2014-03-26 16:08:45

ስምንተኛው ዓለም አቀፍ የቤተሰቦች ቀን


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. በ 2015 ዓ.ም. የሚካሄደው ዓለም አቀፍ የቤተሰቦች ቀን በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት በፊላደልፊያ ከተማ እንዲከናወን መወሰኑ የቤተሰብ ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ቪንቸዞ ፓሊያ ትላትና በቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ሕንፃ በሚገኘው የጉባኤ አዳራሽ ተገኝተው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ማሳወቃቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ፓውሎ ኦንዳርዛ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችለዋል።
በአሁኑ ወቅት የተናቀና ለተለያየ አደጋ ተጋልጦ የሚገኘው ቤተሰብ ንቁ ልባም ብርቱ በፍቅር የተሞላ ቤተሰብ የሚንከባከብ የሚመራ ለሙሉ እድገት የሚደግፍ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ አስፈላጊ መሆኑ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ያሰመሩበት ሃሳብ ብፅዕ አቡነ ቪንቸንዞ ፓሊያ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ጠቅሰው፣ በፊላደልፊያ ሊካሄድ የተወሰነው ስምንተኛው ዓለም አቀፍ የ2015 ዓ.ም የቤተሰቦች ቀን እ.ኤ.አ. ከመስከረም 22 ቀን እስከ መስከረም 27 ቀን የሚከናወን መሆኑ ገልጠው፦ ስለ ቤተሰብ ጉዳይ በሁሉም አቢያተ ክርስቲያን በፖለቲካው ዓለም በመንግሥታት በተለያዩ ማሕበራት ወቅታዊ የውይይትና የአስተንትኖ ማእከል እንዲሆን የሚያነቃቃ ነው ሲሉ። በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የተሳተፉት የፊላደሊፍያ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ቻርለስ ጆሰፍ ቻፑት በበኩላቸውም፦ በቤተሰብ ላይ የተከሰተው የሚከሰተው ተጨባጭ ሁነት እርሱም ፍች፣ ቃል ኪዳን ማፍረስ መለያየት ተፋትቶ ዳግም መጋባት፣ የመሳሰሉት በተለይ ደግሞ በአሁኑ ሰዓት የሚሰማው በተለያዩ አገሮች በሕግ የተፈቀደ እንዲሆን እየተባለ የሚነገረው በአንዳዊ ጾታዊ ስሜት ባላቸው ሰዎች መካከል ጋብቻ መፍቀድ የሚባለውን ጠቀሰው ይህ ጉዳይ አይመለከተኝም ብሎ በቀላሉ መመልከቱ አላስፈላጊ መሆኑና ተገቢ ምላሽ የሚያሻው ነው እንዳሉ የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ኦንዳርዛ፣ የወሲብ ዓመጽ ሰለባ የሆኑትን ቤሰቦች የቤተሰብ አባላት ጭምር ቀርቦ ከደረሰባቸው ከባድ ሰብአዊ ሥነ አዕምሮአዊ ጉዳት ተላቀው መጪው ሕይወታቸው በሚገባ ለመምራት እንዲችሉ አስፈላጊው የተሟላ ሰብአዊ መንፈሳዊ ሥነ አዕምሮአዊ ድጋፍ በማቅረቡ ረገድ ቤተ ክርስቲያን ለቤተሰብ በምትሰጠው ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ አገልግሎት አማካኝነት ተጠምዳ ሰብአዊ መንፈሳዊ ሕንጸት ታቀርባለች ብለው፣ ይኽ ደግሞ ለጋራ ጥቅም ያቀና ነው እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ኦንዳርዛ አመለከቱ።







All the contents on this site are copyrighted ©.