2014-03-31 16:05:44

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ በሰዎችና በድኾች መካከል በሚጸናው ምኅረት ኢየሱስ ይጠባበቀናል


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. መጋቢት 28 ቀን 2014 ዓ.ም. ቅዱስ ኣባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የአዲስ አስፍሆተ ወንጌል ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት አቢይ ጾም ምክንያት በማድረግ 24 ሰዓት ለጌታ በሚል መርሃ ግብር ባነቃቃው የንስኃ ቀን በይፋ ለማስጀመር ከቀትር በኋላ በቅዱስ ጲጥሮስ ባዚሊካ በመሩት የሚሥጢረ ንስኃ ሊጡርጊያ፦ “መለወጥ የአንድ አፍታ ጥያቄ ሳይሆን በመላ ሕይወት ቀጣይነት የሚኖረው ተግባር ነው” በሚል ቅዉም ሃሳብ ላይ ያነጣጠረ ሥልጣናዊ ስብከት ማሰማታቸው የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ጃዳ አኵይላኒ ገልጠው ቅዱስ አባታችን የሠሩት የምሥጢረ ንስኃ ሊጡርጊያ አጠናቀው በማናዘዣ ሥፍራ ተገኝተው ተናዘው እንዳበቁ በተራቸው አንዳንድ ምእመናን እንዳናዘዙና በዚሁ በተካሄደው ሥነ ሥርዓት 61 አናዛዥ ካህናት መሳተፋቸው አስታውቀዋል።
ቅዱስ አባታችን ባሰሙት ሥልጣናዊ ስብከት፦ “መለኰታዊ ምህረት ያጣጣመ በሰዎችና በድኾች መካከል ምኅረት ይጸና ዘንድ ቀንደኛ ተወናያን ሆኖ እንደሚገኝ የተረጋገጠ ነው። በተናቁት በታናናሽ ወንድሞች ዘንድ ኢየሱስ ይጠባበቀናል፣ ምኅረት ተቀብለን ምኅረትን እንሰጣለን፣ በታናናሽ ወንድሞቻችን ዘንድ ከኢየሱስ ጋር ለመገናኘት እንጓዝ፣ አዎ እንዲህ ባለ ሁነት ፋሲካን በእግዚአብሔር ደስታ እናከብራለን። መለወጥ የአንድ አፍታ ሁነት ሳይሆን በመላ ሕይወት የሚደረግ ጥረት ነው። ማንም ከእኛ ውስጥ ኃጢአተኛ አይደለሁኝም ሊል አይችልም…” ብለው ሐዋርያ ዮሐንስ ንስኃ ግቡ በማለት ጌታ ታማኝነትንና ቅንነትንና ምኅረትን የሚለግሰን መሆኑ በማረጋገጥ አዲስ ሰው በምስጢረ ጥምቀት የእግዚአብሔር ልጅ የሚያደርገው የክርስቶስና የእርሱ አካል የሆነቸው ቤተ ክርስቲያን አካል የሚያደርገን የእግዚአብሔርን ሕይወት የሚቀበል መሆኑ ቅዱስነታቸው በማረጋገጥ፦ “ይኽ አዲስ ሕይወት ተጨባጩን ዓለም በጠቅላላ ሁሉን ነገር በአዲስ አመለካከትና እይታ፣ በጠፊው ዓለም ዘላቂነት በሌለው ነገር ሳንዘናጋ እንድንገነዘብ ያደርገናል፣ ስለዚህም ነው ኃጢአትና ወደ ኃጢአት የሚመሩን ልምዶች በማስወገድ አስፈላጊ በሆነው ነገር ላይ እናተኰር ዘንድ የምንጠራው” እንዳሉ የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ አኵይላኒ አክለው፦ “በእግዚአብሔር አዲስ በሆነው ሰው ዘንድ ልብ መልካም ልማዶች ይታያሉ፣ በእውነት በመናገርም ኃሰትንና የኃስተን ተግባር ያገላል፣ ያለህን ተካፈል እንጂ አተስረቅ፣ ከሁሉም ጋር በተለይ ደግሞ በከፋ ድኽነት ጫንቃ ሥር ከሚገኙት ጋር ተካፍሎ ለመኖር ደግ ሁን፣ ምኅረትን እንጂ ቂም በቀልን ማግለል የሌላውን ሰው ስም የሚያጎድፍ ስለ ሌላው ክፉ ከመናገር መቆጠብ፣ አወንታዊው ሁነት መመልከት፣ መታደስ ማለትም እንዲህ ነው። “የኢየሱስ ፍቅር ዘለዓለማዊ ነው፣ ይኽ ፍቅር የእግዚአብሔር ሕይወት በመሆኑም ፍጻሜ የለውም። ኃጢአትን የሚያሸንፍ ዳግም ለመነሳት በአዲስ በንፈስ ለመጀመር ኃይል የሚሰጥ ነው፣ ምክንያቱም በምኅረት ልብ ይታደሳል ወጣት ልብም ይሆናል። ክርስቲያን ይኸንን ፍቅር በኖረ ደረጃ የክርስቶስ ታማኝ ሐዋርያት ይሆናል። ፍቅር በገዛ እራስ ተዘግቶ መቅረትን ችሎ አይኖርም፣ በባህርዩ ክፍት ነው፣ የሚስፋፋ የሚያፈራ ዘወትር አዲስ የሚያደርግ ነው” ካሉ በኋላ በመጨረሻም የአዲስ አስፍሆተ ወንጌል ያነቃቃው 24 ሰዓት ለጌታ በተሰኘው የንስኃ ጥሪ መሠረት በሮማ ከተማ የተለያዩ አቢያተ ክርስቲያን ለሚሥጢረ ንስኃ ለ 24 ሰዓት ክፍት ሆነው በማገልገል በሁሉም ቁምስናዎች ካህናት ለማናዘዝ ዝግጁዎች ሆነው እንደተገኙም አስታውሰው፦ በጌታ ታድሳችሁ በዕለታዊ ሕይወታችሁ ለምትገናኙዋቸው ሁሉ ኃዳሴን በማቅረብ ከጌታ ጋር ዳግም ታድሶ የጸናው ጓደኝነታቸሁ እንዲጎላ አድርጉ፣ እግዚአብሔር አባታችን ይጠባበቀናል ይምረናል ወደ እርሱ ስንመለስ እርሱ አቢይ በዓል ያደርጋል ለጌታና የጌታ አቢይ በዓል ወደ እርሱ የሚመለስ ሰው ነው” በማለት ያስደመጡት ሥልጣናዊ ስብከት እንዳጠቃለሉ አስታወቁ።








All the contents on this site are copyrighted ©.