2014-02-20 09:46:36

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ ፈተና ለሞት የሚዳርግ አደገኛ ወረርሽኝ ቢሆንም ፈውሱ የኢየሱስ ቃል ነው


RealAudioMP3 አሣሣቹ ፈተና ለመቋቋም የሚቻለው የኢየሱስ ቃል በማዳመጥ ብቻ መሆኑ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ሁሌ ጧት እንደ ተለመደው እ.ኤ.አ. የካቲት 18 ቀን 2014 ዓ.ም. በአገረ ቫቲካን ቅድስት ማርታ ሕንፃ በሚገኘው ቤተ ጸሎት በመሩት መስዋዕተ ቅዳሴ ባሰሙት አስተንትኖ እንዳሰመሩበት ሲገለጥ፣ ምንም’ኳ ደካሞች ብንሆንም ክርስቶስ በእኛ ላይ ያላው እማኔ ውስንነታችንን የሚሻገር ሰፊ አድማስ በመክፈት ዘወትር እንደሚለግስልን በማብራራት፣ በላቲን ሥርዓት የዕለቱ ምንባብ ላይ ተንተርሰው፣ የቅዱስ ያዕቆብ መልእክት እንድ እውነት እርሱም ሰውን የሚፈትነው የሚፈታተነው እግዚአብሔርና ከእግዚአብሔር አለ መሆኑ ያረጋግጥልናል፣ ስለዚህ ፈታኙ በሰው ገዛ እራስ ካለው ኃጢአት የሚጸንስና የሚዘራው ስሜት ሲሆን፣ አንድ የተፈጸመ ኃጢአት ሞትን እንደሚያስከትል፦ “ፈተና ከየት ይመጣል? በእኛ ውስጥ እንዴት ባለ ሁኔታ ይሠራል? አዎ ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ ፈተና ከእግዚአብሔር ሳይሆን ከገዛ እራሳችን ስሜት፣ ደካማነት፣ የአዳም ኃጢአት ጥሎት ካለፈው ጠባሳ የሚመነጭ መሆኑ ያረጋግጥልናል፣ ፈተና ሦስትስ ባህርያት አሉት እርሱም ያድጋል ይዛመታል፣ ገዛ እራሱ ምክንያታዊ ሆኖ ይቀርባል፣ ኢየሱስ ስለ መልካም ዘርና እንክርዳድ ምሳሌ በመጠቀም ሲያስተምር፣ መልካሙ ዘር ይፈራል በጠላት የሚዘራው እንክርዳድም በተመሳሳይ መልኩ ይፈራል፣ ፈተናም እያደገ ይሄዳል ካልገታነው ሁለመናችንን ይወርሳል” በዕለቱ የማርቆስ ወንጌል ምንባበ ዘንድ ደቀ መዛሙርት እርስ በእርሳቸው በቂ እንጀራ ይዘው ባለ መምጣታቸው ሲወቃቀሱና ኢየሱስ በሁኔታው ተገርሞ ከፈሪሳውያንና ከሄሮዶስ እርሾ እንዲጠነቀቁ የሚሰጠው ማሳሰቢያ ቅዱስ አባታችን ጠቅሰው፣ ሆኖን ደቀ መዛሙርት የሚለውን ከማዳመጥ ይልቅ በገዛ እራሳቸው ተዘግተው እርስ በእራስቸው ይወቃቀሳሉ፣ ይኽ ደግሞ ለጌታ ቃል እድል ቦታ አለ መስጠት ማለት መሆኑ፦ “እኛም ልክ እንደዚሁ በፍተና ላይ ስንገኝ፣ የጌታ ቃል አናዳምጥም እናስተውልም፣ ኢየሱስ ከዚያ በእራስ ላይ ከሚዘጋው ሁለ መናን ከሚያደነዝዘው ፈተና ደቀ መዛሙርቱን ለማላቀቅ ተአምር ይሰራል፣ እንጀራውን ያበዛል፣ እንዲህ ባለ መልኩም ከዚያ እርቆ ከማስትዋል የሚያስቀረን ፈተና ያላቅቀናል፣ በፈተና ስንገኝ ከፈተናው የሚያላቅቀን ከፊታንች ሰፊ አድማስ የሚከፍት የኢየሱስ ቃል ነው፣ ቃሉ ያድናል፣ ሁሌ ከፈተና እንዴት ለመላቀቅ እንደምንችል ያስተምረናል፣ ኢየሱስ ታላቅ ነው፣ ከፈተና እንዴት ለመላቀቅ መንገዱን የሚያስተምር ብቻ ሳይሆን በእኛ ላይ መተማመንን ይቀጥላል” ይኽ ጌታ በእኛ ላይ የሚያኖረው መተማመን በፈተና ላይ ስንገኝ ምንም’ኳ ብንፈተንና ኃጢአተኞችም ብንሆን ፈጽሞ የማይተወን እኛን ከመጠባበቅ የማይቦዝን ቅርባችን ከመሆን እንደማያቋርጥ ቅዱስነታቸው በማብራራት፦ “ጌታ ከደቀ መዛሙርት ጋር እንዳደረገው ሁሉ ዘወትር በፈተና ስንገኝ በትእግስቱ በመመልከት፣ በፈተና በዚያ በችግር ተከበህ በነበርክበት ወቅት ያደረግኩልህን አስብ አይዞህ አትፍራ አይኖችህን ወደ ላይ በማድረግ ሰፊ የጌታ አድማስ ተመልከት፣ በገዛ እራስህ ላይ እትዘጋ፣ ለእያንዳንዳችን የሚለንን ቃል ለማዳመጥ እንድንችል እንዲደግፈን እንለምን፣ በኃጢአት ስንገኝ ስንወድቅ ስንፈተና የሚያድነን የእርሱ ቃል ነው” በማለት ያስደመጡት አስተንትኖ እንዳጠቃለሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.