2014-03-28 16:26:07

የ ዩ ኤስ መንግስት መሪ ፕረሲዳንት ባራክ ኦባማ ቫቲካን
ይፋ ጉብኝት ፡


ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ትናትና ረፋድ ላይ የዩናይትድ ስቴትስ መንግስት ፕረሲዳንት ባራክ ኦባማ ተቀብለው አነጋግረዋል። ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት እና ፕረሲዳንቱ ሲገናኙ ይህ የመጀመርያ ግዝያቸው መሆኑ ነው ። ፕረሲዳንት ባራክ ኦባማ ቫቲካንን ሲጐበኙ የትናትናው ሁለተኛ ግዚያቸው ነው። በ209 ሐምለ ወር ላይ እኤአ ቫቲካንን መጐብኘታቸው እና በወቅቱ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ከነበሩ ከበነዲክት 16ኛ ጋር መጐብኘታቸው ይታወሳል።ይሁን እና ቫቲካን ላይ የወጣ መግለጫ እንዳመለከተው ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ እና ፕረሲዳንት ባራክ ኦባማ ለ50 ደቂቃ በተነጋገሩበት ግዜ ስለ ሰላም የሃይማኖት ነፃነት የስደተኞች መብት እና የሕልና ተቃውሞ በመሳሰሉ ርእሰ ጉዳዮች ሐሳብ ለሐሳብ ተለዋውጠዋል ። የዩ ኤስ አመሪካ መሮኢ ፕረሲዳንት ባራክ ኦባማ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ማሕበራዊ ፍትህ ለማንገስ የሚያደርጉት ጥረት እና ስለ ድሆች ያላቸውን ሐሳቢነት እንደሚያዳንቁ ገልጠዋል።ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ እና ፕረሲዳንት ባራክ ኦባማ የሰዎች ሕገ ወጥ ዝውውር እና አስከፊነቱ ትኩረት በመስጠት መወያየታቸው ተያይዞ ተመልክተዋል። ፓፓ ፍራንሲስ ለሳቸው እና ቤተ ሰቦቻቸው እንዲጸልዩላቸው ፕረሲዳንት ባራክ ኦባማ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስን መጠየቃቸው የቫቲካን የዜና አገልግሎት ጠቁሞ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት እና ፕረሲዳንት ባራክ ኦባማ ስጣታ መለዋወጣቸው አስገንዝበዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ ከየቅድስት መንበር ዋና ጽሐፊ ከብፁዕ ካርዲናል ፒየትሮ ፓሮሊን ጋ ተገናኝተው በቅድስት መንበር እና የዩ ኤስ መንግስት መካከል ያለውን ግንኙነት ዓለም አቀፍ ነክ ጉዳቶች በተለይ የመካከለኛው ምስራቅ ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ ርእሰ ጉዳይ መወያየታቸው የቫቲካን መግለጫ አስገንዝበዋል። የዩ ኤስ አመሪካ መራሄ መንግስት ፕራሲዳንት ኦባማ ከቫቲካን ጉብኝት በኃላ ፡ ከጣልያን ርእሰ ብሔር ጆርጆ ናፖሊታኖ ከጠቅላይ ሚኒስትር ማተዮ ረንጺ ጋር ተገኛተዋል ። ከቀትር በኃላም የዘለዓለማዊት ሮማ ልዩ መለዮ የሆነውን ኮለሰዩም በግል ጐብኝተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.