2014-02-19 18:15:10

ከወንድሞቻችን ጋር እንታረቅ፣ ሕሜታና ስም ማጥፋት ገዳይ ናቸውና ወጊድ እንበላቸው”


ቅ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ትናንትና እኩለ ቀን ላይ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ከማሳረጋቸው በፊት ባቀረቡት ጉባኤ አስተምህሮ “ከወንድሞቻችን ጋር እንታረቅ፣ ሕሜታና ስም ማጥፋት ገዳይ ናቸውና ወጊድ እንበላቸው” ሲሉ በሥርዓቱ የተነበበው የዕለቱን ቃለ ወንጌል መሠረት በማድረግ ሰፊ አስተንትኖ አቅርበዋል፣
በላቲኑ ሥር ዓተ አምልኮ ትናንትና የተነበበው የወንጌል ክፍል ከወንጌል ማቴዎስ የተወሰደ ሲሆን በተራራ ስብከት የሚታወቀው የመጀመርያ የጌታ ስብከትን የያዘ ሲሆን በተለይ በቁጥር 23 እና 24 ላይ “እንግዲህ መባህን በመሠዊያው ላይ ብታቀርብ፥ በዚያም ወንድምህ አንዳች በአንተ ላይ እንዳለው ብታስብ፥ በዚያ በመሠዊያው ፊት መባህን ትተህ ሂድ፥ አስቀድመህም ከወንድምህ ጋር ታረቅ፥ በኋላም መጥተህ መባህን አቅርብ” አቅርብ በሚለው ነጥብ ላይ በማትኮር ለጌታ በጸሎት አምልኮ ከማቅረብ ከወንድሞቻችን ጋር መታረቅ መቅደም እንዳለበት የሚያሳይ መሆኑን አመልክተዋል፣ ወንጌሉ እንደሚያመልክተውም ይህ ታላቅ ስብከት ወይምን የተራራ ስብከት በማለት የሚታወቀው የሙሴ ሕግንና ኦሪትን ለመሻር ሳይሆን ሙላትና ፍጽምና እንዲያለብሳቸው እንደመጣና ራሱም ኢየሱስ በኦሪት ሕግ እንዳደገና እተግባር ላይ እንዳዋለው ገልጠው ኢየሱስ በዚሁ ስብከት ቃላት እጅግ ጐጂ መሆናቸውን ለመግለጥ ያህል አትግደል የሚለውን ትእዛዝ በመጥቀስ ያስተማረውን አስታውሰዋል፣ “ኢየሱስ ቃላት ሊገድሉ እንደሚችሉ ያሳስበናል! አንድ ሰው ምላሱ የእባብ ስንል ምን ማለት ይሆን? ቃላቶቹ እንደሚገድሉ ለማመልከት ነው፣ ስለዚህ ጓደኛችንን ለመጉዳት እጃችን መሰንዘር ብቻ ሳይሆን በእርሱ ላይ የቍጣ የቂም ቃላት በመጠቀም ስሙን በማጥፋት ልንጉዳው ከሞከርን እንደገደልነውና አትግደል የሚለውን ት እዛዝ እንዳላከብርን ያሳስበናል፣ ስለዚህ ስለወንድሞቻችንና እኅቶቻችን መጥፎ አንናገር ሕሜታን እናውግድ አለበለዚያ ቃልቶች ሊገድሉ ይችላሉና፣ “ ስም ማጥፋት ማማት ስንጀምረው ቀላል ነገር ደስ የሚያሰኝ መዝናናኛ ሆኖ ሊሰማን ይችላል፣ ነገር ግን በመጨረሻ ላይ ልባችንን በቂመ በቀልና ምቀኝነት በመሰሉ መራራ ነገሮች ሊሞላውና ሊመርዘው ይችላል፣ እውነት እላችኋለሁ የዚህ መድኃኒት ትንሽ ነገር ነው እያንዳንችን ሕሜታን ለማውገድ ጽኑ ፍቃድና ውሳኔና ያደረግን እንደሆነ በመጨረሻ ቅዱሳን እንሆናለን፣ ኢየሱስ የሚያቀርብልን የፍቅር ምርጫ ወደር የሌለው ነው፣ ይህ ፍቅር መለኪያ የለውም፣ “የጓደኛ ፍቅር ከእግዚአብሔር ጋር ላለን ፍቅር ዋስትና የሚሰጥና ኢየሱስ የሚያቀርብልን መሠረታዊ ዝንባሌ ነው፣ ከጓደናችን ጋር ያልታረቅን እንደሆነ ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ግኑኝነት እውነተኛ ሊሆን አይችልም፣ ስለዚህም ነው ኢየሱስ የእግዚአብሔር ት እዛዛት ውጭ አዊ መታዘዝንና መከታተልን ትቶ ጥልቅ ወደሆነው መሠረታዊ ነገር የሚሄደው በሰው ልጅ ልብ በኅሊና ያለው ነገር ዋነኛ ወሳኝ መሆኑን ለመግለጥ የተግባሮቻችን መልካምም ይሁኑ መጥፎ ምንጭም የሰው ልጅ ልብ መሆኑን ሊያመለክት ስለፈለገ ነው፣ “መልካም መንፈሳዊ ልማድ ለመፍጠር ሕጋጋትን ቃል ለቃሉ ብቻ መከታተል በቂ አይደለም ነገር ግን ጥልቅ የሆኑና የምስጢራዊ ጥበብ ማለት የእግዚአብሔር ጥበብ መግለጫ ያስፈልጋል ይህም በመንፈስ ቅዱስ ጸጋ ልንቀበለው እንችላለን፣ እኛ ደግሞ በክርስቶስ በማመን ለመንፈስ ቅዱስ ስራ ክፍት ለመሆን እንችላለን ይህም በመለኮታዊው ፍቅር ለመኖር ያስችለናል፣ እያንዳንዱ ት እዛዝ በፍቅር ፍጽምና ማግኘት እንዳለበት መገንዘብ ያስፈልጋል ሲሉ ትምህርታቸውን ደምድመዋል፣







All the contents on this site are copyrighted ©.