2014-03-24 19:44:48

ከኢየሱስ ጋር መገናኘት ሕይወትን ይለውጣል! ምሕረት ከቅድመ ፍርድ እጅግ ይልቃል፣


ይህንን ያሉት ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ትናንትና እኩለ ቀን ላይ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡት ም እመናንና ነጋድያን ከጸሎተ መል አከ እግዚአብሔር በፊት ባቀረቡት ጉባኤ አስተምህሮ ነበር፣ ቅዱስነታቸው ስለሳማራዊትዋ ሴትና ስለ ኢየሱስ ውይይት የሚመለከተውን የዕለቱን ቃለ ወንጌል መነሻ በማድረግ “ጌታ ከማንኛው ቅድመ ሁኔታው ፍርድ በላይ ነው” ሲሉ ያ በብዙ ነገር ከሰዎች ተገልላ ብቸኛ ጊዜን በመምረጥ ከያዕቆብ ኩሬ ውኃ ለመቅዳት በእኩለ ቀን አከባቢ እቦታው ለተገኘችው ሴት ኢየሱስ ሲውያያትና መገድ አላፊ ሊያቀርበው ከሚችለው “ውኃ አጠጪኝ” ከሚለው ጥያቄ በመነሳት በአይዳውያንና ሰማርያውያን መካከል ያለው የመለያየት ሁኔታን ተሻግሮ እንዲሁም መሠረታዊ የእምነት አስተያየታቸው ልዩነትን ተሻግሮ ያች እውነተኛ የጌታ ጥማት የነበራትን ሴት ቀስ በቀስ ማንነቱን በመግለጥና እርሱ እውነተኛ የሕይወት ውኃ ምንጭ መሆኑ ተገለጠላት፣ ሴቲቱ ሁኔታውን በሚገባ ከተገነዘበች በኋላ የምሥራች ዜናውን ለወገኖችዋ ለመንገር እንስራዋን ትታ አገር ቤት በመግባት ነቢዩንና አዳኙን እንዳገኘት ስታበስር መንደረኞቹ ደግሞ በመንደራቸው እንዲቆይ በጠየቁት መሠረት ለሁለት ቀናት ያህል በሰማርያ መስበኩንና አብዘኛዎቹ በእርሱ እንዳመኑ ይገልጣል፣ ጌታ ኢየሱስ ሳምራዊትዋን “ውኃ አጠጭኝ” ብሎ መጠየቁ ትልቅ የውይይቱ መነሻ መሆኑን እንዲህ ሲሉ ገልጠዋል፣
“በባህሉ መሠረት አንድም ቃል እንኳ ትንፍስ ብሎ ለመናገር በማይችልበት ሁነኢታ ኢየሱስ ውኃ አጠጭኝ ሲል ቀስ በቀስ ጥልቅ የሆነ ውይይት ይጀምራል በዚህም ወደ ውስጣዊ ሕይወትና በመግባት ቀስ በቀስ ወደ ደህንነት ያቀርባታል፣ ኢየሱስ አስፈላጊነት ያለው ሰው ባየበት ጊዜ ወደ ፊት እንደሚገፋ ይህም የሚያደርገው ሁሉን የሚያፈቅር በመሆኑ ግልጥ ነው፣ ይህንን ከማድረግ የባህሉ ጫና ወይንም ቅድመ ሁኔታዊ ፍርዶች ሊያቆሙት አይችሉም፣ ኢየሱስ ሴቲቱን ሲያወያያት ምንም ፍርድ አያደርግም ከልማዳዊ የሰላምታ ቃላት በመሻገርም ሴትየዋን ታላቅ ግምት በመስጠት ያወያያታል፣ ጥማቱ ከውኃ ጥማት ወዲያ ነበር የደህንነት ጥማት ሴትየዋ ልብዋን ለጌታ እንድትከፍት ለማድረግ ነበር፣
