2014-02-28 19:06:04

ጳጳስ ከሙታን ተለይቶ የተነሣ ክርስቶስ ትሑትና ጽኑ ምስክር መሆን አለበት፣


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍርናቸስኮስ ስለ ጳጳሳት የሚያስብ የቅድስት መንበር ማኅበር አባላት ጋር ተገናኝተው በተወያዩበት ወቅት “ቤተ ክርስትያን መንጋዎቻቸውን በሚገባ የሚጠብቁ እውነተኛ እረኞች ያስፈልግዋታል፣ ጳጳስ ከሙታን ተለይቶ የተነሣ ክርስቶስ ትሑትና ጽኑ ምስክር መሆን አለበት፣ አስተዳዳሪ ጳጳሳት አያገለግሉም፣” ሲሉ ጳጳሳት ሲመረጡና ሲሰየሙ መደረግ ያለባቸውን ጥራቶችና ጥንቃቄዎች በዝርዝር ገልጠዋል፣ ባለነው ዘመን ለቤተክርስትያን የሚያስፈልግዋት ጳጳሳት እውነትን በትሕትናና በመተማመን የሚያስተምሩ መሆን እንዳለባቸውም አመልክተዋል፣
ቅዱስነታቸው ጳጳሳት ሲመረጡ የመጨረሻ ፊርማ የሚያኖሩ እንደመሆናቸው መጠን ስለጳጳሳት የሚያስበር የቅድስት መንበር ማኅበር በጸሎትና በጥናት ትክክለኛውን ሰው ለመምረጥ ብዙ ጥረት ማድረግ እንዳለባቸው ለጵጵሳና የሚመረጠው ሰው ደግሞ በማኅበሩ ከመጠራቱ በፊት በጌታ የተጠራ መሆኑን ማረጋገጥ እንደሚያስፈልግም ገልጠዋል፣
“ከበስተሰማይ የሚከታተለን ያስፈልጋል! የሚያስፈልገው እረኛ በእግዚአብሔር ሰፊ ልብ የሚመለከት እንጂ እንደ የአንድ የንግድ ሥራ አስተዳዳሪ የማስተዳደር ችሎታ ያለው አያስፈልገንም፣ በመንፈሳውነት ከፍ ያለና የእግዚአብሔር አመለካከት ያለው በዚሁ መንፈስ የሚመራን ነው የሚያስፈልገን፣ በእግዚአብሔር አመለካከት ብቻ ነው መጻኢያችን የሚወሰነው፣ በሌላ በኩል ደግሞ ለሁሉ አብያተ ክርስያን የሚሆን እረኛ ልዩና አንድ የሆነ መመዘኛ የለንም፣ ኢየሱስ ክርስቶስ የእያናዳንድዋ ቤተ ክርስትያን ችግርና ሁኔታ ስለሚያውቅ ለእርሷ የሚሆን እረኛ እንደሚሰጥ እናምናለን ስለዚህ በኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃን የተመራን እንደሆነ ለእያንዳንዷ ቤተ ክርስትያን የሚሆን እረኛ ለመምረጥና ለመሰየም ልንሳሳት አንችልም፣ ምርጫችን ትክክለኛ እንዲሆን ከተለያዩ ሰብአዊ መመዘኛዎች እውቀትና ጓደኝነት እንዲሁም ሌላ ዝንባሌዎች ነጻ ሆነን የተገቡ እረኞችን እንጂ ለእኛ ደስ የሚሉ እረኞች ከመምረጥ ጥንቃቄ እንደሚያስፈልግም አብራርተዋል፣ በዚህም ምክንያት በዚሁ ማኅበር የሚሰሩ ሁላቸው ኃላፊነታቸውን በሚገባ ለመወጣት ችሎታና ብቃት ያላቸው ሆነው የአገልግሎት ሕይወትና የቅድስና ሕይወት የሚኖሩ መሆን እንዳለባቸውም ገልጠዋል፣ የቤተ ክርስትያናችን መጻኢ መሠረትዋ በሆነው በክርስቶስ እጅ መሆኑን በማመን እና ስቃይና መስቀል ደግሞ ሁሌ እንዳሉ በማስታወስ ከሙታን ተለይቶ የተነሣ ክርስቶስ ምስክሮችን ለማግኘት ብርቱ ጥረት እና ጸሎት እንዲሁም እምነት እንደሚያስፈልግ አደራ ብለዋል፣
“ከሙታን ተለይቶ የተነሣ ክርስቶስ ምስክር ማን ነው? ብለን የጠየቅን እንደሆነ ክርስቶስን ከመጀመርያ የተከተለውና ከሓዋርያት ሥር የተቋቋመና ምስክርነታቸውን የተቀበለ ሰው ነው፣ ይህ መመዘኛ ለእኛም የአንድነታችን መጠናከርያ ነው፣ ጳጳስ ስንል ይህንን ሁሉ የሚመስክር ከቤተ ክርስትያን ጋር ሆነው የክርስቶስ ትንሣኤን የሚመሰክሩ መሆን አለባቸው ሲሉ አሳስበዋል፣
“ስለሌሎች ለመሞት ያለው ብርታት ማለትም ለመንጋዎቻቸው ሲሉ ሕይወትን መሰዋትና ለመንጋዎቹ አገልግሎት ሁሉን መተው በጵጵስና ደም የታተመ ነው፣ ለጵጵስና ተል እኮ ሁሉን መተውና መስዋ ዕትነት ባህርያውያን ናቸው፣ መዓርገ ጵጵስና ለገዛ ራስ ሳይሆን ለቤተ ክርስትያን ለመንጋ ለሌሎች በተለይ ደግሞ ለተገለሉና ለተናቁ ሰዎች ልዩ ትኵረት መስጠት ነው፣” ብለዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.