2014-03-19 20:02:12

የር.ሊ.ጳ ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ


ውድ ውንድሞችና እኅቶች እንደምን አደራችሁ! ዛሬ መጋቢት 19 ቀን የእመቤታችን ድንግል ማርያም እጮኛና የእንተላዕለ ኩሉ ቤተ ክርስትያን ጠባቂ የሆነ የቅዱስ ዮሴፍ በዓል እናከብራለን፣ ስለዚህ የዛሬን አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ ስለ ቅዱስ ዮሴፍ ይሆናል፣ እመቤታችን ድንግል ማርያምንና ልጇ ኢየሱስን መጠበቅን ስላወቀ እንድናወቀውና እንድናከብረው ይገበናል፣ የቅዱስ ዮሴፍ ዋና ባህርይ ጠባቂ መሆን ነው ተልእኮውም ያው የጥበቃ ተልእኮ ነው፣ ዛሬ ጥበቃን የሚመለከት ልዩ አመለካከት ይዤላችሁ ቀርቤ አለሁ፣ ይህ ልዩ ጥበቃ ደግሞ የማስተማር ሂደትን የሚመለከት ነው፣ ኢየሱስን የጠበቀና ያሳደገ እንዲሁም በጥበብና በዕድሜና በጸጋ ሲያድግ ደግሞ የሸኘው ቅዱስ ዮሴፍን የአስተማሪ ምሳሌ በማድረግ እንመለከታለን፣
ቅዱስ ዮሴፍ የኢየሱስ አባት ነበር እርግጥ ባህርያዊ አባቱ እግዚአብሔር ነበር ነገር ግን ቅዱስ ዮሴፍ በኢየሱስ እድገት አባት ማድረግ ያለበትን ያደርግ ነበር፣ እንታድያ እንዴት አሳደገው ብለን የጠየቅን እንደሆነ ደግሞ በወንጌሉ እንደተመለከተው በጥበብ በዕድሜና በጸጋ ነው መልሱ፣ በዕድሜ ማደግ ከሚለው የጀመርን እንደሆነ ባህርያዊ የሰውነት ማደግ ማለትም በሥጋና በሥነ ልቦና ማደግን ያመለክታል፣ ቅዱስ ዮሴፍ ከእመቤታችን ድንግል ማርያም ጋር በመተባበር የኢየሱስ ማሳደግ ኃላፊነትን በመውሰድ በሚገባ አሳደገው፣ እርግጥ ነው አስፈላጊው የዕድገት ስልጠና እንዳይጐድል ሁሌ ስለእርሱ ያስብ ነበር፣ ይህ ጥበቃ እጅግ ከባድ መሆኑን መዘንጋት የለብንም የከበደውም ደግሞ ገና ሕጻን ልጅ ሳለ ከእናቱ ማርያም ይዞት ወደ ግብጽ ሲሸሽና ከባዱን የጥገኝነት ኑሮ ሲኖር፣ ምን ይሁን ዮሴፍም ኢየሱስን ከሄሮድስ እጅ ለማዳን ከእርሱና ከማርያም ጋር ወደ ግብጽ ተሰደደ፣ ከስደት በኋላ ወደ ናዝሬት በተመለሱበትና እንደ ቤተሰብ መኖር ከጀመሩ የኢየሱስ የረዘመው ጊዜ እዛ ያልፋል፣ በእነዚህ ዓመታት ዮሴፍ ኢየሱስን የጽርበት ስራውን አስተማረው ኢየሱስም የእንጨት ጠራቢነት ስራውን ከአባቱ ተማረው፣ ቅዱስ ዮሴፍ ልጁን በእንዲህ ያለ መንገድ አሳደገው፣
ወደ ሁለተኛው የልጅ ማሳደግ ወገን ያለፍን እንደሆነ ደግሞ ያ በጥበብ ማደግ የሚለው ነው፣ ቅዱስ ዮሴፍ ለኢየሱስ የዚህ ጥበብ አር አያና መምህር ነበር ይህ ጥበብ ከእግዚአብሔር ቃል ይመገባል፣ ቅዱስ ዮሴፍ ታናሹን ኢየሱስ እንዴት አድርጎ የእግዚአብሔር ቃል እየሰማ እንዳሳደገው ያሰብን እንደሆነ ከሁሉ በላይ ደግሞ በናዝሬት በሚገኘው ቤተ መቅደስ አብሮት እየሄድ መሆኑን እንገነዘባለን፣ ኢየሱስ በቤተ መቅደሱ ቃለ እግዚአብሔርን እንዲሰማ ቅዱስ ዮሴፍ ይሸኘው ነበር፣
