2014-02-07 18:55:57

ቅዳሴ እና ስብከት ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ፡


ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ እንደተለመደው ሁሉ ትናትና በቅድስት ማርታ በሚገኘው ቤተ ጸሎት ሥርዓተ ቅዳሴ አሳርገዋል።በርካታ መነኲስያት መነኮሳን እና ምእመናን በዚሁ ቅዳሴ ተስታፋፊ መሆናቸው ሥርዓተ ቅዳሴውን የተከታተለ የቫቲካን የዜና ምንጭ አስታውቀዋል።ፓፓ ፍራንቸስኮ በዚሁ ሥርዓተ ቅዳሴ ባሰሙት ስብከት ፡ የሕልፈት ሚስጢር ትኩረት መስጠታቸው እና እግዚአብሔርን ሶውስቱ ምሕረቶች መጠየቅ ይገባል ካሉ በኃላ እነሱም ከቅድስት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ጋር ተሳስሮ ማለፍ ከተስፋ ጋር መሞት ወይም ማለፍ የምስክርነት ውርሻ ትቶ ማለፍ መሆናቸው አስገንዝበዋል። የዕለቱ ቃለ ቅዱስ ወንጌል በመጥቀስም የንጉስ ዳዊት ሕልፈት አመልክተው ንጉሱ ሕይወቱ ለህዝብ አገልግሎት መስጠቱ እስኮ ሕልፈቱ ድረስ የእግዚብሔር ህዝብ አጋር መሆኑ ማረጋገጡ ሐጢአተኛ መሆኑ ማመኑ እና ከአግዚአብሔር ምሕረት መለመኑ ሰብከዋል። ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ስብከታቸው በማያያዝ እንዲህ ሲሉ ሰብከዋል ፡ ንጉስ ዳዊት ሐጢአተኛ እዎ ከሀዲ ግን አይደለም ። እስከ መጨረሻ ሕልፈቱ ክህዝበ እግዚአብሔር ጋር ተጋርተዋል ነበር ያሉት ።ስብከታቸው በማያያዝም የተወደደዳችሁ ህዝበ ክርስትያን እኛም ከቤተ ክርስትያን ጋር ተቁራኝተን እንድናልፍ ምሕረት መጠየቅ ይጠበቅብናል ማለት እምነታችን አጠናክረን የኢየሱስ ክርስቶስ ትእዛዛትን አሟልተን ሚስጢራቱ ተቀብለን ምሕረቱ ጠይቀን ክርስትናዊ ካቶሊካዊ እሴታን ጠብቀን ማለፍ እና ወደ መንግስተ ሰማያቱ መድረስ ነው በማለት ስበከዋል። ይህ የማይገዛ የማይለወጥ የእግዚአብሔር ምሕረት የሚጠይቅ የክርስትና እሴት መሆኑ በማመልከት ሐጢአተኞች ልንሆን እንችላለን ከሀዲዎች ግን አይደለንም እና ብለዋል ቅድስነታቸው ። ንጉስ ዳዊት በሰላም ተረጋግቶ እና ተዝናንቶ ሞተ በእግዚአብሔር ምሕረት ተደረጎለት ወደ መንግስተ ሰማያት መጓዙ ስላወቀ እና ስለተረጋገጠ መሆኑ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ አክለው ሰብከዋል።ቅድስት ተረዛ ዘ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሕልፈት ስትቃረብ ከሞትዋ በኃላ የሚጠብቃት እያሰበች መጨናነቅ እንዳላት መጠቁምዋ እና ከሰማየ ሰማያት እብድ ነሽ እንዴ የሚጠብቅሽ ጨለማ የሚል ድምጽ መስማትዋ አትታ የዲያብሎስ ፈተና መሆኑ ተገነዘበች ብለዋል ፓፓ ፍራንሲስ ። ሕልፈታችን ሳይመጣ በእግዚአብሔር ያለንን ተስፋ እና ምሕረት ግዙፍ መሆን አለበት ያሉት ቅድስነታቸው የመጻኢ ዘለዓለማዊ ሕይወታችን ከአሁን ጀምረን መንከባከብ ይጠበቅብናል ብለዋል። ቅዱሳን የተውሉን የእመነት የተስፋ የመቀደስ እና የሰብአውነት የምሕረት ተቋዳሽ የምስጋና የጽድቅ ውርሻ ትተን ማለፍ ይጠበቅብናል በማለት ቅድስነታቸው ሰብከዋል ።








All the contents on this site are copyrighted ©.