2014-03-11 17:19:05

ከሰይጣን ጋር ከመደራደር ይልቅ በቃለ እግዚአብሔር እናርቀው፣


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍርናቸስኮስ ትናንትና እኩለ ቀን እንደተለመደው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ከም እመናንና ነጋድያን የመል አከ እግዚአብሔር ጸሎት ከማሳራጋቸው በፊት የዕለቱን ቃለ ወንጌል በመመርኰዝና ያለነው ጊዜ ጾመ ሁዳዴ በመሆኑ ለለውጥና ለንስሓ በምናደርገው ጉዞ ምርጥ ጊዜ በመሆኑ ሁላችን ሰይጣንን ደጋግመን መካድ እንዳለብንና እርሱ የሚያቀርብልንን ፈተናና ከተግባሩ በቃለ እግዚአብሔር ራሳችንን መከላከል አለብን ሲሉ አሳስበዋል፣
በላቲኑ ሥር ዓተ አምልኮ ትናንትና የተነበበው ቃለ ወንጌል የኢየሱስ ጾምና ፈተና የሚመለከት ሲሆን ቅዱስነታቸው በኢየሱስና በሰይጣን መካከል ስለነበረው ትግል በማትኰር ጌታ ኢየሱስ በዮርዳኖስ በዮውሐንስ ከተጠመቀና መንፈስ ቅዱስ ከወረደው በኋላ በመንፈስ ተገፍቶ ከዲያብሎስ ጋር ፊት ለፊት ለመጋፈጥ ምድራዊ የደህንነት ተለእኮውን ከመጀመሩ በፊት በረሃ ገባ፣ ፈታኙ ዲያብሎስ ኢየሱስ የመስቀል መንገድን ትቶ ቀለል ያለ የማሸንፍ የሥልጣንና የችሎታ መንገድ እንዲከተል የውሸት ተስፋዎች እየሰጠ ይፈትነዋል፣
“ምጣኔ ሃብታዊ የተደላደለ ኑሮ ድንጋዮችን ወደ ዳቦ በመለወጥ ችሎታ የተመለከተ እንዲሁም በሁለተኛው ፈተና የተመለከተ ከቤተመቅደሱ ጫፍ መወርወርና በእግዚአብሔር መላእክት እጅ በመዳን የእግዚአብሔር ተአምር በማሳየት ትእይት የቆመው ፈተና በመጨርሻም ለሰይጣን በመስገድ የሚገኛ የዓለም ሙሉ ሥልጣንና ግዛት ሶስቱ የፈተና ክፍሎች ናቸው፣ እኛም ጥሩ አድርገን እናውቀዋለን፣ ኢየሱስ ግን ሶስቱንም ፈተናዎች ይቃወማቸዋል ከአባቱ ጋር ካለው የማይነቃነቅ አንድነት ለመከተል ያለውን ጽኑ ፍላጎት አለምንም ጥርጣሬና ከኃጢአትን ከዓለም አስተሳሰብ ምንም ዓይነት ድርድር እንደማያደርግ ቍርጡን ይነግረዋል፣
“ኢየሱስ እንዴት አድርጎ እንደሚመልስ አስተውሉ፣ እርሱ ሔዋን በኤደን ገነት እንዳደረገችው ከሰይጣን ጋር አይደራደርም፣ ከሰይጣን ጋር መደራደር እንደሌለብን እጅጉን ያውቃል ምክንያቱም አታላይ ነውና፣ ለዚህም ኢየሱስ ሔዋን እዳንደረገችው ከሰይጣን ጋር ከመደራደር ይልቅ በቃለ እግዚአብሔር ለመከላከል ይመርጣል በዚህም በቃለ እግዚአብሔር ኃይል ይዋገዋል፣ በፈተና ጊዜ ፈተናዎች በሚያጋጥሙን ጊዜ ይህንን እናስታውስ! ከሰይጣን ጋር መደራደር አያዋጣንም ነገር ግን ዘወትር በቃለ እግዚአብሔር ራሳችንን እንከላከል፣ ይህም ያድነናል፣ ሰይጣን በመጀመርያ ላቀረበለት ፈተና ኢየሱስ የሰው ልጅ በዳቦ ብቻ እንደማይኖር ነገር ግን ከእግዚአብሔር በሚወጣው እያንዳንዱ ቃል ነው የሚኖረው፣
