2014-04-04 16:18:01

ብፁዕ አቡነ ቹሊካት፦ ድኽነት ጨርሶ ለማጥፋት ቤተሰብ መሠረት ነው


RealAudioMP3 ባለፉት ቀናት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሕንጻ ሚለኒዩም የተሰየመው ዓለም አቀፍ የልማት እቅድ ዙሪያ በተወያየት ሦስተኛው ክፍለ ጉባኤ የተሳተፉት በተባበሩት መንግሥታት ለቅድስት መንበር ቋሚ ታዛቢ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ፍራንሲስ ቹሊካት፣ ድኽነት ጨርሶ ለማጥፋት ቤተሰብ መሠረት ነው በሚል ቅዉም ሃሳብ ላይ ያተኵረ ንግግር ማስደመጣቸው የቅድስት መንበር መግልጫ አስታወቀ።
ድኽነት ጨርሶ ለማጥፋት የሚል ውሳኔ ለዓለም አቢይ ተጋርጦ የሚያቀርብ ተቀባይነት ያለው የልማት እቅድ ችላ ሊባል የማይገባው እውነተኛው እድገት እንደሆነ እማኔ ያለው መሆን እንደሚገባው የገለጡት ቋሚ ታዛቢ ብፁዕ አቡነ ቹሊካት ድኽነት በማጥፋት እውነተኛውና ሰብአዊነት የተካነው ልማት ለማረጋገጥ የቤተሰብ ሰብአዊ መብትና ክብር ጥበቃ ወሳኝ መሆኑና ቤተሰብ መንከባከብ ቤተሰብ ለሚያፈራው የነገው ተስፋ የሆነው ትልውድ ከወዲሁ መንከባከብ ማለት እንደሆነም ማብራራታቸው የቅድስት መንበር መግለጫ ያመለክታል።
በብራዚል ሪዮ ደ ጃነይሮ ተቀባይነት ያለው የልማት እቅድ በሚል ርእስ ሥር እ.ኤ.አ. በ 2012 ዓ.ም. በኢንዳስትሪ የበለጸጉት አገሮች ያካሄዱት ጉባኤ ብፁዕነታቸው አስታውሰው በትውልድ መካከል የትብብርና የመተሳሰብ ባህል እንዲጸና ያለው አስፈላጊነት የሚል ጉባኤ ያሰመረበት ሃሳብ ጠቅሰው ተቀባይነት ያለው የልማት ዕቅድ የነገው ተስፋ የሆነው ትውልድ መሠረታዊ ፍላጎት ግምት የሚሰጥ መሆን አለበት ይኽ ማለት ደግሞ ቤተሰብ ማእከል የሚያደርግ መሆን እንዳለበት የሚያመለክት እርሱም ለማኅበርሰብ ብሎም ለኅብረተሰብ እርባና ያተኮረ ከመሆኑም ባሻገር ድህረ 2015 ዓ.ም. የሚል ተቀባይነት ያለው የልማት እቅድ መንግሥታት በሚከተሉት ተቀባይነት ያለው የልማት እቅድ ቤተሰብ ማእከል እንዲያደረጉ አደራ ብለው ቤተሰብ ቅድሚያ መስጠት የልማቱን እቅድ የሚያፋጥን ይሆናል እንዳሉ አስታውቀዋል።
በመጨረሻም ብፁዕነታቸው ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ወንጌላዊ ኃሴት በሚል ርእስ ሥር የደረሱት ሐዋርያዊው ምዕዳን ዘንድ “በእውነቱ እግዚአብሔር የሕብረሰብ የሕዝቦች የድኾች ሕይወት ጉዳይ በጥልቀት የሚያስቡ የፖለቲካ አካላት እግዚአብሔር እንዲያድለን እንጸልይ” ባሰፈሩት ሃሳብ ያስደመጡት ንግግር ማጠቃለላቸው የቅድስት መንበር መግለጫ ያመለክታል።







All the contents on this site are copyrighted ©.