2014-02-12 16:07:23

ደ ቦርቶሊ፦ የበነዲክቶስ 16ኛ ስልጣን ማስረከብ ነቢያዊ ትእምርት ለር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ አዲስ በር የከፈተ ተግባር ነው


RealAudioMP3 የቅዱስ ጴጥሮት ተከታይነት የሚጠይቀው ጉልበት ያንሰኛልና በእግዚአብሔር ፈቃድ ሓዋርያዊ ሃላፊነቴን ለእግዚአብሔር አስረክባለሁ ያሉበት ዝክረ አድነኛው ዓመት ምክንያት በኢጣሊያ ኮረረ ደላ ሰራ ዕለታዊ ጋዜጣ ዋና አስተዳዳሪ ፈሩቾ ደ ቦርቶሊ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ የካቲት 11 ቀን 2013 ዓ.ም. ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ቅዱስ ጴጥሮሳዊ ስልጣናቸውን ለቀቁ የሚል ዜና እንደተሰማ ገርሞኝ የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ብፁዕ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ስቃይ እንዳሰላስል ከማድረጉም አልፎ ይኽ የማንኛውም የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ተግባርና ትህትና መሆን አለበት የሚል አመለካከት በአምሮአቸው እንደፈጠረ ገልጠው፣ በነዲክቶስ 16ኛ ያሳዩት ተግባር አቢይ በቤተ ክስቲያን ለብዙ ዘመናት ያልታየ ታሪካዊና ሥር ነቀላዊ ተግባር ነው መግሆኑ ገልጠዋል።
ከሳቸው በኋላ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሆነው የተመረጡት ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ሲመረጡ በተራ አነጋገር በምርጫው ከሳቸው ያላነሰ ድምጽ በማግኘት የተወዳደሩዋቸው ነው ተብለው የሚነገርላቸው ብፁዕ ካርዲናል ቦርጎሊያ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ መመረጣችው እሳቸው የወሰዱት ውሳኔ ትንቢት የጸነሰው ምርጫ ነበር ለማለት እንደፍራለሁ፣ በመሆኑ ነቢያዊ ተግባር ነው። ትንቢት የቤተ ክርስቲያን ኅዳሴ የሚል ነው። ቅዱስነታቸው ልሂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛና ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ሁለት በተለያየ ባህርይ አበይት ናችው፣ ቤተ ክርስቲያን የማይቋረጥ ቀጣይነት ባህርይ የሚኖርባት መሆንዋ ተመስክረዋል በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.