2014-03-26 17:06:07

የር.ሊ.ጳ ሳምታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ፤


ውድ ወንድሞችና እኅቶች! እንደምን አደራችሁ!
የመባቻ ምሥጢራት በማለት የሚታወቁትን ምሥጢረ ጥምቀት ሜሮንና ቅዱስ ቍርባንን ታላቅ የጸጋ ስጦታ ሆነው በክርስቶስ እንደአዲስ እንድንወለድ የሚያደርጉን መሆናቸውን አይተናል፣ እኛ ሁላችንን እንደ የጌታ ኢየሱስ ተከታዮች በቤተ ክርስትያን አንድ የሚያደርገን መሠረታዊ ጥሪም ይህ ነው፣ ከእነዚህ በመቀጠል ሌሎች ሁለት ምሥጢራት ልዩ ጥሪ የሚያመለክቱ አሉ እነርሱም ምሥጢረ ክህነትና ምሥጢረ ተክሊል ናቸው፣ እነኚህ ምሥጢራት ክርስትያን ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተ ክርስትያንን ለማቆም ሕይወቱን በሰዋበት ምሳሌ እና በክርስቶስ ስም ሕይወትን የፍቅር ስጦታ አድርጎ መስጠትን ያመለክታሉ፣
የክህነት ምሥጢር በመዓርገ ጵጵስና መዓርገ ክህነትና መዓርገ ዲቍና የቆመ ሲሆን ጌታ ኢየሱስ ለሓዋርያት መንጋውን በመንፈስ ቅዱስ ኃይልና እንደልቡ እንዲጠብቁ አደራ በሰጣቸው መሠረት የአገልግሎት ሥልጣን ነው፣ ይህ ማለትም የኢየሱስ መንጋን በመንፈስ ቅዱስ ሥልጣን እንጂ በሰው ኃይልና በገዛ ፍላጎት ችሎታ ሳይሆን በመንፈስ ቅዱስ ኃይልና አፍቃሪው የኢየሱስ ልብ እንደሚፈልገው እንደ ልቡ መጠበቅ ነው፣ አንድ ካህን ጳጳስ ወይምንም ዲያቆን የጌታ መንጋን በፍቅር መጠበቅ አለባቸው፣ በፍቅር ካላደረገው ምንም ጥቅም የለውም፣ በዚህ መንገድ ተመርጠውና መዓርግ ለብሰው ለዚህ አገልግሎት የሚላኩ ሁላቸው የኢየሱስ በመንጋው መካከል መኖሩን ይቀጥላሉ፤ ይህንን የሚያደርጉት ደግሞ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል በእግዚአብሔር ስምና በፍቅር ነው የሚያደርጉት፣
የመጀመርያው ነጥብ እነኚህ ይህንን መዓርግ የሚቀበሉ የማኅበረ ክርስትያኑ ኃላፊዎች ናቸው፣ የትኛው ኃላፊነት ብለን የጠየቅን እንደሆነ ደግሞ በኢየሱስ ዘንድ አለቃ መሆን ለአገልግሎት መዘጋጀት ነው፣ ይህንን ደግሞ ለሐአርያት እንዲህ ሲል አስተማራቸው “የአሕዛብ አለቆች እንዲገዙአቸው ታላላቆቹም በላያቸው እንዲሠለጥኑ ታውቃላችሁ። በእናንተስ እንዲህ አይደለም፤ ነገር ግን ማንም ከእናንተ ታላቅ ሊሆን የሚወድ የእናንተ አገልጋይ ይሁን፥ ከእናንተም ማንም ፊተኛ ሊሆን የሚወድ የእናንተ ባሪያ ይሁን፤ እንዲሁም የሰው ልጅ ሊያገለግል ነፍሱንም ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣም፣” (ማቴ 20፤25-28. ማር 10፤42-45) አንድ ጳጳስ ማኅበሩን የማያገልግል ከሆነ ይሄ ጥሩ አይደለም፣ እንዲሁም ማኅበሩን የማያገልግል ካህን ከሆነም ይህም ጥሩ አይደለም ሁላቸው ተሳስተዋል፣
