2014-02-28 15:59:50

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ ክርስትናውን በቃልና በሕይወት የማይኖር ክርስቲያን የሚገድል መሰናክል ይሆናል


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. የካቲት 27 ቀን 2014 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እንደ ተለመደው ጧት በአገረ ቫቲካን ቅድስት ማርታ ሕንፃ በሚገኘው ቤተ ጸሎት በመሩት መስዋዕተ ቅዳሴ፦ “ክርስትናውን እምነት በቃልና በሕይወት ሳያሳካ የሚኖር ክርስቲያን ለሞት የሚዳርግ ገዳይ እንቅፋት ይሆናል” በሚል ክርስቲያን ክርስትናውን እምነቱን በሕይወት ኣሳክቶና ነቅቶ ሊመሰክረው የተጠራ መሆኑ በሚያሳስብ ጥልቅ ትእዛዛዊ ምዕዳን ላይ ያነጣጠረ ስብከት ማሰማታቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
ቅዱስ ኣአባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ምሥጢረ ሜሮን የሚቀበል ክርስቲያን ለመሆን ያለው ፍላጎት በጽናት እንደሚያረጋግጥና፣ ክርስቲያን መሆን ማለት ደግሞ ኢየሱስ ክርስቶስን መምስከር ማለት ነው። እንደ ክርስቲያን የሚያስብ እንደ ክርስቲያን የሚያዳምጥ እንደ ክርስቲያን የሚተገብር ይኽም ቃልንና ሕይወት ያሳካ ክርስቲያናዊ ሕይወት መኖር ያለው አሰፍላጊነትና ይኽ ደግሞ አማራጭ እንዳልሆነም ገልጠው፣ አንድ ሰው አማኝ ነኝ እምነት አለኝ ቢል ቃልንና ሕይወትን ያላሳካ እምነት የሚኖር ከሆነ ክርስቲያን አይደለም፣ ቃልንና ሕይወትን ያላሳካ ክርስቲያናዊ ሕይወት በአሁኑ ወቅት አቢይ ጉዳት እያስከተለ መሆኑም ሲገልጡ፦ “በዕለቱ ምንባብ ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ ክርስቲያን ነን በማለት ገዛ እራሳቸውን ከፍ ከፍ የሚያደርጉ ሆኖም ግን ሠራተኞቻቸውን ግን ሲበዘበዙ ይታያል ይኸንን ሓዋርያው፣ ‘…እነሆ ኣርሻችሁን ያጨዱት የሠራተኞች ደመወዝ በእናንተ ተቀምቶ ይጮኻል የአጫጆችም ድምጽ ወደ ጌታ ጸባዕት ጆሮ ገብቶአል … ‘ (ያዕ. ምዕ. 5፣ 1-6) አዎ ጌታ ኃያል ነው፣ ይኸንን ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ የሚሰማ ሰው በቀጥታ ይኽማ የኮሙኒስቶች ጽንሰ ሃሳብ ነው ሊል ይችላል፣ አይ ይኽንን ያለው ሐዋርያ ያዕቆብ ነው፣ የጌታ ቃል ነው፣ ቅንነትና ሕይወትና ቃልን ያላሳካ ክርስቲያን ክርስትናውን ባላሳካ ሕይወት የሚኖር እንቅፋት ነው፣ የሚገድል እንቅፋት ነው” እንዳሉ የገለጠው የቅድስት መንበር መግለጫ አክሎ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዙውን ጊዜ በመደጋገም ስለ እንቅፋት መሆን ያለው አደገኛነት ደጋግሞ የሚሰጠው ማስጠንቀቂያ መሆኑና በዕለቱ ምንባበ ወንጌል ሉ.ቃ. ምዕ. 9፣ 41-50 የተደመጠውን ጠቅሰው፦ …በእኔም ከሚያምኑት ከእነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን የሚያሰናክል ሁሉ ትልቅ የወፍጮ ድንጋይ በአንገቱ ታስሮ ወደ ባሕር ቢጣል ይሻለው ነበር…..’ አንድ ኢእግዚአብሔራዊነትን የሚያምን ሰው አጋጥሞህ አላምንም እግዚአብሔር የለም ቢሊህ እንተ ስለ እግዚአብሔር ህላዌ የሚያረጋግጥ በዚህ ዓለም የተጻፉት መጻሕፍት ብታነብለት ይለወጣል ብሎ ማሰብ ያስቸግራል፣ ነገር ግን በዚህ በኢአማንያን ፊት በቃልና ሕይወት የተሳካ ምስርክነት ስታቀርብ ይኽ ተጨባጭ ሁነት ቀስ በቀስ በኢአማንያኑ ልብ መሥራት እንደሚጀምር አያጠራጥርም፣ የአንተ የተሳካው ምስክርነት በኢአማንያኑ ልብ ውስጥ ገብቶ ውስጣዊው አለ መረጋጋቱን ስለ ሚያነቃቃው ይኽ ደግሞ ለመንፈስ ቅዱስ ሥራ እድል ይሆናል፣ መላይቱ ቤተ ክርስቲያን በጠቅላላ አማንያን እኛም ‘ጌታ ሆይ የክርስትናችን እምነት የተሳካ ነው ወይ ብለን እንጠይቀው’ ብለው ስብከቱን ሲያጠቃልሉ፦ “ሁላችን ኃጢአተኞች ነን፣ ሆኖም ሁላችን ምህረትን የመለመን ብቃቱ አለን። እርሱ ምኅረትን በመስጠትና የማይደክም የማይሰለች ነው ምህረትንና ይቅርታን የመለመኑ ትሕትና ያስፈልጋል፣ ‘ጌታ ሆይ የተሳካ ክርስቲይናዊ ሕይወት አልኖርኩምና ማረኝ፣ ብለን እንለምነው በተሳካ ሕይወት በክርስትናው እምነታችን እንጓዝ ማለትም በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያለን እምነት በቃልና በሕይወት እየመሰከርን እርሱ ኃጢአተኞች መሆናችን ያውቃል፣ ሆኖም ምኅረት ለመጠየቅ የሚያበቃ ብርታት፣ ሲሳሳት እንቅፋት ሆኖ መገኘት እጅግ የሚያስፈራቸው እንድንሆን ዘንድ ጌታን ጸጋውን ይስጠን” እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.