በመጨረሻም ሶስተኛውን ነጥብ የተመለከትን እንደሆነ በጸጋ ማደግን ነው፣ ስለዚህ ጉዳይ ቅዱስ ሉቃስ ኢየሱስን በተመለከተ ሲጽፍ “የእግዚአብሔር ጸጋ በእርሱ ላይ ነበር” (2፤40) ይላል፣ እዚህ ላይ በዕድሜና በጥበብ ከማደግ አንጻር የተመለከትነው እንደሆነ የቅዱስ ዮሴፍ ድርሻ የተወሰነ ነው፣ ነገር ግን አንድ አባትና አንዲት እናት ልጃቸውን በጸጋ ስለማደግ የሚያደርጉት የለም ማለት ታላቅ ስህተት ይሆናል፣ ኢየሱስን በዕድሜ በጥበብና በእግዚብሔር ጸጋ ማሳደግን ነው ቅዱስ ዮሴፍ ያደረገው፣ በሶስቱም ጐኖች እንዲያድግ ማድረግ እንዲያድግ መርዳት ነበር ሥራው፣
ውድ ወንድሞችና እኅቶች የቅዱስ ዮሴፍ ተል እኮ እርግጥ አንድና የማይደገም ነበር ምክንያቱም ሁኔታው በፍጹም ልዩ ነውና፣ ሆኖም ግን ኢየሱስን በሚጠብቅበት ጊዜ በዕድሜ በጥበብና በጸጋ እንዲያድግ ያስተምረው ነበር ስለዚህ የሁሉም አስተማሪ አር አያን የሁሉም አባቶች ምሳሌ ነው፣ ስለዚህ ለወላጆችና ለካህናት እንዲሁም በቤተ ክርስትያንና በማኅበረሰባችን የማስተማር ኃላፊነት ላላቸው ሁላቸው በቅዱስ ዮሴፍ ጠበቃ ስር አማጥናለሁ፣ ዛሬ የቅዱስ ዮሴፍ በዓል የአባቶችም በዓል ስለሆነ ሁላቸውን ወላጆች ሁላቸውን አባቶች ልዩ ሰላምታዬን ከልቤ አቀርባልችኋለሁ፣ እስቲ በአደባባዩ እንመልከት አንዳንድ አባቶች አሉን? አባቶች እጆቻችሁን አንሱ! በዚሁ የእናተው ዕለት በሆነው ደስ ይበላችሁ ልጆቻችሁ እንዲያድጉ በመተው ሁሌ እጐናቸው እንድትሆኑ እግዚአብሔር ልዩ ጸጋ እንዲሰጣችሁ እለምናለሁ፣ ልጆቻችሁ እናንተን ይፈልጋሉ ሁሌ ቅርበታችሁ እንድያለያቸው ፍቅራችሁ እጅግ ያስፈልጋቸውል፣ ለልጆቻቸው እንደ የዕድሜ የጥበብና የጸጋ ጉዞ ጠባቂ የሆነው ቅዱስ ዮሴፍን ሁንላቸው፣ አስተምርዋቸው ከእርሳቸውም ጋር ተጓዙ፣ ይህንን ያደረጋችሁ እንደሆኑ እውነተኛ አስተማሪዎች ትሆናላችሁ፣ ለልጆቻችሁ በምታደርጉት ሁሉ ላመስግናችሁ እወዳለሁ፣ እግዚአብሔር ይስጥልኝ፣ እዚህ ለምትገኙ አባቶችና ለሁላቸውም አባቶች መልካም የአባት ቀን ይሁንላችሁ፣ ቅዱስ ዮሴፍ ይባርካችሁ ይጠብቃችሁም፣ አንዳንዶቻችን ደግሞ አባቶቻችንን ያጣን አለን ጌታ የጠራቸው በአደባባዩ ከሚገኙ ብዙዎች አባቶቻቸው የሉም፣ ለሁላቸውም የዓለም አባቶች በሕይወት ያሉም ይሁኑ የሞቱትም ይሁኑ አሁን እንጸልያላቸው አባቱ ያለም ይሁን አባቱ የሞተ አሁን ሁላችን የእያንዳዳችን አባት በማስታወስ ስለአባቶቻችን እንጸሊ፣ ታላቁን አባትችንን ሁላችን አብረን እንለምነው በሰማይ የምትኖር አባታችን እንድገም… በማለት አቡነዘበሰማያትን በኅብረት በመድገም ትምህርታቸውን ደምድመዋል፣
ይህ በእንዲህ ሳለ ቅዱስነታቸው ስለክርስትያናዊ ፍቅር ትዊተር በተሰኘው መገናኛ ብዙኃን “የክርስትያን ፍቅር መስፈርያ የለውም፣ የደጉ ሳምራዊ ትምህርት ይህ ነው፣ የኢየሱስ ትምህርትም ይህ ነው” ሲሉ አጭር መልእክት ጽፈዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.