2014-04-04 20:13:31

ርዋንዳ ቤተ ክርስትያን ከ20 ዓመታት በፊት በተደረገው የዘር ማጥፋት ግድያ ቍስሎች በመፈወስ ዕርቅ የሰፈናበት የርዋንዳ ኅብረተሰብ ለመገንባት በርትታ መሥራት አለባት


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ትናንትና ለቪዚታ አድ ሊሚና በሮም ለሚገኙ የርዋንዳ ጳጳሳት ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት “የርዋንዳ ቤተ ክርስትያን ከ20 ዓመታት በፊት በተደረገው የዘር ማጥፋት ግድያ ቍስሎች በመፈወስ ዕርቅ የሰፈናበት የርዋንዳ ኅብረተሰብ ለመገንባት በርትታ መሥራት አለባት” ሲሉ ዕርቅና ፍትሕ በሃገሪቱ እንዲነግሥ በተቻላቸው መጠን እንዲጥሩ አደራ ብለዋል፣ቅዱስነታቸው በተለይ ያስታወሱት ያ ከሃያ ዓመታት በፊት በርዋንዳ የተካሄደው የዘር ማጥፋት የእርስ በእርስ ጦርነትና ከአንድ ሚልዮን በላይ ሕይወታቸውን ያጡበት ሁኔታን ነበር፣ ልክ የዛሬ ሃይ ዓመት በርዋንዳ በሁቱ እና ቱሲ መካከል የተካሄደው የእርስ በእርስ ጦርነት በዚሁ ዕለታት ሃያኛ ዓመት ዝክሩ በርዋንዳና በመላው ዓለም እየተስታወሰ ነው፣ ለዚህም ነው ቅዱስነታቸው የፍጻሜው ክብደትና ዘግናኝነት በማስታወስ ገና ያልተፈወሱ ቍስሎች መኖራቸውን በማሳሰብ በተለያዩ ጐሳዎች መካከል ያለው ቅድመ ሁኔታዊ ፍርዶችንና መከፋፈሎችን በማውገድ የዕርቅ ጉዞን እንዲያዳብሩ አደራ ብለዋል፣
ቅዱስነታቸው ይህ ሥራ ቀላል አለመሆኑና ገና ልትፈውሳቸው እጅግ ከባድ የሆኑ ቍስሎችና ስቃዮች እንዳሉ በማሳሰብ የዚሁ ስቃይ ተካፋይ መሆናቸውና በዚሁ ቍስሎች ለሚሰቃዩና ለመላው የርዋንዳ ሕዝብ አለምንም የሃይማኖትና የጐሳ ልዩነት እንዲሁም ፖሎቲካዊ ምርጫ ልዩነት ለሁላቸው በጸሎታቸው እንደሚያስብዋቸው አረጋግጠዋል፣ ለርዋንዳ ቤተ ክርስትያን ዛሬም ቢሆን ከሃይ ዓመታት በኋላ ዕርቅና የቍስሎቹ ፍወሳ ተቀዳሚ ሥራዋ ነው፣ የርዋንዳ ጳጳሳትም ይህንን ለማድረግና በዚሁ ጐዳና ወደፊት ለመራመድ በርትተው መሥራት እንዳለባቸው ምክንያቱም በደሎችን ይቅር ማለትና እውነተኛ ዕርቅን ለማንገሥ የማይቻሉ ቢመስሉም በእምነትና በጸሎት ከጌታ ኢየሱስ ሊገኙ እንደሚቻል አረጋግጠዋል፣ ጉዞው እጅግ ረዥም መሆኑ ለዚህም ትዕግሥት እንዲሁም እርስ በእርስ መከባበርና ውይይት እንደሚያስፈልጉ ገልጠዋል፣
ቤተ ክርስትያን ዕርቅና ሰላም የሰፈነበት የርዋንዳ ማኅረሰብ ለማቆም እንደምትሰራም አረጋግጠዋል፣ በዚህም ጳጳሳት የወንጌል እውነትን በክርስትያናዊ እምነትና ተስፋ እንዲመሰክሩ ቈርጠው መነሣት እንዳለባቸው አሳስበዋል፣ ወንጌል ልቦችን የሚነካበትና ጥልቅ ለውጥ የሚያመጣው በፍቅር የተሳሰርን ስንሆን ብቻ ነው ያሉት ቅዱነታቸው ቤተ ክርስትያንችን አንድ ቃል ሆና መስበክ ያለባት ይህንን ሲሆን ይህንን የምታደርገው ደግሞ ከኵላዊት ቤተ ክርስትያን ጋር እና ከቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ አንድ በመሆን ነው ሲሉ ማንኛውን ቅድመ ፍርድና ጐሳዊ ልዩነትን መሻገር እንዳለባቸውና ሃገራዊ ዕርቅ በመፍጠርና ከመንግሥትም ጋር የመተማመን ግኑኘት በመጠንከር ይሰሩ ዘንድ አደራ ብለዋል፣ እፊታችን ሰኔ 6 ቀን የሚዘከረን የርዋንዳና የቅድስት መንበር ግኑኝነት 50ኛውን ዓመት መዘከሩን አሳስበው ከመንግሥት ጋር ገንቢና እውነተኛ ውይይት ሲደረግ የጋራ የሆነ ሃገራዊ ዕርቅና ኅብረተሰባዊ ግንባታን ያደርብራል ይህንም የሚደረገው ሰብ አዊ ክብሮችን በመጠበቅና ፍትሕና ሰላም በመንገስ እውን ይሆናል፣ ስለዚህ የርዋንዳ ቤተ ክርስትያን ከገዛ ራሷ ወጥታ የዚህ ውይይት መጀመርያ ቀስቃሽ መሆን እንዳለባትም አሳስበዋል፣
ከዚህ በመቀጠል ቅዱስነታቸው ያሳሰቡት ሌላ ነጥብ ደግሞ የትምህርት ጉዳይ ሆኖ በተለይ ወጣቶችን ማስተማር እንዲሁም በስብከተ ወንጌልና ለክህነት በሚደረገው ዝግጅት ም እመናን ተራቸውን በሚገባ እንዲወጡና እንዲያበረክቱ መማር እንዳለባቸው አሳስበዋል፣ ወጣቶችን ማስተማር የአንድ አገር መጻኢ ቍልፍ ነው ያሉት ቅዱስነታቸው በአገሪቱ የተለያዩ ስልጠናዎችና ትምህርት በማበርከት የሚገኙ ውሉደ ክህነትን አመስግነዋል፣
በመጨረሻም በዘመናችን ቤተ ክርስትያንን አደጋ ውስጥ እየጣለ ያለውን ዓለማውነትን ሊያወግዱና ሰርጎ እንዳይገባም በትጋት እንዲጠብቁ አደራ ብለዋል፣ ለመላው የርዋንድ ሕዝብም በኪበሆ ድንግል ማርያም ጥበቃ አቅርበዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.