2014-03-03 19:31:51

የር.ሊ.ጳ የመልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ፤


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ትናንትና እኩለ ቀን ላይ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ከማሳረጋቸው በፊት የዕለቱን ቃለ ወንጌል በመመርኰዝና ባሁኑ ግዜ በኡክራይናና በሩስያን መካከል ያለውን ችግር አስመልክተው “ኡክራይና የውይይት መንገድ መምረጥ እንዳለባትና ሃብት ለሁሉ ካልተከፋፈለ ፍትሕ እንደሚጐድል” አመልክተዋል፣ በተለይ ደግሞ ክሪመያ ክፍለ ሃገር እየታየ ያለው ወደ ውጉያ የሚያመራ ሁኔታ ቅዱስነታቸውን እጅግ እንዳሳሰባቸውን በኡክራይናና በራሻ መካከል የሰላም ውይይት እንዲካሄድ የሚከተለውን ጥሪ አቅርበዋል፣
“በአገሪቱ ውስጥ እየታየ ያለውን አለመግባባት ጉዳዩ የሚመለከታቸው ሁላቸው በመረዳዳት እንዲፈትዋቸውና ለአገሪቱ መጻኢ አብረው እንዲሠሩ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ደግሞ ለስምምነትና ለውይይት የሚደረገውን ጥረት ሁሉ እንዲደግፉ እማጠናለሁ” ብለዋል፣
በላቲኑ ሥር ዓተ አምልኮ ትናንትና የተነበበው ውንጌል ምን እንበላለን ምንስ እንጠጣለን ምንስ እንለብሳለን ብሎ በመጨነቅ ብዙ ሃብት የሚያካምቹ ከሰማይ ወፎችን ከበረሃ አበባዎች መማር እንዳለባቸው የሚያመልክት ክፍል ሲሆን ቅዱስነታቸውም በዚሁ መሠረት ወንጌሉ እንደሚያረጋግጠው እግዚአብሔር የሁላችን አባት በመሆነ ስለሁሉም ነገር እንደሚያስብልንና ሁሉን እንደሚያዘጋጅልን አምነን መጀመርያ መንግስቱንና ጽድቁን ማለት ፍትሕን ማንገስ እንዳለብን አመልክተዋል፣ የእግዚአብሔር መለኮታዊ አሳቢነት በእምነታችን አንቀጾች ከሚገኙ እውነት እጅግ የሚያጽናና ክፍል መሆኑን የገለጡ ቅድስነታቸው ባለነው ዘመን ብዙ ሰዎች ሰብ አዊ ክብረታቸውንና መብታቸውን በሚፈታተን ሁኔታ እየሩ መሆናቸውን እንዲህ ሲሉ ገልጠዋል፣
“እነኚህ ሁኔታዎች ከማንኛው ግዜ በላይ እውን ናቸው! ለሁለት ጌቶች ማለት ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ ልናገነግል እንደማንችል እናስታውስ፣ እያንዳንዱ ለገዛ ራሱ ብቻ ሃብት እስከአከማች ድረስ ፍትሕ ሊኖር አይችልም፣ ይህንን እናስታውስ! እያንዳንዱ ለገዛ ራሱ ብቻ ሃብት በማከማቸት ከተገኘ ፍትርሕ ሊኖር አይችልም፣ ነገር ግን በዚህ ምትክ በእግዚአብሔር አሳቢነት ተማምነን መጀመርያ የእርሱን መንግሥት አብረን ከፈለገንና ያለንን ሁሉ የተካፈልን እንደሆነ የዕለቱን እንጀራ የሚያጣ ሊገኝ ከቶ አይችልም፣ ራስ ወዳድነት ምንኛ ያህል አደገኛ መሆኑን ተመልከቱ፣ ሃብትን ለማከማቸት ብቻ የሚያስብ ልብ በእግዚአብሔር ፊት ባዶ ነው፣ ስለእግዚአብሔር ምንም ደንታም የለውም ቦታም የለውም፣ ለዚህም ነው ኢየሱስ ብዙ ጊዜ ለሃብታሞች ሲወቅሳቸው የምናገኘው ምክንያቱም ዋስትናቸውን በዚህ ዓለም ሃብትና ንብረት ለማኖር ሲሉ ስለ እግዚአብሔር ስለጓደኛ ሊያስቡ አይችሉምና፣
