2014-03-12 16:34:57

አንደኛ ዓመት ርእሰ ሊቃነ ጵጵስና ፍራንሲስ :
የቅድስት መንበር ቃል አቀባይ አስተያየት፡


ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ነገ መጋቢት 13 ቀን 20014 እኤአ ለመንበር ሐዋርያ ቅዱስ ጰጥሮስ ከተሰየሙ እነሆ አንድ ዓመት ሟልተዋል። የቅድስት መንበር ቃል አቀባይ እና የራድዮ ቫቲካን ዳይረክተር አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ የፓፓ ፍራንሲስ አንድ ዓመት ርእሰ ሊቃነ ጵጵስና ትኩረት በመስጠት በራድዮ ቫቲካን በኩል አስተያየት ሰጥተዋል ።በመሠረቱ አንድ ዓመት ርእሰ ሊቃነ ጳጳስና ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በጣም አሪፍ መኖሩ የቅድስት ቃል አቀባይ ጠቅሰው ካቶሊካውያን እና ካቶሊካውያንያልሆኑ በቅድስነታቸው እንደተማረኩ በሚያስተላልፋቸው መልእክቶች መደሰታቸው የተያዙት የቤተ ክርስትያን ተቋሞች እደሳ መደገፋቸው በተጨባጭ የታየ ጉዳይ እንደሆነ ገልጠዋል። ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቤተ ክርስትያን ድሃ እና ለድሆች የቆመች መሆንዋ በተደጋጋሚ በመግለጥ ከዶሆች ጐን መሆንዋ ፓፓ ፍራንሲስ ማስገንዘባቸውም ቃል አቀባዩ አስታውሰዋል ።
ባለፈው ዓመት በተከበረው ጸሎተ ሐሙስ በሥርዓተ ላቲን ማለት ነው ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ እዚህ ሮም ውስጥ ወደሚገኘው እስር ቤት ተጉዘው እስር ቤት ውስጥ የሚገኙ ወጣቶች እግሮች ማጠባቸው ባለፍረው ወርሀ ጥቅምትወደ ደቡባዊ ጣልያን ሲሲሊ ግዛት ወደ ደሴት ላምፐዱሳ ተጉዘው ከምስራቅ አፍሪቃ መካከለኛው ባሕር ሲያቃርጡ ለሕለፈት ስለ ተዳረጉ መጠለያቸው በሕይወት ከተረፉ ጋር መገኛነታቸው የቅድስት መንበር ቃል አቀባይ እና የቫቲካን ራድዮ ዳይረክተር በማስታወስ ለቅድስነታቸው ያላቸውን አድናቆት ገልጠዋል። በማያያዝም ባለፈው ወርሀ ሐምለ እኤኣአ ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን በብራዚል በተከበረበት ግዜ ወደ ሪዮ ደ ጃነሮ በተጓዙበት ግዜ እና ከየላቲን አመሪካ ወጣቶች በተገናኙበት ግዜ ለወጣቶቹ የሰጡት ምክር እና ሞራል የማይረሳ መሆኑ አስታውሰዋል።የቅድስት መንበር ቃል አቀባይ እና የራድዮ ቫቲካን ዳይረክተር አባ ፈድሪኮ ሎምባርዲ ነገ ተዘክሮ የሚውለውን የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ አንደኛ ዓመት ርእሰ ሊቃነ ጵጵስና ምክንያት በማድረግ የሰቱት አስተያየት በማያያዝ በቅርቡ ለንባብ ያበቁት Evangelii Gaudium የቅዱስ ወንጌል ደስታ የተሰየመ ሐዋርያዊ መልዕክት ርእሰ ሊቃነ ጵጵስናቸው ቅዱስ ወንጌልን እንደገና እና በበለጠ መልኩ ለዓለም እንዲዳረስ ያላቸውን እቅድ የሚያስረዳ እንደሆነ ያስርዳል ብለዋል ። ባልፈው ወርሀ የካቲት እንደ ኤውሮጳውያን አቆጣጠር የመሩት የካርዲናሎች ጉብባኤ እና የቅድስት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ሕይወት ያደረጉት ግምገማ ራሱ ዓቢይ ርእስ መሆኑ ቃል አቀባዩ ከሰጡት አስተያየት ለመረዳት ይቻላል ሲሉ አስገንዝበዋል።ፓፓ ፍራንሲስ የህዝበ ክርስትያን እረኞች ለደካሞች ለአረጋውያን ለሕጻናት እና ለቤተ ሰብ ልዩ እንክብካቤ እንዲሰጡ እረኞቹ አከባብያቸው እንዲዳስሱ ዜና ሰናየ ለሁሉ እንድያዳርሱ በመደጋገም እያሳሰቡ መሆናቸው አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ የቅድስት መንበር ቃል አቀባይ እና የራድዮ ቫቲካን ዳይረክተር አመልክተዋል። በመቀጠልም በሳምንት አንድ ግዜ ሮቡዕ ለምእመናን እና ለሀገር ጐብኝዎች የሚሰጡት ትምህርተ ክርስቶስ ስኬታማ መሆኑ ከህዝበ ክርስትያን ጋር በቀጥታ እየተገናኙ መሆናቸው ገልጠዋል።ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ህዝበ እግዚአብሔርን በበለጠ እና በተጨባች አኳኀን ወደ እግዚአብሔር ለማቅረብ እሱ ማለት እግዚአብሔር ህያው መሆኑ በአጠቃላይ የሚንቀሳቀስ እና የማይንቀሳቀስ ዓለምን የፈጠረ እግዚአብሔር ዘወትር ከፍጥረቶች ጐን እንደሚገኝ ምድራዊ ሕይወት ሐላፊ መሆኑ ህዝበ ክርስትያን ለሰማያዊ ሕይወት መዘጋጀት እንደሚጠበቅበት አውቆ እንዲረዳ ይፈልጋሉ ብለው ያሉ ቃል አቀባዩ በዓለም ዙርያ ሰላም ፍትሕ መተባበር መረዳዳት እንዲኖር ይፈልጋሉ ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.