2014-04-07 18:31:40

የእግዚአብሔር ምሕረት ወሰን የለውም፣


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ትናንትና እኩለ ቀን ላይ በቅዱስ ጴጥሮስ አደበባይ ከተሰበሰቡት በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ምእመናንና ነጋድያን ጋር የመል አከ እግዚአብሔር ጸሎት ከማሳረጋቸው በፊት “ለእግዚአብሔር ምሕረት ወሰን የለውም” ሲሉ ካስተማሩ በኋላ ዛሬ የሚዘከረውን የርዋንዳ እልቂት ሃያኛ ዓመት እና በአፍሪቃ እያስፋፋ ያለው የኢቦላ መልከፍት በማስታወስ እንዲሁም የዛሬ አምስት ዓመት በአኲላ ያጋጠመው የመሬት መንቀጥቀጥ አስታውሰው “በነጻ ፍላጎቶቻችን በመርጥናቸው የጥፋትና ሞት መቃብሮች ክርስቶስን አይበግሩትም” ብለዋል፣
በላቲኑ ሥርዓተ አምልኮ ትናንትና የተነበበው የወንጌል ክፍል ከዮሐንስ ወንጌል የተወሰደ ሆኖ ስለ የአል አዛር ከሙታን መነሣት የሚገልጥ ነበር፣ ይህንን ምሳሌ በመጠቀምም ቅዱስነታቸው “ኃጢአቶቻችን ከዘፈቁን መቃርር መውጣት ያስፈልገናል” ሲሉ ከ60 ሺ በላይ ለሚሆኑ በአደባባዩ የነበሩትን ሕዝብ አስተምረዋል፣
“ዓይኖቻችንን ጋርደው ይዘውን ካሉ የትዕቢትና ትምክህተኛነት መሸፈኛዎች ነጻ ለመውጣት እንታገል፣ ምክንያቱም ት ዕቢት የገዛ ራሳችን የብዙ ጣዖቶች እና ነገሮች ባሮች ያደገናልና፣ ለዚህም ጌታ ኢየሱስ ሁሌ ጨቍኖ ይዞን ካለ ጨለማ ነጻ እንድንወጣ እየጠራን፣ ይህ እስር ቤት የውሸት የግል ጥቅምን ያስቀደመና ፈሪሳዊ ሕይወት ለመምራት ይገፋፋናል፣
“ክርስቶስ በገዛ ፍቃዳችን ክፋትንና ሞትን በመምረጥ እንዲሁም በጥፋቶቻችንና በኃጢአቶቻችን በገነባቸው መቃብሮች አይበገርም፣ ሁሉም ቻይ ስለሆነ በእነዚህ ነገሮች አይሸነፍም፣ ለአል አዛር እንዳለው ሁሉ ለእያንዳንዳችን ኑ ዉጡ እያለ ይጠራናል፣
“ና ውጣ” የሚለው ት እዛዝ ለእውነተኛ ነጻነት የሚደረግ እጅግ ቆንጆ ጥሪ ነው፣ የእኛ ትንሣኤ ኢየሱስን በመታዘዝ ወደ ብርሃንና ወደ ሕይወት ስንወጣ ይጀምራል፣
“አብዛኛውን ጊዜ በኃጢአት የተሸፈንን ነን! እነኚህ ሽፋኖች መገለጥ አለባቸው፣ እንዲህ በማድረግም እውነተኛ ገጽታችን ልናገኝ እንችላለን ይህንም ገጽታ በእግዚአብሔር አምሳልና አር አያ የተፈጠረን ስለሆንን ሽፋኖቹ ከተወገዱ በኋላ እውነተኛ ገጽታችንን እናገኛለን፣ የአል አዛር ትንሣኤ የእግዚአብሔር ጸጋ እስከ የት መድረስ እንደሚችል ያመለክተናል ይህም እኛ እስክነለወጥ መሆኑ ነው፣
“ተጠንቅቃችሁ አዳምጡ! ለሁላችን ለተሰጠው የእግዚአብሔር ምሕረት ምንም ወሰን የለውም፣ ጌታ ዘወትር ከእርሱና ከሕያዋን ብርሃን የሚለዩንን የኃጢአቶቻችን የመቃብር ድንጋዮች ነጻ ሊያወጣን ዝግጁ ነው፣ ለሁላችን ለተሰጠው መለኮታዊው ምሕረት ወሰን የለውም፣ ይህንን አረግ በደንብ እንድታስታውሱት ይሁን፣ ለሁላችን ለተሰጠው መለኮታዊው ምሕረት ወሰን የለውም፣
“እስቲ አንዴ አብረን ሁላችን እንድገመው ለሁላችን ለተሰጠው መለኮታዊው ምሕረት ወሰን የለውም፣ ሲሉ ካስተማሩ በኋላ የመል አከ እግዚአብሔር ጸሎት አሳርገዋል፣
ከመል አከ እግዚአብሔር ጸሎት ብኋላ ስለርዋንዳ እልቂት እንዲህ ብለዋል፣
“በቆራጥነትና በተስፋ ፍሬዎቹን በመሳየት ያለውን የዕርቅ ጉዞን እንዲቀጥሉና የአገሪቱ ሰብአዊና መንፈሳዊ ግንባታ ኃላፊነትን እንዲለብሱ ያለኝን አባታዊ ቅርበትየን ለርዋንዳ ሕዝብ መግለጥ እወዳለሁ፣ ሲሉ የርዋንዳውን እልቂት ሃያኛው ዓመት በማክበር ለሚገኙ የርዋንዳ ሕዝብ መልካም ምኞታቸውን ገልጠዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.