2014-03-14 16:26:42

አንደኛ ዓመት ርእሰ ሊቃነ ጵጵስና ፍራንሲስ ፡


ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ለመንበረ ሐዋርያ ከተሰየሙ እነሆ ትናንትና አንድ ዓመት ሞልቷል ። ፓፓ ፍራንሲ ባለፈው ዓመት 2013 ወርሀ መጋቢት 13 ቀን እኤአ በብጹዓን ካርዲኖሎች መንበረ ሐዋርያ ቅዱስ ጰጥሮስ እንዲመሩ መሰየማቸው የሚታወስ ነው ለመንበረ ሐዋርያ ቅዱስ ጰጥሮስ ከመሰየማቸው በፊት በአርጀንቲና የቡኤኖስ አይረስ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ኾርኸ ማርዮ በርጎልዮ ይጠሩ መኖራቸው ይታወቃል ።ይሁን እና ፓፓ ፍራንሲስ የቅድስት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን 265ኛ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት መሆናቸው የቤተ ክርስትያኒቱ ታሪክ ዘግበዋል።ፓፓ ፍራንሲስ የቀድሞ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት የነበሩ 16ኛ በገዛ ፈቃዳቸው እና ፍላጎታቸው ከመንበረ ሐዋርያ ቅዱስ ጰጥሮስ እንደተገለሉ እሳቸው እንዲተኩ መሰየማቸው ይታወቃል ። ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ከላቲን አመሪካ ክፍለ ዓለም የመጀመርያ የኢየሱሳውያን ማሕበር የቅዱስ ፍራንቸስኮ ስም የመረጡ የመጀመርያ እንደሆኑ የሚታወስ ነው ። ፓፓ ፍራንሲስ ለመንበረ ሐዋርያ ቅድስ ጰጥሮስ እንደተሰየሙ ቫቲካን ውስጥ በሚገኘው ሲስቲና ቤተ ጸሎት እንደ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት የመጀመርያ ስርዓተ ቅዳሴ እንዳሳረጉ ቤተ ክርስትያንን ለሁሉም ክፍት ድሃ እና ለድሆች የቆመች ቤተ ክርስትያን እንደሚፈልጉ ማስታወቃቸው ፡ ከተመረጡ ከሶውስት ቀናት በኃላ ዓለም አቀፍ ጋዜጠኞች በጳውሎስ ስድስተኛ አዳራሽ ተቀብለው ባነጋገሩብት ግዜ Conclave ማለት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ለመምረጥ የሚቀመጠው የካርዲናሎች ጉባኤው እሳቸው እንደመረጠ ጥሩ ትውውቅ ካላቸው በብራዚል የቀድሞ የሳኦ ፓውሎ ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ ካርዲናል ሁመስ አጠገባቸው እንደነበሩ እና በል ተመርጠሀል እና ድሆችን አትርሳ እንዳልዋቸው እና በቀጥታ የአሲሲ የድሆች እና የሰላም አባት ቅዱስ ፍራንቸስኮ ትዝ እንዳላቸው እና ፍራንቸስኮ እንዲጠሩ መውሰናቸው ፓፓ ፍራንሲስ ለጋዜጠኞቹ ገልጠው ነበር ።አያያዘው ድሃ ቤተ ክርስትያን ለድሆች እሻለሁ ማለታቸውም አይዘነጋም ።ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ይህን ካሉ በኃላ ለአንድ ሺ አምስት መቶ ዓመታትአርእስተ ሊቃነ ጳጳሳት የኖሩበት ሐዋርያዊ አዳራሽ ይሄማ ሶስት መቶ ሰዎች የሚያኖር አዳራሽ ነው በማለት እንግዶች እና ካርዲናሎች በሚኖሩበት በቅድስት ማርታ ለመኖር መወሰናቸው የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ልዩ አውቶሞቢል ትተው በተራ መኪና እየተንቀሳቀሱ መሆናቸው ለመረዳት ተችለዋል።ይሁን እና ቅድስነታቸው ለመንበረ ሐዋርያ ቅዱስ ጰጥሮስ እንደተሰየሙ ለመጀመርያ ግዜ በቅዱስ ጰጥሮስ አደባባይ ከተሰበሰቡ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ምእመናን እና ሀገር ጐብኝዎች በጋርዮሽ መልአከ እግዚአብሔር ጸሎት በደገሙበት ግዜ እሱ ማለት እግዚአብሔር ምሕረት ከመስጠት አይቆጠብም እኛ ግን አንዳንድ ግዜ ምሕረት ለመጠየቅ እንዳከማለን ይህ መሆን የለበትም እግዚአብሔር መሐሪ እንደሆነ እኛም ምሕረት ለመስጠት መማር አለብን ብለው ነበር ። ፓፓ ፍራንሲስ ለመንበረ ሐዋርያ ቅዱስ ጰጥሮስ እንደተሰየሙ ከአንድ ሳምንት በኃላ በላቲ ሥርዓተ አምልኮ ቀነ ጸሎተ ሐሙስ ካሳል ደል ማሮሞ ወደ ተባለ ወህኒ ቤት ተጉዘው የወጣቶች እግሮች ማጠባቸው እና እስረኞቹን ኢየሱስ ክርስቶስ የሚሰጠንን ተስፋ መሰረቅ የለበትም በማለት የማበረታቻ መልዕት ማስተላለፋቸው የሚታወስ ነው ።ቤተ ክርስትያን ድሆች እና በተለያዩ ምክንያቶች የሚሰቃዩ ክርስትያኖች ወደ ሚኖርበት አከባብ በመጓዝ ቅዱስ ወንጌል ማብሰር ተስፋ መስጠት ዋነኛ ዓላማ መሆኑ ፓፓ ፍራንሲስ በየግዜው የሚያስተላልፉት መልዕክት እንደሆነ ይታወቃል።ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ የኢየሱሳውያን ማሕበር አባል መሆናቸው የሚታወስ ሲሆን የዚሁ ማሕበር መስራች ቅዱስ ኢግናጽዮ ዲ ሎዮላ ጠቅሰው Deus semper maior አስደናቂው እግዚአብሔር ዘወትር ማመስገን መውደድ መከተል ማፍቀር እንደሚገባን ያስገነዝባሉ ።ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ለሐዋርያ ቅዱስ ጰጥሮስ እንደተሰየሙ ከአስር ቀናት በኃላ ከሳቸው በፊት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት የነበሩ እና በገዛ ራሳቸው ፋልጎት እና ፈቃድ መንበረ ሐዋርያ ቅዱስ ጰጥሮስ የለቀቁ በነዲክት 16ኛ ለመጕብኘት ወደ ካስተል ጋንዶልፎ መጓዛቸው እና ክእሳቸው በጋራ መጸለየቻው አይዘነጋም።
በነዲክት 16ኛ የወሰዱት ርምጃ በቤተ ክርስትያን ዘመናዊ ታሪክ የመጀመርያ በመኖሩ በአማንያን መደናበር እንዲከሰት ማድረጉ የሚትጋወስ ነው ። ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በአንድ ዓመት ውስጥ ለቅድስት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ሁነኛ እና ተጨባጭ አዎንታዊ ግፊት የሰጡዋት ሲሆን ቤተ ክርስትያኒቱ የህዝበ ክርስትያን አገልጋይ ቅዱስው ወንጌል አብሳሪ የመንግስት ሰማያት መንገድ አመልካች እና መሪ እንድትሆን አበክረው ሰርተዋል።