2014-04-02 16:39:17

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ.ና የቅርብ ተባባሪዎቻቸው ብፁዓን ካርዲናሎችና ጳጳሳት ጉባኤ


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 1 ቀን 2014 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የመሩት የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን የቅርብ ተባባሪዎቻቸው የቅድስት መንበር ጳጳሳዊ ምክር ቤቶችና የቅዱሳት ማኅበራት ሊቀ መናብርትና ተጠሪዎች አበይት ሓዋርያዊ ባለ ሥልጣናት ብፁዓን ካርዲናሎችና ብፁዓን ጳጳሳት ያስተፈ ጉባኤ በአገረ ቫቲካን ሓዋርያዊ ሕንጻ በሚገኘው ቦሎኛ በተሰየመው የጉባኤ አዳራሽ መካሄዱ የቅድስቲ መንበር የዜናና ማኅተም ክፍል መግለጫ ይጠቁማል።
ይኽ በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ተመርቶ የተካሄደው ጉባኤ ቅዱስነታቸው የደረሱት ወንጌላዊ ኃሴት የተሰየመው ሐዋርያዊ ምዕዳን ላይ ያስተነተነና እንዲሁም በተለያዩ የቅድስት መንበር ጳጳሳዊ ምክር ቤቶችና ቅዱሳት ማኅበራት በተናጥል የተሰጠው ምላሽ ያሳደረው መንፈስ ዙርያ የሃሳብ ልውውጥ በማድረግ የተሰነዘሩት አስተያየቶች የቃኝ ሲሆን ዓላማውም ሓዋርያዊ ምዕዳኑን ሠፋ በማድረግ ለማሟላት በሚል እቀድ ላይ ያተኮረ እንደነበርም የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.