2014-02-10 16:48:27

የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት፡


ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ትናትና ሰንበት በቅዱስ ጰጥሮስ ከተሰበሰቡ ምእምናን ጋር መልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ደግመዋል ። ፓፓ ፍራንሲስ የዕለቱ ቃለ ወንጌል ጠቅሰው ኢየሱስ ክርስቶስን እንደተከተሉ ሐዋርያት እናም የምድር ጨው የዓለም ብርሃን እንድንሆን ተጠርተናል ይህ የሚሆነው ግን ትሕትና ሲኖረን ነው በማለት ለምእመናን ተናግረዋል። በማያያዝ ሚስጢረ ጥምቀት የተቀበልን ሁላችን ሐዋርያት እና የቅዱስ ወንጌል ልዑካን እንድንሆን ተጠርተናል ህያው ቅዱስ ወንጌል ለመሆንም ጭምር ብለዋል ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ።የክርስቶስ ብርሃን ምስክሮች በመሆን ለዓለም የክርስቶስ ምስክሮች መሆናችን በግብር ማሳየት ይጠበቅብናል ብለዋል ፓፓ ፍራንሲስ ።ብርሃን የእግዚአብሔር ፀጋ ነው እና ብርሃኑ ለዓለም ብርሃን የሚሰጥ ብርሃን የደስታ እና የተስፋ ርሃን ያሉት ቅድስነታቸው ምእመናን የክርስቶስ ምስክሮች መሆናቸው ከቶ መዘነጋት የለባቸውም ብለዋል።በማያያዝ እስኪ ልጠይቃችሁ እንደጠፋ ላምባዲና ወይም እንደ በራ ላምባዲና ወይም ፋኖስ ለመኖር ትፈልጋላችሁ በማለት ምእመናንን ጠይቀዋል ምእመናንም ጮክ ብለው እንደ በራ ላምባዲና እንጂ ሲሉ መልሰዋል። በእግዚአብሔር የተሰጠን የብርሃን ጨረር ለሊሎች ማዳረስ የክርስትያን ተልእኮ ጥሪ እና ግዴታ እንደሆነ መዘንጋት የለብንም ብለዋል ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ። ነገ ወርሀ የካቲት 11 ቀን እኤአ ቤተ ክርስትያን ዓለም አቀፍ የህሙማን ቀን አክብራ እንደምትውል አስታውሰውም ምእመና ለታመሙ ሁሉ እንዲጸልዩ አሳሰብዋል ።ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በዚሁ ትናትና እሁድ በቅዱስ ጰጥሮስ አደባባይ ከምእመናን ጋር የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት በደገሙበት ግዜ በደቡባዊ በሩስያ ከተማ ሶቺ ላይ እየተካሄደ ያለውን 22ኛ ዓለም አቀፍ የክረምት ኦሊምፒክስ አስታውሰው ፡ የኦሎምፒክስ ውድድር የስፖርት ፌስታ እና የወዳጅነት ውድድር እንዲሆን ተመኝተዋል። በዚሁ የክረምት ኦሎምፒክ የሚወዳደሩ ክርስትያኖች በዓለም ላይ እንደሚበራ ብርሃን በመሆን እንዲያገለግሉ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ አመልክተዋል። በዚሁ ሩስታ ውስጥ እየተካሄደ ያለውን የኦሎምፒክ ውድድር ከ87 ሰባት ሀገራት የተውጣቱ ከ2.800 የሚበልጡ ስፖርተኛች ተሳታፊ መሆናቸው ያታወቃል ።የክረምት ኦሎምፒክስ በሩስያ ሲካሄድ ይህ የመጀመርያ ግዜ መሆኑ የሚታወስ ሲሆን ውድድሩ በከፍተኛ የጸጥታ ጥበቃ እና ቁጥጥር እየተካሄደ መሆኑ ከቦታ የደረሱ ዜናዎች ያመለክታሉ ። ይህ በዚህ እንዳለ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በቅዱስ ጰጥሮስ አደባባይ ከምእመናን ጋር መልእከ እግዚአብሔር ጸሎት በደገሙበት እና የኦሎምፒክ ስፖርት ውድድር ትኩረት በመስጠት ሲናገሩ ፡ በሩስያ ሶቺ ላይ እየተካሄደ ያለውን የኦሎምፒክ ላዘጋጁ እና ለስፖትረኞች ሁሉ በዚሁ አጋጣሚ ሰላምታዪ ለምስተላለፍ እወዳለሁ የስፖርት ትልቅ በዓል እና የወድጅነት የደስታ ውድድር እንዲሆን እመኛለሁ ነበር ያሉት ።








All the contents on this site are copyrighted ©.