ሌላው ከክርስቶስ ጋር በሚደረገው ምሥጢራዊ መዋሃሃድ ከክህነት የሚፈልቀው ጸባይ ደግሞ ለቤተ ክርያትያን የሚኖረው ያሚያቃጥል ፍቅር ነው፣ ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ኤፈውሶን ሰዎች በጻፈው ስለክርስቶስ የሚለውን እናስተንግን፤ “ባሎች ሆይ፥ ክርስቶስ ደግሞ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ወደዳት ሚስቶቻችሁን ውደዱ፤ በውኃ መታጠብና ከቃሉ ጋር አንጽቶ እንዲቀድሳት ስለ እርስዋ ራሱን አሳልፎ ሰጠ፤ እድፈት ወይም የፊት መጨማደድ ወይም እንዲህ ያለ ነገር ሳይሆንባት ቅድስትና ያለ ነውር ትሆን ዘንድ ክብርት የሆነችን ቤተ ክርስቲያን ለራሱ እንዲያቀርብ ፈለገ።” (5፤25-27) ይላል፣ በክህነታዊ መዓርግ ጸጋ አንድ ካህን ሁለመናውን ለቤተ ክርስትያን ይሰዋል በሙሉ ልቡም ያፈቅራታል፤ ቤተሰቡ እርሷ ናትና፣ ጳጳሳትና ካህናት ቤተክርስትያንና ማኅበረ ክርስትያኖቻቸውን ያፈቅራሉ፣ እንዴት ያለን እንደሆነን ደግሞ ልክ ክርስቶስ እንዳፈራት አድርገው ያፈቅርዋታል፣ ስለ ቃል ኪዳን ቅዱስ ጳውሎስ ባሎች ኢየሱስ ቤተ ክርስትያኑን እንደሚያፈራት ሚስቶቻችሁን አፍቅሩ ይላል፣ ይህ የፍቅር ታላቅ ምሥጢር ነው ማለትም የአገልግሎቱና የቃል ኪዳኑ ፍቅር፣ እነኚህ ሁለት ምሥጢራት የሰው ልጆች እንደምሥጢር ወደ ጌታ የሚጓዙባቸው ጐዳናዎች ናቸው፣ በመጨረሻም ሐዋርያ ጳውሎስ ልተማሪው ጢሞቴዎስ የሚለውን አደራ “በትንቢት ከሽማግሌዎች እጅ መጫን ጋር የተሰጠህን፥ በአንተ ያለውን የጸጋ ስጦታ ቸል አትበል። “(1ጢሞ 4፤14) በማለት ያስጠነቅቀዋል፣ የጳጳሱ ተል እኮና አገልግሎት እንዲሁም የካህኑ ተል እኮና አገልግሎት በጸሎት ቃለ እግዚአብሔር በማዳመጥና በየዕለቱ መሥዋዕተ ቅዳሴን በማሳረግ እንዲሁም ምሥጢረ ንስሓን በማዘውተር ካልተጠበቀና ካልተንከባከቡት እውነተኛ የአገልግሎት ትርጉምን ሊያጠፋን ከኢየሱስ ጋር በጥልቀት አንድ በመሆን የሚገኘው ደስታ ሊጠፋ ይችላል፣ የማይጸልይ ጳጳስ ቃለ እግዚአብሔር የማይሰማና በየዕለቱ መሥዋዕተ ቅዳሴ የማያሳርግ እንዲሁም ለምሥጢረ ንስሓ ራሱን የማያቅርብ ካህንም ይሁን ይህንን የማያደርግ ከሆነ ከክርስቶስ ጋር ያላቸው አንድነት ያጠፋሉ ፈሪሳዊ ሕይወት በመኖርም ቤተ ክርስትያንን ያቆስላሉ፣ ስለዚህ ጳጳሳትንና ካህናትን ጸሎት እንዲያደርጉ ቃለ እግዚአብሔርን እንዲያዳምጡ በየዕለቱ መሥዋዕተ ቅዳሴ እንዲሳርጉ የምሥጢረ ኑዛዜ ልማድም እንዲሆንቸው በጸሎት እንርዳቸው፣ ይህ እጅግ አስፈላጊ ነው፣ ምክንያቱም በቀጥታ የጳጳሳቱና የካህናቱ የሕይወት ቅድስናን ስለሚመለከት፣ በአንጎሌ በሚመላለሰኝ አሳብ ትምህርቱን ለማጠቃለል እወዳለሁ፣ ካህን ለመሆን ምን ማድረግ ያስፈልጋል፣ የት ይሸጡ ይሆናል? እንደዛ አይደለም አይሸጡም፣ የክህነት ጥሪ ጀማሪ ጌታ ራሱ ነው፣ ጌታ ይጠራል ካህን ለመሆን የሚፈልገውን ሁሉ ይጠራል፣ ዛሬ እዚህ አደባባይ ይህ ጥሪ የተሰማቸው ወጣቶች ሊኖሩ ይችላሉ፣ ካህን የመሆን ፍላጎት ከእግዚአብሔር በሚመጡ ነገሮች ሌሎችን የማገልገል ፍላጎት ያላቸው ይኖሩ ይሆናል፣ መላው የኑሮ ዘመንህን ትምህርት ክርስቶስ ለማስተማር ማጥመቅ ምሕረት ማደል መስዋዕተ ቅዳሴን ማሳረግ ሕመምተኞችን መርዳት ወዘተ ፍላጎቶች ሊኖሩ ይችላሉ፣ አዎ መላው የምሥጢረ ክህነት ሕይወት እንደዛ ነው፣ ምናልባት ከእናንተ መካከል ኢየሱስ ይህንን ጥሪ በልቡ ያኖረለት ካለ በደንብ ተንከባከቡት በልባችሁ አድጎ ለመላዋ ቤተ ክርስትያን የሚሆን ፍሬ እንዲያፈራም በርትታችሁ ጸልዩ፣ እግዚአብሔር ይስጥልኝ፣








All the contents on this site are copyrighted ©.