“ስለሃብታ ብቻ በማሰብ በተገዛ ልብ ለእምነት ብዙ ቦታ አይገኝም፣ ልቡ በአጠቃላይ በሃብት ስለተያዘ ለእምነት የሚሆን ቦታ አይገኝበትም፣ ይህን ከማድረግ ይልቅ በእግዚአብሔር አሳቢነት ተማምኖ የሚጠባበቅ ከሆነ ግን በልቡ መጀመርያ ቦታ የሚያገኘው የእግዚአብሔር ፍቅር ነው፣ እንዲህ በማድረግም ይህ ፍቅር ወደ ሃብት ሊመራው ሃብቱንም ከጓደኞቹ ጋር እንዲካፈል እና ለእርዳታና ለብልጽግና ፕሮጀክቶች ያገልግላል፣ በዘመናችን እና በቤተ ክርትያን ታሪክ ይህንን የመሳሰሉ የፍቅር ሥራዎች ብዙ ናቸው፣ እንዲህ ባለ መንገድ ለሌሎች በምንሰጠው አገልግሎት እና ያለንን ከሌሎች ጋር በመካፈል የእግዚአብሔር አሳቢነት ለኛም ለሌሎችም ይተላለፋል፣ ሲሉ የፍቅር ሥራ ምንኛ ያህል እንደሚረዳ ካስተማሩ በኋላ እንዲህ ሲሉ በአደባባዩ ለተገኙ ሁሉን ያሳሰበ ምሳሌ አቅርበዋል፣
“ይህንን ታውቃላችሁን! መግነዝ ምንም ነገር ይዘን የምንሄድበት ኪስ የለውም! ስለዚህ ጊዜ ሳለን ያለንን ብንካፈል ጥሩ ነው ምክንያቱም ወደ ሰማይ ይዘነው የምንጓዘው ያ ከሌሎች ጋር ያካፈነውን ነው፣
ቅዱስነታቸው አያይዘው ያተኰሩበት ቃለ ወንጌል “ሕይወት ከምግብ ሰውነትም ከልብስ ይበልጣል” የሚለው ሓረግ የሚያስተምረን ዕሴቶችን በቅደም ተከተል ማስቀመጥ እንዳለብን እንደሚያሳስበን እንዲህ ሲሉ ገልጠዋል፣
“ለማንም የዕለት እንጀራ ውኃ ልብስ ቤት ስራ እና ጤና እንዳይጉድል ሁላችን በሰማያት የሚኖር አባታችን ልጆች መሆናችንና ወንድማሞችና እኅትማሞች መሆናችን ማስታወስ አለብን፣ በዘንድሮም ዓለም አቀፍ የሰላም ቀን ያስተላለፍኩት መል እክትም ይህ ነበር ወደ ሰላም የሚወስደን ጐዳና የወንድማማች አብሮ የመጓዝና ያለህን በኅብረት መካፈል መሆን ጠቅሼ ነበር፣ ሲሉ ካስተማሩና ጸሎተ መል አከ እግዚአብሔር ካሳረጉ በኋላ በተለያዩ ቋንቋዎች ሰላምታ ባቀረቡበት ወቅት በዚህ ሳምንት የምንጀምረውን ጾመ አርባ የለውጥ ጉዞ እንዲሆን ከጠላት ጋር በምንደርገው ትግል የጸሎት የጾምና የምሕረት ተግባር መሣርያዎችን በደንም እንድንጠቅም አደራ ብለዋል፣
“የሰው ልጅ የፍትሕ የዕርቅና የሰላም ፍላጎት አለው፤ እነኚህን ለማግኘት የሚችለውም ምንጫቸው ወደሆነው ወደ እግዚአብሔር በሙሉ ልቡ የተመለሰ እንደሆነ ነው፣ ሁላችን የእግዚአብሔር ይቅር ባይነት ያስፍልገናል፣ ጾመ አርባን ስንጀምር እግዚአብሔር በማክበር መንፈስና በዚሁ ግዜ በተለያዩ ችግሮችና ግጭቶች እጅግ እየተፈተኑ ላሉ ወንድሞቻችን ጋር በመተባበር እንዲሆን አደራ ሲሉ መልካም ቀንና ምሳ በመመኘት ትምህርታቸውን ደምድመዋል፣
ይህ እንዲህ ሳለ አት ፖንተፊክስ በተሰኘው የዘመናችን የትዊተር መገናኛ ለሁላቸው በካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ትምህርት ቤቶች ለሚያስተምሩ አመሰግናለሁ፣ ማስተማር ልክ ሕይወት እንደመስጠት አንድ የፍቅር ተግባር ነው፣ ሲሉ አጭር መልእክት እንደጻፉ ከቅድስት መንበር የወጣ መግለጫ አመልክተዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.