2014-03-05 18:31:41

የር.ሊ.ጳ ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ፤


ውድ ወንድሞችና እኅቶች! መልካም ቀን ይሁንላችሁ! ዛሬ የጾመ ሁዳዴ ጉዞ የምንጀምርበት ለሶሙነ ሕማማት የሚያደርሰን በጌታ ሕማማትና ሞትና የደህንነታችን አንኳር ወደሆነው ወደ ጌታ ትንሣኤ የሚያደርሰን ጉዞ የሚጀምርበት የአመድ ሮብ እናስታውሳለን፣ ጾመ ሁዳዴ ለዚሁ ታላቅ የምሥራች ስለሚያደርሰን ጾሙ ታላቅና የግድ ነው ለዚህም በእያንዳንዳችን የልብ ለውጥ የንስሓ ጊዜ ሊሆነን ይችላል፣ እኛ ሁላችን የመሸሻል እና ወደ ተሻለ መንፈሳዊ ሕይወት መለወጥ እጅግ ያስፈልገናል፣ ጾመ ሁዳዴ ለዚህ ይረደናል በዚህም ዕለት ዕለት ከምንኖረው ልማድ ወጣ ብለን በዚሁ በጾም ጊዜ ማድረግ ያለብንን እናታችን ቤተክርስትያን ሁለት ነገሮች ታሳስበናለች፣ እነዚህም የክርስቶስ የደህንነት ሥራን ሕያው በሆነ መንገድ ማስተንተንና በምሥጢረ ጥምቀት የገባነውን ቃል በልዩ መንፈስ እንድንኖር ትጠራናለች፣ ጌታ ለደህንነታችን የሰራውን አስደናቂ የምሕረት ሥራን ማወቅና ማስተንተን ልባችንና አእምሮአችንን ወደ እግዚአብሔር እንዲያዘነብል ያደርጋል፣ እግዚአብሔር ለሕዝቡ ያደረገውን አንድያ ልጁን በመስጠት ዓለምን ያደናበትንና ለሕዝቡና ለመላው ሕዝብ ያደረገውንና ገናም እያደረገ ያለውን የምሕረት ሥራ እጅግ የሚያደንቅ ነው፣ ይህንን እግዚአብሔር ለኛ ያሳየውን ፍቅር በምናስተነትንበት ጊዜ ወደ እርሱ በበለጠ ለመቅረብ ፍላጎት ይኖረናል፣ ለውጥና ንስሓም ይህ ነው፣
በጥምቀት የገባነውን ቃል በሚገባ መኖር የሚለውን ሁለተኛ ነጥብን የተመለከትን እንደሆነ ደግሞ በጐደናዎችና በአገሮቻችን ከምናያቸውና ከምንሰማቸው የወርደትና የድህነት ኑሮን አለመለማመድን ያመለክታል፣ አንዳንድ መጥፎ ልማዶችን ምንም ሳትቃወም በለዘብተኛነት የመቀበል ፈተና አለ! የባሰውኑ ደግሞ ዓለማችንን እያማቀቀ ባለው ድህነትና ችግር ለሚሰቃዩት ወገኖች ማየት መርዳትንና መተባበርን ችላ የማለት ፈተናም አለ፣ በዜና የምንሰማቸውንና የምናያቸውን የዓመጽ የስቃይና የችግር ዜናዎችን ለመደናቸው ምንም እንዳልሆነ ደንታ ቢሶች ሆነን ስንመለከት የባሰውኑ ደግሞ በየጐዳኖዎቹ በረሃብና እርዛት እየተሰቃዩ ያሉ ወንድሞቻችንና እኅቶቻችን አይተን እንዳላየን ሆነን ማለፍም አለ፣ ራሱን ሁሉን እንደሚችል አድርጎ በመገመት ለልጆቻቸው ጸሎት ማስተማርን ያቋረጡ ከሁሉ የባሰ ደግሞ ት እምርተ መስቀል እንኳ አለማድረገን እንደልማድ ባደረጉት ቤተሰቦች ተከበን ነው ያለነው፣ አንድ የማቀርብላችሁ ጥያቄ አለኝ! ልጆቻችሁ ሕጻናቶቻችሁ በሰመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ብለው ትእምርተ መስቀል ማድረግን ያውቃሉን? እሰቡበት፣ የልጅ ልጆቻችሁስ ት እምርተ መስቀል ማድረግ ያውቃሉን? አስተማርችኋል ወይ? ይህንን ነገር በልባችሁ እሰቡበት መልሱም በልባችሁ ይሁን፣ በሰማያት የምትኖር አባታችንን መድገም ይችላሉን? ለእመቤታችን ድንግል ማርያም በሰላሙ ቅዱስ ገብርኤል በመድገም ይማጠንዋታልን? እሰበቡበት መልስም ስጡለት፣ ይህ እንደ ክርስትያን ሆነ የመኖር ፈተና እየተጋፈጠን ነው ልባችንን እንደ ፅጸ ፋርስ እያደነዘዘው ነው፣
ዘመነ ጾም እንደ የለውጥ ጊዜ ነው የሚሰጠን፣ በእግዚአብሔር አሳቢነትም የሕይወታችን ጉዞ ለመለወጥና ሁሌ ለሚጋፈጠን መጥፎ ነገር ለመወዋጋት የሚሰጠን ጊዜ ነው፣ ዘመነ ጾመ አርባ እንደ የንስሓና የለውጥ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር በመቅረብና ቃለ ወንጌሉን በትሕትና በመታዘዝ የየግላችን እና የማኅበሮቻችን መታደስ የምናዘወትርበት ቢዜ ነው፣ በዚህም ለወንድሞቻችንና ለፍላጐታቸው በአዲስ ዓይን እንድንመለከት ዕድል የሚሰጠን ጊዜ ነው፣ ስለዚህ ዘመነ ጾም ወደ እግዚአብሔርና ወንድሞቻችን ፍቅር ለመመለስ የሚሰጠን ዕድል ነው፣ ይህ ፍቅር “ድሆችን በእርሱ ፍቅር ሃብታሞች እንዲያደርግ ራሱን ድኃ አድረገ” (2ቆሮ 8፤9) የሚለውን በነጻና በጌታ ምሕረት የተሰጠንን ፍቅር የሚያሳስብ ነው፣ የኢየሱስ ክርስቶስን እምነት ሕማማት መስቀልና ትንሣኤን በማስተንተን መጠን የሌለው የጌታ የደህንነት ስጦታን ለመረዳት እንችላለን፣
በመስቀሉ ያሳየንን ፍቅር ምስጋና ለማቅረብ እውነትኛ እምነት ልባችንን ለንስሓና ለወንድሞቻችን መክፈት ያስፈልጋል፣ ዘመነ ጾምን በሚገባ ለመኖር እነኚህ ነገሮች መሠረታውያን ናቸው፣ በዚህ ጉዞ የእመቤታችን ድንግል ማርያም ታማኝ መከላከልና እርዳታ መጠየቅ ያስፈልጋል፣ ምክንያቱም እርሷ የመጀመርያ የክርስቶስ አማኝ ስለሆነች በዚሁ ብርቱ የጸሎትና የንስሓ ጊዜ እንድትሸኘን በሚገባ ነጽተን እና በመንፈስ ታድሰን ታላቁን የልጅዋ ምሥጢረ ፋሲካ በዓል ለማክበር ታስችለን ዘንድ እንማጠናት፣








All the contents on this site are copyrighted ©.