2014-02-12 16:01:19

ቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛና በገዛ ፈቃድ ቅዱስ ጴጥርሳዊ ስልጣን መልቀቅ
ዝክረ አንደኛ ዓመት


RealAudioMP3 የዛሬ አንድ ዓመት በፊት እ.ኤ.አ. የካቲት 11 የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ቅዱስነታቸው ልሂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በገዛ ፈቃዳቸው ይኽም የቅዱስ ጴጥሮስ ተልእኮ በሚገባ ለመፈጸም የሚጠይቀው ጉልበት መዳከም ምክንያት ለቤተ ክርስቲያና ለሕዝበ እግዚአብሔር በማሰብ በጸሎት አና አስተንትኖ የእግዚአብሔር ፈቃድ በመታዘዝ ስልጣኑን በገዛ ፈቃዳቸው እንደለቀቁ ያሳወቁባት ቀን መላ ቤተ ክርስቲያንና ዓለም ያሳሰበ ውሳኔ፣ ወዲያውኑ ያስገረመና ጭንቀት ያሳደረ ሆኖ ቀጥሎ ውሳኔ ያርቆ አሳቢነት ጥበብ የተካነ ብቻ ካልሆነ በስተቀረ ማንም የማይፈጽመው የአንድ አቢይ ሰው የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ የላቀ መንፈሳዊንት የሚያጎላ የሚሰጠው መሆኑ ሁሉም ተገንዝቦት የላቀ ትህትና የመሰከረ ለእግዚአብሔር ፈቃድ የታዘዘ መሆኑ ተገልጠዋል።
በነዲክቶስ 16ኛ በብፁዓን ካርዲናሎች ጉባኤ ፊት ተገኝተው በላቲን ቋንቋ እ.ኤ.አ. የካቲት 11 ቀን 2013 ዓ.ም. በሮማ ሰዓት አቆጣጠር ልክ ከጠዋቱ 11 ሰዓት ተኩል ላይ ሰላምታን አቅርበው ማንም ያልጠበቀው ፈጽሞ ይሆናል ያላለውን በአእምሮውም ያልነበረው፣ ለቤተ ክርስቲያንና ለሕዝበ እግዚአብሔር ጥቅም ለእግዚአብሔር ፈቃድ በመታዘዝ በእድሜ መግፋትና የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይነት የሚጠይቀው ጉልበት መጓደል ምክንያት ጴጥሮሳዊ ስልጣኔን አስረክባለሁ በማለት ገልጠው ገና እንዳበቁ፣ የዓለም የመገናኛ ብዙኃን ቀዳሜ ገጽ በመስጠት የተለያየ አስተያየት ወዲያውኑ የሰጡበት ሁሉንም ያስገረመ ውሳኔ መሆኑ የሚዘከር ሲሆን፣ እ.ኤ.አ. የካቲት 13 ቀን 2013 ዓ.ም. እንደ ቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ለመጨረሻ ጊዜ የለገሱት ረቡዓዊ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ፦ “ወድ ወንድሞቼና እህቶቼ እደምታውቁት ሁሉ ቅዱስ ጴጥሮሳዊ ስልጣኔን በገዛ ፈቃዴ አስረክቢያለሁ…ስለ ወዳጅነታቸሁ አመሰግናችዋለሁ፣ እ.ኤ.አ. የካቲት 19 ቀን 2005 ዓ.ም. ጌታ በኃላፊት ያሰረከበኝ ጴጥሮሳዊ ስልጣን በነጻነት ለቤተ ክርስቲያን እርባና በእግዚአብሔር ፊት ከረዥም ጸሎትና አስተንትኖ በኋላ በሙሉ የህሊና አስተዋይነት የውሳኔው ከባድነትን በመቀበል ቅዱስ ጴጥሮሳዊ ሥልጣን የሚጠይቀው ጉልበት መጓደል ምክንያት ላስረከበኝ ጌታ በፈቃዱ ለእርሱ በመታዘዝ ለእርሱ አስከረክቢያለሁ” ሲሉ ማስደመጣቸው የሚታወስ ሲሆን፣ በላቲን ሥርዓት የአቢይ ጾም መግቢያ ምክንያት በቅዱስ ጴጥሮስ ባሲሊካ በመሩት በራስ ላይ ዓመድ የመነስነስ ሥርዓተ ጸሎት ለተገኘው በብዙ ሺህ ለሚገመተው ምመን ብፁዓን ካርዲናሎች ብፁዓን ጳጳሳትና ካህናት ሁሉ በተገኙበት በዚያኑ ወቅት የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል በርቶነ ባስደመጡት ንግግር፦ “ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ለሰጡት ብርሁ የገርነት የየዋህነት በእግዚአብሔር ማሳ አገልጋይ አብነት እናመሰግንዎታለን፣….አገልግሎቱም እግዚአብሔርን ወደ ሕዝብ ሕዝብ ወደ እግፍዚአብሔር የሚደርስ ነው። በዚህ ተልእኮ የፈጸሙት የጥበብ የትህትና አገልግሎት አብነት ነው” እንዳሉም የቅድስት መንበር መግለጫ ያስታውሳል።
