2014-03-12 16:14:43

ቶጎ፦ ሕዝባዊና አገራዊ እርቅ ይበርታ


RealAudioMP3 በቶጎ የክልሎች ሕዝባዊ ምርጫ የመንግሥት መዋቅሮች የተገባ ሕዳሴ ማረጋገጥ በቶጎ የእውነት የፍትህና የሰላም ድርገት ያቀረበው አደራ ገቢራዊ ከሆነ የሰላሙ ጉዳይ ብሎም ለሕግ ሉአላዊነት ዋስትናና በአገሪቱ ለለልማት እቀድ አቢይ አስተዋጽኦ ያለው እንደሚሆን የቶጎ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት በቅርቡ በሎሜ ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ ፍጻሜ ባወጣው መግለጫ እንዳመለከተ ሲገለጥ፣ ብፁዓን ጳጳሳት እ.ኤ.አ. ባለፈው ሐምሌ ተካሂዶ የነበረው ምርጫ ተከትሎ የተዛመተው ፖለቲካዊ ውጥረት ላይ በማተኮር፣ ውጥረቱ ያስከተለው ችግር መፍታት ለአገሪቱ ሰላም መረጋገጥ መሠረት እንደሚሆን ያመለክታሉ።
የመንግሥት መዋቅሮች የፖለቲካ ሰልፎች እንዲሁም ሕዝብ በጽናት በአገሪቱ የተጀመረው የእርቅ ሂደት በማበረታታት ለሰላም እንዲቆሙ የቶጎ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ በኖኢት ኮምላን መሳን አሎዎኑ የተካሄደው ስብስባ በንግግር ሲከፍቱ እንዳሰመሩበትና የአገሪቱ የዘርአ ክህነት ተማሪዎች የሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ አስፈጻሚ አባላት የተሟላ ሕንጸት ማግኘት ያለው አንገብጋቢነት ብሎም የአገሪቱ የፖለቲካ አካላትና በተለያየ አቢይ ኃላፊነት የተቀመጡ ሁሉ የታነጹ የአገሪቱ መጪው ሕይወት ብሩህ በማድረጉ ረገድ አስተዋጽኦ ለመስጠት እንዲችሉ የተሟላ ሕንጸት ያስፈልጋቸዋል እንዳሉ ከቶጎ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የተላለፈው መግለጫ ይጠቁማል።
በሌላው ረገድ የተካሄደው የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 2014 ዓ.ም. ቅድስት ቤት ክርስቲያን ቅድስና ስለ ምታውጅላቸው ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ 23ኛ ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ በተመለከተ ርእስ ሥር ውይይት አካሂዶ የዘርአ ክህነት ተማሪዎች የቅድመ ዝግጅት ሕንጸት በአዲስ መንፈስ ማደራጀት በአገሪቱ ቅድሳት ስፍራዎች የሚካሄደው መንፈሳዊ ንግደት በተሟላ አሰራር ማደራጀት እንዲሁም የቶጎ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት በአገሪቱ የቤተ ክርስቲያናዊ ፍርድ ቤት ህዳሴ ርእስ ሥር ውይይት ተካሂዶ በመጨረሻም ለሚቀጥሉት ሦስት ዓመት የሚከተለው የሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ አቅድ መወጠናቸው የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት መግለጫ ይጠቁማል።








All the contents on this site are copyrighted ©.