2014-04-04 16:06:07

ቤተ ክርስቲያን አዲስ ሶስት ቅዱሳን ታደለች


RealAudioMP3 እግዚአብሔር ለኵላዊት ቤተ ክርስቲያን ሦስት አዲስ ቅዱሳኖች እነርሱም ፍራንቸስኮ ደ ላቫል ማሪያ ደል ኢንካርናዚዮነና ጁዘፐ ደ ኣንኪየታ ቅዱስ አባታች ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የቅዱስን ጉዳይ የሚከታተለው ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ አማቶ ያቀረቡት ሰነድ ፍሪማቸውን በማኖር በሰጡት ውሳኔ መሰረት እንዳደላት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ በነደታ ካፐሊ ገለጡ።
እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 24 ቀን 2014 ዓ.ም. ሮማ በሚገኘው በቅዱስ ኢግናዚዮ ዘ ሎዮና ለቅድስናው የሚያርገው የምስጋና መሥዋዕተ ቅዳሴ በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የሚመራ መሆኑ የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ በነደታ ካፐሊ አያይዘው ቅዱስነታቸው ብፁዕ ካርዲናል አማቶ ባቀረቡት ሰነድ መሠረት ጭምር ለአራት የቤተ ክርስቲያን ልጆች የብፅዕና ለስምንት የክቡር በእግዚአብሔር ውሳኔ ማጽደቃቸው አስታውቀዋል።
የቤተ ክርስቲያን የቅዱሳን ታሪክ እንደሚያመለክተው ሦስቱ አዲሶች ቅዱሳን የተናቁትን የተርሱትን በድኽነት ጫንቃ ስር የሚገኙትን ንኡሳን የኅብረተሰብ ክፍል በቤተ ክርስቲያን ተልእኮ በወንጌላዊ ልኡክነት ኢየሱስ ክርስቶስን በመምሰል ያገለገሉ ስቃይና መከራ በተደቀነበት ወቅትም የመስቀል ብርሃን ከመከተል ያላመነቱ እንደሆኑና ማሪያ ጉያርት እ.ኤ.አ. በ 1599 ዓ.ም. በፈረንሳይ ቱርስ የተወለዱ የአባታቸውን ውሳኔ በመታዘዝ ተድረው የአንድ ልጅ እናት ለመሆን በቅተው የተወለደው ሕፃን ገና የጥቂት ወራት ዕድሜ እያለው ጋለሞታ ሆነው ቀርተው’፣ ከሟች ባለ ቤታቸው የወረሱት የንግድ ድርጅት ከነበረበት የብድር ጫና ሁሉ በማላቀቅ በዚያኑ ዘመን የነበረው የተባዕትነት ባህል ተጋፍጠው በማስተዳደር ሥልት ተደናቂት ያተረፉ ነገር ግን ቀስ በቀስ የጸላይ ያስተንታኝ የሰቂለ ህሊና መንፈስ እየማረካቸው በኢየሱስ ፍቅር በመሞላት መኖር ጀምረው በ 1620 ዓ.ም. ልክ ከ 11 ዓመት በኋላ በኦርሶሊን የደናግሎች ማኅበር ገብተው አንዱን ልጃቸው ለእህታቸው አስረክበው የገዳማዊ ሕይወት ጀምረው፣ ስማቸውን ለገዳማዊ ሕይወት ምክንያት ማሪያ ደል ኢንካርናዚዮነ በሚል ተተክቶ የማኅበሩ አባል ለመሆን ጸጋው ታድለው መጀመሪያ ወደ ካናዳ ኪዩበክ ተልከው ወንጌል በመመስከር ትምህርተ ክርስቶስ በማስተማር ሕፃናትን በመንከባከብና በማንጸ በማገልገል ላይ እያሉ በ 1672 ዓ.ም. እሳቸው የጀመሩት የካናዳ ኦርሶሊኒ ደናግል ማኅበር ዛሬ በካናዳ የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን እናቶች ማኅበር በሚል ስም የሚታወቀው የደናግል ማኅበር ተስፋፍቶ ለቤተ ክርስቲያንና ለሕዝበ እግዚአብሔር አቢይ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑ ለማወቅ ተችለዋል።
ፍራንቸስኮ ደ ላቫል በካናዳ ኵይበክ ቀዳሜ ብፁዕ ጳጳስ በፈረንሳይ የተወለዱ የኢየሱሳውያን ማኅበር አባል ለመሆን በቅተው በ 1647 ዓ.ም. የኤቨሩክ ሐዋርያዊ መሥተናብር ሆነው እያገለገሉ እያሉ ከኢየሱስውያን ልኡካነ ወንጌል ጋር በነበራቸው ጥብቅ ግኑኝነት ተነቃቅተውም በኢንዶቻይና የቶንኪኖ ሐዋርያዊ መሥተናብር ሆነው ተልከው በ1658 ዓ.ም. ጳጳስ እንዲሆኑ ተሹመው የአዲሲቷ ፈረንሳይ ሐዋርያዊ መሥተናብር በካናዳ በምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የተለያዩ ቁምስናዎች በማቋቋም ትምህርት ቤቶችና የጤና ጥበቃ መስጫ ማእከሎችን በመመሥረት የአገሪቱ ቀደምት ተወላጅ ዜጎች ለተለያየ አደጋ ለተጋለጡት ቅርብ በመሆን በማገልገል በ 1676 ዓ.ም. በተሟላ የሕንጸት ተልእኮ አገልጋይ በሚል መንፈሳዊ አላማ ሥር አገልግሎት የሚሰጥ የኖትረ ዳም ማኅበር እንደመሠረቱም የቤተ ክርስቲያን የቅዱሳን የታሪክ ማኅደር ይጠቁማል።
ሦስተኛው ቅዱስ ጁዘፐ ኣንኪየታ የብራዚል ሐዋርያ በሚል መጠሪያ የሚታወቁ እ.ኤ.አ. በ 1980 ዓ.ም. ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ብፅዕና የታወጀላቸው የኢየሱሳውያን ማኅበር አባል በስፐይን እ.ኤ.አ. በ 1534 ዓ.ም. የተወለዱ በፖርቱጋል ኮይምብራ የፍልስፍናና ቲዮሎጊያ ትምህርታቸውን አጠናቀው እ.ኤ.አ. በ 1553 ዓ.ም. ወደ በብራዚል ተልከው በሳን ሳልቮዶር ደ ባሂያ ተመድበው የአገሩ ቀደምት ተወላጆች ቋንቋ እርሱም የቱፒ ቋንቋ በጥልቀት የሚያውቁ ንኡሳንን የኅብረተሰብ ክፍል በማገልገል በቱፒ ቋንቋ የዚያ ቋንቋ መማርያ መጽሓፍ ቀደምት ደራሲ ለመሆን የበቁ የሳን ፓውሎና የሪ ደ ጃነይሮ ከተማ ቀደምት መሥራቾች ውስጥ አንዱ እንደሆኑም የሚነገርላቸው በ 42 ዓመት ዕድሚያቸው በብራዚል የኢየሱሳውያን ማኅበር አለቃ በመሆን ለ 11 ዓመት ያገለገሉ ቅዱስ መሆናቸው የቤተ ክርስቲያን የቅዱሳት የታሪክ ማኅደር ይጠቁማል።







All the contents on this site are copyrighted ©.