“ሴትየዋ በዚሁ የኢየሱስ አቀራረብ ተመሰጠች፣ እኛ ሁላችን የምንጠይቃቸው ነገር ግን በልባችን አምቀን የምንይዛቸው ጥያቄዎች ትጠይቀዋለች፣ እኛም እንደዛ ዓይነት ብዙ ጥያቄዎች አሉን ነገር ግን ኢየሱስን ለመጠየቅ ብርታት ይጐድለናል፣ ውዶቼ ዘመነ ጾመ አርባ ወደ ውስጣችን እንድናተኵርና እውነተኛ መንፈሳዊ ፍላጎቶቻችንን ለጌታ እንድናቀብና በጸሎት የጌታ እርዳታ እንድንጠይቅ ጊዜው ነው፣ ዛሬም ቢሆን የሳምራዊትዋ ሴት ምሳሌ በመከተል ጌታ ሆይ ዳግም እንዳልጠማ የሕይወት ውኃ ስጠኝ እንበለው፣
በወንጌሉ የሚገኘው ሌላ ነጥብ ደግሞ ሓዋርያቱ በሁኔታው እጅግ መገረማቸው ነገር ግን ደፍሮ ለምን ከሴት ጋር እንደሚወያይና የማይሆን ነገር እያደረገ ነው ብሎ ሊናገረው የቻለ የለም፣
“ሆኖም ግን ጌታ ከቅድመ ፍርዶች እጅግ የላቀ ነው ለዚህም ከሳምራዊትዋ ጋር ለመነጋገር ምንም ፍራቻ አልነበረውም፤ ምክንያቱም ምሕረት ከሁሉም ቅድመ ሁኔታዊ ፍርዶች ይልቃልና፣ ይህንን ጠንቅቀን ማወቅና ማስታወስ አለብን ከቅድመ ሁኔታዊ ፍርድ የእግዚአብሔር ምሕረት ይልቃል ኢየሱስም ታላቅ መሓሪ ስለሆነ ይህንን አደረገ፣ ለዚህም ነው ሳምራዊትዋ ምሕረቱን ካጣጠመች በኋላ ወዲያውኑ ወደ ከተማው በመሄድ ሁኔታውን ለሰዎች የንገረች፣ ውኃ ለመቅዳት ወደ የያቆብ ውኃ ጉዳጓድ ሄደች ነገር ግን ሌላ ውኃ አገኘት የሕይወት ውኃ የምሕረት ውኃ አገኘች፣ በሕይወት ዘመንዋ ሁሉ ስትሻው የነበረችውን ውኃ አገኘት፣ ያወግዛትና ይገልላት ወደነበረው መንደር በመሄድም መሲሁን አዳኙን እንዳገኘችው ለመስበክ ተረዋወጠች፣
“መሲሁ ሕይወትዋን የለወጠ ሲሆን ምክንያቱም ከኢየሱስ ጋር መገናኘት ሕይወትን ይለውጣልና፣ ዘወትር፣ አንድ እርምጃ ወደፊት ነው፣ እርምጃውም ወደ እግዚአብሔር ያቀርበናል፣ ስለዚህ ከኢየሱስ ጋር የምናደርገው እያንዳንዱ ግኙኝነች ዘወትር ሕይወትን ይለውጣል፣ በኢየሱስና በሳምራዊትዋ ሴት መካከል ከተድረገው ውይይት መካከል አንዱ እግዚአብሔር የት እንደሚገኝ አይሁድና ሳምራውያንም የተለያየ አመለካከት እንዳላቸው አይሁድ በኢየሩሳሌም ሲሉ ሳምራውያን ደግሞ በአንድ ተራራ እንደሚገኝ ያምናሉ የሚል ነበር፣ ኢየሱስ ግን ሁሉን በማለፍ በእግዚአብሔር ፍቅር ፊት ሁሉም ምንም እንዳልደለ እንዲያው እግዚአብሔር መንፈስ በመሆኑ ከዚያ ሰዓት ጀምሮ እግዚአብሔርን በመንፈስና በእውነት የሚሰግድበት ጊዜ እንደደረሰ ይነግራታል፣
ስለዚህ ሁላችን ወደ እግዚአብሔር የሚያቀርበን ውኃን ከጌታ እንጠይቅ እንደሳምራዊትዋም ጌታን የማግኘት ደስታን እንመስክር ሲሉ ትምህርታቸውን ደምድመዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.