የቅድስት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ተቋማት ለማሳደስም የተለያዩ ርምጃዎች መወሰዳቸው እና እየወሰዱ እንደሚገኙ ከምእመናን ቀጥተኛ ግንኙነት እንዳላቸው በዚሁ ባለፈው አንድ ዓመት ለማስተዋል ተችለዋል። በተለይ የቤተ ክርስትያን ምህደራ ተሐድሶ በሂደት ላይ እንደሚገኝ የሚታወቅ ሲሆን ገና አስደናቂ ርምጃዎች እንዲወዱ እንደሚጠበቁም ይመለከታል ። ቅድስነታቸው በግብረ ሰዶማውያን ላይ ያላቸውን አስተያየት እንዲሰጡ ተጠይቀው እኔ ማን ሆኜ ነውና በነሱ ላይ የሚፈርደው ማለታቸው ቃል ኪዳን ስላፈረሱም ያላቸውን አስተያየት ሲናገሩ መወገዝ መገለል የለባቸውም አብረናቸው መጓዝ አለብን በማለት ፓፓ ፍራንሲስ መልሰዋል። በዚህም አድናቆት ያተረፉ ሲሆን የዓለም ሀገራት የስደተኞች ሁኔታ በማጤን ሰብአዊ ትብብር እንዳያሳዩ መመጸናቸው የሚታወስ ነው ።ፊታችን ጥቅምት ወር የቤተ ሰብ የጳጳሳት ሲኖዶስ እንዲካሄድ ያቀዱ ሲሆን ቤተ ሰብ የማሕበረ ሰብ ብሎም የሕብረተ ሰብ መሰረት ስለ ሆነ ዓቢይ እንክብካቤ እና ጥንቃቄ የሚያሻው ጉዳይ እናደሆነ በየግዜው የሚያወሱት ግዳይ እንደሆነ አይዘነጋም ።የሕጻናት የደካሞች እና አረጋውያን ጉዳይ በእጅጉ እንደ ሚያሳስባቸው ቤተ ክርስትያን ጨምሮ ማሕበረ ሰቦች ለእነሱ ከፍተኛ ትኩረት እንዲሰጡ ከማሳሰብ እንዳልጠቆጠቡም ይታወቃል።ይህ በዚህ እንዳለ በጣልያን የመወሰኛ ምክር ቤት ፕረሲዳንት ፒየትሮ ግራሶ የፓፓ ፍራንቸስኮ አንድ ዓመት ርእሰ ሊቃነ ጵጵስና ተወዳዳሪ የሌለው አዎንታዊ እና አስደናቂ መሆኑ ያላቸውን አስተያየት ሰጥተዋል ። የሀገሪቱ ማለትም የጣልያን ርእሰ ብሄር ጆርጆ ናፖሊታኖም ተመሳሳይ አስተያየት ሰንዝረዋል።
በመጨረሻም የሞስኮ እና የኩላዊት ሩስያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ፓትርያሪክ ብፁዕ ወቅዱስ ክሪል የፓፓ ፍራንሲስ አንደኛ ዓመት የርእሰ ሊቃነ ጳጳስና ፍራንሲስ ምክንያት የደስታ መልዕክት ማስተላለፋቸው ቫቲካን ላይ የወጣ መግለጫ አስታውቀዋል።.ከርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ጋር የአብያተ ክርስትያናቱ ትብብር ማደጉ የፓትርያሪኩ መልዕክት ማመልከቱ እና በዓለም ዙርያ የክስትያኖች የግብረ ገብነት እሴቶች በጋራ ለማስጠበቅ ትብብሩ እንድቀጥል ከፍተኛ ተስፋ እንዳላቸው ማስገንዘቡ መግለጫው አክሎ ዘግበዋል። ፓፓ ፍርፋንሲስ ለሚሰቃዩ እና ለድሆች ያላቸውን ሐሳቢነት የሚመስገን እንደሆነ የፓትርያሪኩ መልዕክት ማስገንዘቡም መግለጫው አመልክተዋል። እግዚአብሔር ለፓፓ ፍራንሲስ አካላዊ እና መንፈሳዊ ኀይል እንዲሰጣቸው የደስታ እና የሰላም ባለቤት እንድያደርጋቸው የሞስኮ እና ኩላዊት ሩስያ ፓትርያሪክ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያሪክ ክሪል ለቅድስነታቸው እንደተመኙላቸው መግለጫው በማያያዝ ገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.