2014-03-19 16:39:03

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ፦ ዓቢይ ጾም እንደ ፈሪሳውያን ቅዱስ ተመስሎ ለመታየት ሳይሆን ሕይወት ለመለወጥ


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. መጋቢት 18 ቀን 2014 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እንደ ተለመደው ጧት በአገረ ቫቲካን ቅድስት ማርታ ሕንፃ በሚገኘው ቤተ ጸሎት መሥዋዕተ ቅዳሴ አሳርገው የዕለቱ ምንባብ ተንተርሰው በለገሱት ስልጣናዊ አስተንትኖ፦ “ዓቢይ ጾም ወደ ጌታ ለመቅረብ ሕይወትን አስተካክሎና ለውጦ ለመገኘት የሚያግዝ ቅዱስ ተግባር ነው። ሕይወትን በገዛ እራስ ብርታት መለወጥ እንደማይቻል ግንዛቤው እንደሌላቸው ፈሪሳውያን አስመሳይ ቅድስና ለመኖርና ቅዱስ ተመስሎ ለመታየት የሚያግዝ ተግባር አይደለም፣ ጻዲቅ የሚለን ብፅዓን ብሎ የሚፈርደን አለና” ብለው ከነቢይ ኢሳያስ የተወሰደውን አንደኛውን ምንባብ ጠቅሰው፣ እንድንለወጥ ጌታ ይጠራናል፣ ዓቢይ ጾም ወደ ኢየሱስ በበለጠ ለመቅረብ የሚያግዘን ቅዱስ አጋጣሚ ነው፣ ሰዶምና ጎመራ ይለወጡ ዘንድ እግዚአብሔር የለወጥ ጥሪ ያቀርባል፣ ይኽ ቃል ሁላችን እንለወጥ ዘንድ የሚያሳስብ የሚጋብዝ እኛነታችንን መንፈሳችንን እንመለከት ዘንድ የሚጠራ ቃል መሆኑ አብራርተው፣ እግዚአብሔር ቅርቦቹ እንድንሆን ይሻል፣ በምህረቱ ይጠባበቀናል፣ ሆኖም ግን፦ ፈሪሳውያን እንደሚያደርጉት አንዳናደርግ ያስጠነቅቀናል፣ ፈረሳያውን መንፈሳውያን ደጋ ደጎች ተመስለው ለመታየት ውጫዊ ማስተካከልን ይመርጣሉ፣ በአደባባይ ይጸልያሉ አንገታቸው ቀና በማድረግ ሰማየ ሰማያትን ይመለከታሉ፣ ለመታየት፣ ከሌሎች በላይ ጻዲቅና ቅን እንደ ሆኑም ይሰማቸዋል፣ አዎ ከኛ መካከልም ብዙዎች እኔ አጥባቂ ካቶሊክ ነኝ እጎቴ ለቤተ ክርስቲያን በጎ አድራጊና ደጋፊም ነው። ብዙ ብፁዓን ጳጳሳት ብፁዓን ካርዲናሎችን አውቃለሁ፣ ከሁሉም የበለጡ እንደ ሆኑም የሚሰማቸው አሉ፣ ይህ ደግሞ ፍሪሳዊነት ይባላል፣ ጌታ ይላል ‘ማንም በገዛ እራሱ ጻዲቅና ቅዱስ አይሆንም፣ ስለዚህ ጻዲቅና ቅዱስ ብሎ የሚገልጥ ፍራጁ አለ። እርሱን ብቸኛው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው” እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
የተበጃጁ፣ ውጫው መበጃጀት የተካኑ ክርስቲያን ሆኖ ላለ መገኘት አስመሳዮች ፈሪሳውያን አለ መሆናችን ማረጋገጫውና ለጌታ ቅርብ መሆናችን መመስክር ማለት ምን ማለት ነው? በመልካሙ መንገድ እየተጓዝን ለመሆናችን ማረጋገጫው ምን ይሆን? የሚለው ጥያቄ ያቀረቡት ቅዱስ አባታችን አክለው፦ “ለተጨቆኑት፣ ለወላጅ አልባ ሕፃናት ለጋለሞታ ጠበቃ መሆን፣ ስለ ባለ እንጀራ ስለ ታመመው፣ ስለ ድኻው በመሃይምነት ለታወረው ቅርብ መሆን፣ ይህ በመልካሙ መግንድ እየተጓዝን ለመሆናች የሚያረጋገጥ የማእዝን ድንጋይ ነው፣ አስመሳዮች ፈሪሳውያን በገዛ እራሳቸው ከልክ በላይ ምሉእ ነኝ ባዮች በመሆናቸ በገዛ እራሱ የተሞላ እኔነት ለሌላው ጊዜ ቦታ የለውም፣ ለሌሎችን ለማየት የታወረ፣ አንድ ሰው በጉዞው ለጌታ ቅርብ ሲሆን፣ የጌታ ብርሃን ይቀበላል ይኽ ብርሃን ሁሉን እንዲያይ ያግዘዋል፣ አዎ ይኽ ደግሞ የመለወጥ ምልክት ነው” እንዳሉ የገለጠው የቅዱስ መንበር መግለጫ አያይዞ፦ “ዓቢይ ፆም ሕይወታችንን ለማስተካከል ለመለወጥ ወደ ጌታ ለመቅረብ የሚደግፈን ሁነት ነው። ከጌታ የራቅን ለመሆናችን ምልክቱ ፈሪሳዊነት አስመሳይነት ነው። አስመሳይ ጌታ አያስፈልገኝም የሚል ነው። በተጋድሎ ለጌታ ቅርብ መሆናችን ምስክር ማረኝ በማለት የምናቀርበው የምህረት ልመና ነው። አስመሳይ የገዛ እራሱ አዳኝ ነው። የሚያድን ጌታ አያስፈልገውም፣ ለጌታ ቅርብ መሆናችን ምህረቱን የመጠየቅና በድኽነት ጫንቃ ሥር ለሚገኙት ቅርብ መሆናችን ነው” ብለው በመጨረሻ ጌታ ብርሃኑና ብርታቱን ይስጠን ብርሃኑ በእኛ ውስጥ የሚከወነውን በጥልቀት ለመመልከት፣ ብርታቱ ለመለወጥ ወደ እርሱ ቅርብ ለመሆን፣ አዎ ለጌታ ቅርብ ሆኖ መገኘት እንዴት ደስ የሚያሰኝ ውብ ሕይወት ነው” በማለት ያሰሙት ሥልጣናዊ አስተንትኖ እንዳጠቃለሉ አመለከተ።








All the contents on this site are copyrighted ©.