“ይህም ኃይል ይሰጠናል፤ የሰው ልጅን እንደማንኛው የጥቅም ዕቃ ከሚመለከተው ዓለማዊ አስተሳሰብ ለመታገልም ይደግፈናል፣ ይህ ዓለማዊ አስተሳሰብ የእውነት የመልካምና ደግ የሆነው የእግዚአብሔርና የፍቅሩ ረኃብን እንድናጠፋ ያደርገናል፣ እንዲሁም ለሁለተኛው ፈተና እግዚአብሔር አምላክህን በፈተና አታግባ የሚል ጽሑፍ አለ ብሎ ይመልሳል፣
“የዚህ ምክንያትም የእምነት ጐዳና በጨለማና መጠራጠር በመላበት ሁኔታዎችም ስለሚታከሉበት ቃለ እግዚአብሔር በትዕግሥትና ብጽናት እንዲጠባበቅ ይረደዋል፣ በመጨረሻም እግዚአብሔር አምላክህን ብቻ ታመልካለህ ለእርሱ ብቻ ትሰግዳለህ የሚል ጽሑፍ አለ ብሎ ሲመልስ ደግሞ ያሉንን ጣዖቶች ሁሉ መደምሰስ እንዳለብን ያመለክታል፣
“ከጣዖቶች ከማይረቡ የሥጋዊ ኃሳቦች ተለይጠን መሠረታዊ ከሆነው ከአምላካችን ጋር ሕይወታችንን ማነጽ እንዳለብን ያስተምራል፣ ስለዚህ በጥምቀጥ የገባነውን ቃል ማሳደስ አለብን፣
“በእግዚአብሔር ጐዳናዎች ለመራመድና በመንፈስ ቅዱስ ደስታ ወደ በዓለ ትንሣኤ እንድንደርስ ሰይጣንን ተግባሮቹንና ፈተናዎችን እንካድ፣ ሲሉ ካሳሰቡ በኋላ የመል አከ እግዚአብሔር ጸሎት አሳርገዋል፣
ከመል አከ እግዚአብሔር ጸሎት በኋላ በተለያዩ ቋንቋዎች ባመስገኑበትና ልዩ ልዩ አደራዎች ባቀረቡበት ወቅት በዘመነ ጾም መደረግ ያለበትን የምግባረ ሠናይ መተባበር እንዲሁ ሲሉ አሳስበዋል፣
“በዚሁ የጾመ ሁዳዴ ጊዜ ዓለም አቀፉ የምግባረ ሠናይ ካሪታስ ኢንተርናስዮናሊስ በዓለም ውስጥ ረኃብን ለማጥፋት የሚያቀርበውን ጥሪ እናስታውስ፣ ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸውና በቅድስት መንበር አስተዳደር የሚተባበርዋቸው በኩርያ ሮማና የሚታወቀው የካርዲናላት ጳጳሳትና ካህናት ቡድን የዘመነ ጾም ሱባኤ ለማድረግ ስለሚሄዱ በጸሎት እንድናስታውሳቸው ጠይቀዋል፣
“እኔንና ተባባሪዎቼ የኩርያ ሮማና አባላት ዛሬ ማታ ጀምረን ለአንድ ሳምንት በምናካሄደው ሱባኤ በጸሎት እንድታስታውሱን አደራ፣ እግዚአብሔር ይስጥልን ሲሉ ጉባኤ አስተምህሮውን ደምድመዋል፣
ይህ በእንዲህ ሳለ አት ፖንተፊክስ በተሰኘው የትዊተር ፖስታቸው “የአዳዲስ የክርስትያን ሙሽሮች ትግል በአንድነት መሆን ለሁል ግዜ እርስ በእርስ መፈቃቀርን ማወቅና ይህ ፍቅር እንዲዳብር ዕድል መፍጥር መሆን አለበት” ሲሉ አጭር መልእክት ጽፈዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.