በሁላችን ይደር ይገኝ!!
ይህን ደግሞ አንማረውም ይህ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ነው፣ ለዚህ ነው ሁልግዜ አምላካችንን የመንፈስ ቅዱስን ስጦታን እንዲሰጠን መጠየቅና መማለድ አለብን ይህን የጥበብና የእውቀት ስጦታ ነው በእግዚብሔር ዓይን እንድናይና እንድንመለከት ያስተምረናል በእንግዚአብሔር ልብ እንድናዳምጥና በእግዚአብሔር ቃል እንድናወራ ያስተምረናል። በዚህ ጥበብና እውቀት ወደ ፊት እንሄዳለን ቤተሰባችን ቤተክርስቲያናችን እንመሠርታለን ሁላችንም በቅድስና እንኖራለን። ዛሬ የጥበብ ስጦታን እንዲሰጠን እንለምን። እመቤታችን ድንግልማርያም የጥበብ እናት ስትሆን ይህንን ስጦታ እንድታስገኝልን እንለምናት። እግዚአብሔር ይስጥልኝ!!








All the contents on this site are copyrighted ©.