2014-02-20 09:50:55

ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ “ቅዱስ ውሳኔ ስለ ሥርዓተ አምልኮ (ሊጡርጊያ)”


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. የካቲት 18 ቀን 2014 ዓ.ም. በጳጳሳዊ ላተራነንሰ መንበረ ጥበብ፦ “ቅዱስ ጉባኤ፣ ለአንድ አቢይ ቤተ ክርስቲያናዊ ሱታፌ መትጋትና ለዚሁ ዓላማ በመቆም ማመስገን” በሚል ርእስ ሥር የመለኮታዊ አምልኮ እና የቅዱሳት ምስጢራት ሥርዓት ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር ሁለተኛው የቫቲካን ቅዱስ ጉባኤ ሥርዓተ አምልኮ (ሊጡርጊያ) ውሳኔ ዝክረ 50ኛው ዓመት ምክንያት ያዘግጀው ዓውደ ጥናት መከፈቱ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ፋቢዮ ኮላግራንደ አስታወቁ።
ስለዚሁ በመካሄድ ላይ ስላለው ዓውደ ጥናት በማስመልከት የመለኮታዊ አምልኮና የቅዱሳት ምሥጢራት ሥርዓት ተንከባካቢ ቀዱስ ማኅበር ኅየንተ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ኹዋን ሚገል ግረነስኪ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ “እግዚአብሔር ለሰጠው የሥርዓተ እምልኮ ኅዳሴ ማመስገን የተገባ ነው፣ ውሳኔው ለቤተ ክርስቲያን አቢይ ጸጋ እርሱም የሕዝበ እግዚአብሔር ሊጡርጊያዊ ሱታፌው ያጎለበተ፣ ሕዝበ እግዚአብሔር በሥርዓተ አምልኮ ያለው ተሳታፊነት በሁለተኛ ደረጃ የሚቀመጥ አለ መሆኑ ቅዱስ ጉባኤ በመንፈስ ቅዱስ አስተንፍሶ ለሰጠው ውሳኔ የሚያመሰግን ዓውደ ጥናት ከመሆኑም ባሻገር፣ ከውሳኔው በኋላ ዛሬ አርእስተ ሊቃነ ጳጳሳት በተለያዩ ሥልጣናዊ አስተምህሮቻቸው፣ ምዕዳንና ዓዋዲ መልእክቶቻቸው አማካኝነት የሰጡት ውሳኔው እግብር ላይ ለማዋል ያመለከቱት መንገዱ ሁሉ በመከተል ለመኖር ምን መደረግ አለበት ለሚለው ጥያቄ መልስ ለማቅርብ የሚጥር ዓውደ ጥናት ነው” ካሉ በኋላ ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ “Novo Millennio Ineunte-በአዲስ የሚለኒዩም ጅማሬ” በተሰኘው ሓዋርያዊ መልእክት ሥር በአዲስ ሚለኒዩም የቤተ ክርስቲያን ሐዋርያው ግብረ ኖልዎ እርሱም ቤተ ክርስቲያናዊ ሱታፌ ለመኖር የሚያግዝ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ያሰፈረው ቤተ ክርስትያናዊነት እንዴት ለመኖር እንደሚቻል በማመልከት፣ ሱታፌ ማለት ቃሉን መቀበል ሥጋሁ ወደሙ መቀበል ማለት ነው፣ ስለዚህ በቤተ ክርስቲያን እንደ የክርስቶስ አካል የምትኖረው እንቅስቃሴ የሚመለክት መሆኑ ብፁዕነታቸው ገልጠው፣ እርግጥ እውነትን ፍለጋ የሚደረገው ሥነ ባህላዊ ጥናት የሚቀጥል ነው፣ ጥልቅ ጥናቱም የእውነትን ባህርይ የሚያከበር መሆን አለበት፣ ሊጡርጊያ የሚኖረው እውነትና በሊጡርጊያ የሚኖረው እውነት ለመገንዘብ ሥነ ባህላዊ ጥናት ይጠይቃል፣ ይኽ ደግሞ የሊጡርጊያ ባህርይ መረዳት ማለት ነው። ስለዚህ የሊጡርጊያ ቲዮሎጊያዊ እውነት መንፈሳዊና የሊጡርጊያ ምሥጢር ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ትርጉም ለመረዳት የሚደግፍ ዓውደ ጥናት ነው በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.