2014-02-28 16:04:44

ብፁዕ አቡነ ቶማሲ፦ በሶሪያ ሰላም እንዲረጋገጥ የሚወያየው የሰላም ጉባኤ ዘገምተኛ ሂደት


RealAudioMP3 ዋና መቀመጫው ጀነቭ በሆነው በተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብትና ክብር በሚከታተለው ማኅበር የቅድስት መንበር ቋሚ ታዛቢ ቢሮ በዓለም የሚታዩት አንገብጋቢ ጥያቄዎች በጥልቅ የሚከታተል መሆኑ ሲገለጥ፣ ከሚከታተላቸው ጥያቄዎች ውስጥ የሶሪያ ጉዳይ አንዱ ሲሆን፣ በሶሪይ ሰላም ለማረጋገጥ ታልሞ የሚካሄደው የሰላም ውይይት በእውነቱ አስፈላጊ ነው ነገር ግን ዘገምተኛ መሆኑ በዚህ በተባበሩት መንግሥታት ማኅበር የቅድስት መንበር ቋሚ ታዛቢ ብፁዕ አቡነ ሲላቭኖ ማሪያ ቶማሲ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር በስልክ ባካሄዱት ቃለ ምልልስ አስታውቀዋል።
በአሁኑ ሰዓት ለሰብአዊ መብትና ክብር ጥበቃ ጉዳይ ተቀዳሚው ውሳኔ በመካከለኛው ምስራቅ በሌሎች ክልሎች በአፍሪቃ ማለትም በመካከለኛይቱ ረፓብሊካዊት አፍሪቃ በሱዳን፣ በኤውሮጳ እርሱም በኡክራይን ሰላም ማረጋገጥ የሚል መሆኑ ገልጠው፣ ሰለዚህ የሚታዩት ግጭቶች ሰላማዊ መፍትሔ አሰጥቶ የሕዝብ ሰላማዊ ሕይወት ማረጋገጥ የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ የጀነቭ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተቀዳሚ አለማው ነው። ሶርያን በሚመለከት በመካሄድ ላይ ያለው የሰላም ውይይት ዘገምተኛ ነው፣ ሆኖም የሰላሙ ድርድር ቀጣይነት አግኝቶ የታለመው የሰላም ዓላማ ያስጨብጥ ዘንድ የሁሉም መልካም ፈቃድ ይጠይቃል፣ የአገሪቱ ሰላም ለማረጋገጥ የሚካሄደው የሰላም ውይይት ወሳኞችና አቢይ ተጽእኖ ያላቸው አገሮች የተባበሩት መንግሥታት አመሪካና ሩሲያ ሰላም እንዲረጋገጥ ከግላል ግል ጥቅም ተላቀው ገላጋይ ማለትም መካከለኛ ስምምነት ሊያደርጉ ይገባል ብለዋል።
እ.ኤ.አ. 2014 ዓ.ም. ሚያዝያ ወር መግቢያ ሊካሄድ በተወሰነው በመካከለኛው ምስራቅ ሰላም ለማረጋገጥ መከናወን የሚገባው ጉዳይ የሚያፈላልገው ዓለም አቀፍ ጉባኤ በማሮናዊ ሥርዓት ለምትከተው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ካርዲናል በቻራ ራይ እንዲሳተፉ ጥሪ መተላለፉ ብፁዕ አቡነ ቶማሲ ገልጠው፣ ስለዚህ ይኽ ዓይነት ጉባኤ በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ሁኔታ ሰላማዊ መፍትሔ እንዲያገኝ ለሚጥሩት ሁሉ አቢይ ድጋፍ ነው ብለዋል።
በአሁኑ ወቅት እጅግ አሳሳቢ የሆነው በኤውሮጳ የሚታየው እርሱም የኡክራይን ወቅታዊው ሁኔታ ዘክረው፣ ይኽ ጉዳይ የኤውሮጳ ኅብረት አገሮችና ፈደራላዊት ሩሲያ የሚመለከት ነው፣ በርግጥ ሕዝቡ ሉዓላዊነት በሚለው ጥያቄ ለአገሪቱ ፖለቲካዊ ኤኮኖሚያዊ የመከላከውያው ኃይል ጉዳይ ጭምር ብሔራዊ ሉአላዊነት ያለው እንዲሆን ለመጠየቅ ያካሄደው አድማ በአገሪቱ ያለው የኤውሮጳ ደጋፊው ምዕራባዊ ክልልና የሩሲያ ፖለቲካ ደጋፊ ምስራቃዊ ክልል መካከል ውጥረት መኖሩ የሚያመለክት ነው፣ ምንም ቢሆን አገሪቱ ሉአላዊነቷ እንድነቷ የሚያቅብ ሰላማዊ እርቅ ያለው አስፈላጊነት ገልጠው ከዚሁ ጋር በማያያዝ የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብትና ክብር አስከባሪ ድርጅት 25ኛው ክፍለ ጉባኤው ውሁዳን የኅብረተሰብ ክፍል ዜጎች ለመብት ረገጣ አደጋ የሚያጋልጠው አመጽ አድልዎ የመሳሰሉት ጸረ ሰብአዊ መብትናክብር ጉዳይ ርእስ ሥር የሚመክር በቅርቡ እንደሚጀምር አስታውሰው፣ በዚህ ሊካሄድ በተወሰነው ጉባኤ ቅድስት መንበር የምግብ አቅርቦት ሰብአዊ መብት፣ በሕፃናት ላይ የሚፈጸመው አመጽ ቀድሞ ለመከላከል፣ የሃይማኖት ነጻነት በተሰኙት ርእሶች ሥር የሚደምጠው ንግግር እንዳለ ገልጠው ይኽም የቤተ ክርስቲያን የማኅበራዊ አንቀጸ እምነት ትምህርት መሠረት የሰብአዊ መብትና ትብብር የመሳሰሉት እሴቶች ለገዛ እራሱ የሰብአዊ መብትና ክብር ክፍል ነው ስለዚህ እድገት ትብብር የሰብአዊ መብትና ክብር ጥበቃ ለማረጋገጥ መሠረት መሆኑ እንደምታስተጋባ ገልጠው ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.