እ.ኤ.አ. የካቲት 14 ቀን 2013 ዓ.ም. ቅዱስነታቸው ልሂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የሮማ ሰበካ ካህናትና ቆሞሶችን ተቀብለው፦ “ምንም’ኳ ቅዱስ ጴጥሮሳዊ ሥልጣኔን ባስረክብ በጸላይ ገዳማዊ ሕይወት የምኖር ብሆንም ቅሉ፣ በጸሎት ለሁላችሁ ቅርብ ነኝ፣ እናንተም በዚህ ዓይነት መንፈስ ለእኔ ቅርብ እንደምትሆኑ ተስፋ አደርጋለሁኝ” የሚል ጥልቅ ሃሳብ ዓዘል ስልጣናዊ ንግግር ማስደመጣቸው ያስታወሰው የቅድስት መንበር መግለጫ አክሎ፦ እ.ኤ.አ. ሰንበት የካቲት 24 ቀን 2013 ዓ.ም. እንደ ቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ እኩለ ቀን ጸሎት መልእከ እግዚአብሔር ከመምራታቸው በፊት ባስደመጡት አስተንትኖ፦ እግዚአብሔር ወደ ተራራ እወጣ ዘንድ ጠርቶኛል፣ ይኽ ደግሞ በጥልቀትና በጽሞና በአስተንትኖ በጸሎት እጠመድ ዘንድ ስለ ፈለገ ነው። ቤተ ክርስቲያንን መተው ማለት ግን አይደለም፣ ኃላፊነቱን በገዛ ፈቃዴ እርሱ ሲወስን በዚህ ዓይነት ውሳኔ ቤተ ክስቲያንን እስካሁን ድረስ እንዳደረግኩት በተመሳሳይ ጽናትና ጥልቅ መሥዋዕትነት ካለኝ እድሜ ጋር በተስተካከለ አገልግሎት አገለግል ዘንድ ነው” እንዳሉ ይዘክራል። “…ከመስቀል ለመሸሽ አይደለም፣ በአዲስ አገባብ ከተሰቀውለው ጌታ ጋር የምሆንበት የምኖርበት ሁነት ነው። ቤተ ክርስቲያንን ለማስተዳዳር የነበረኝ ጴጥሮሳዊ ሥልጣን በመያዝ ሳይሆን በጸሎት በመንፈስ በቅዱስ ጴጥሮስ ክልል የምኖርበት አገልግሎት ነው። በዚያች ጀልባ ጌታ አለ፣ ይህች በጀልባ የምትመሰለው ቤተ ክርስቲያን የእኔ ሳትሆን የጌታ መሆንዋ ዘወትር ግንዛቤውና እምነቱ አለኝ፣ የእርሱ ነች ትሰጥም ዘንድም አይተዋትም፣ የሚመራት እርሱ ነው፣ እርግጥ ነው፣ በመረጣቸውና በጠራቸው ሰዎችን አማካኝነት ይመራታል፣ ምክንያቱም ፈቃዱ ነውና። ይህ በማንም በምን የማይደበዝዝ የዘወትር እምነቴ ነው” እንዳናሉና እ.ኤ.አ. የካቲት 28 ቀን 2014 ዓ.ም. ይፋዊ ቅዱስ ጴጥሮሳዊ ሥልጣን በማስረከብ ሮማ አቅራቢያ በካስተል ጋንዶልፎ ወደ ሚገኘው ጳጳሳዊ ሕንፃ ለመዛወር በቅድሚያ ከ 144 ብፁዓን ካርዲናሎች ጋር በቅዱስ ቀለመንጦስ የጉባኤ አድራሽ ተገናኝተው፦ “ዘወትር ለመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ የተገዛችሁ ትሆኑ ዘንድና ጌታ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ በመንፈስ ቅዱስ ይሰጠንም ዘንድ በጸሎቴ ለእናተ ቅርብ ከመሆን አላቋርጥም፣ የእርሱ ፍላጎትና ፈቃድ ይገለጥ ዘድን፣ ከእናንተ መካከል መጪው የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ አለ፣ ከዚህች ሰዓት ጀምሬ አለ ምንም ቅድመ ሁነትና በሙሉ ተአዝዞና በእክብሮት ለሚመረጡት የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ አረጋግጥለታለሁ” የሚል ጥልቅ ሃሳብ አዘም መልእክት አስደምጠው በአገረ ቫቲካን ከሚገኘው የሄሊኮፕተር ማረፊያ ሲነሱ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ወደ አራት ሺሕ የሚጠጋ ሕዝብ ቅዱስነታቸው ለመሰናበት በተገኘበት ልክ በሮማ ሰዓት አቆጣጠር 5 ሰዓት ላይ ከአገረ ቫቲካን ተነስተው ካስተል ጋንደልፎ እንደደረሱም ተመሳሳይ አቀባበል ተደርጎላቸው እዚያው ባስደመጡት ንግግር፦ “እንደ ተራ መንፈሳዊ ነጋዲ እዚህ በመካከላችሁ እገኛለሁ፣ ይኽ ደግሞ የመጨረሻው የምድራዊ ሕይወቴ ነጋዲነት የሚመለከት ነው። በምሉ ልቤና በፍቅር በጸሎቴ በአስተንትኖየ ባለኝ አቅም ለሁሉምና ለኵላዊት ቤተ ክርስቲያንና ለመላ ሰው ልጅ ጥቅም እተጋለሁ፣ ለእኔ ባላችሁ ፍቅር መደገፌ ይሰማኛል፣ ደህና እደሩ” ብለው ተሰናብተው የካተል ጋንደልፎ በሮች በአገረ ቫቲካን ጳጳሳዊ የስዊዘርላንድ ዘብ ጥበቃ በሰጡት የሰልምታ ሥነ ሥርዓት መሠረት ጳጳሳው ሕንጻ በሮች ተዘግተው አዲስ የመረጡት ሕይወት አንድ በማለት መኖር እንደጀመሩ የቅድስት መንበር መግለጫ ያስታውሳል።







All the contents on this site are copyrighted ©.