2014-01-31 16:18:10

የቤተ ክርስቲያን የተራድኦ ማኅበር ‘ካሪታስ’ና የስደተኞች ጉዳይ የሚከታተለው ማኅበር ሰነድ


RealAudioMP3 በካሪታስ የሚጠራው የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የግብረ ሠናይ ማኅበርና የስደተኞች ጉዳይ የሚከታተለው ሚግራንተስ የተሰየመው ማኅበር ስደተኞች በኢጣሊያ በሚል ርእስ ሥር ባወጣው ሰነድ እንደሚያመለክተው በዓለም ተከስቶ ያለው የኤኮኖሚ ቀውስ የስደተኞች ጸአት የገታው ቢሆንም ቅሉ በኢጣሊያ የሚኖሩት የስደኞች ቁጥር ብዛት አምስት ሚሊዮን መድረሱ ያመለክታል።
እ.ኤ.አ. በ 2012 ዓ.ም. በዓለም አንጻር ሲታይ 3% የሚሸፍነው ከጠቅላላው የዓለም ሕዝብ ብዛት ውስጥ መሰደዱና በ 2013 ዓ.ም. ወደ ኢጣሊያ የገባው የስደተኛው ብዛት ከ2012 ዓ.ም. ጋር ሲነጻጸር በ 334 ሺሕ ከፍ ብሎ መገኘቱ የጠቆመው የጥናቱ ሰነድ አክሎ፣ ወደ አገራቸው የሚመለሱ ቁጥር ብዛት ከፍ እያለ መምጣቱንም ያመለክታል።
ሰነዱን ያጠናቀሩት ኦሊቨራ ፎርቲ ሰነዱን ለንባብ ለማብቃት በተካሄደው አውደ ጉባኤ ባሰሙት ንግግር እንዳመለከቱትም፦ “ስደተኛው በቀላሉ ለአደጋ የሚጋለጥ የኅብረተሰብ ክፍል ነው፣ በቅድሚያ በአገራቸው ያጋጠማቸውና ለስደት የዳረጋቸው ችግር ቀጥሎም በተሰደዱበት አገር የሚያጋጥማቸው የሥራ አጥነት የመኖሪያ ቤት አለ ማግኘት…ወዘተ የሚያስከትልባቸው ችግር በአገራቸው ያጋጥማቸው ከነበረው ችግር የተሻለ ባለ መሆኑም ወደ አገራቸው እንዲመለሱ እያደራጋቸው ነው በተለይ ደግሞ በድኽነት ምክንያት ለሚሰደዱት የሚመለከት ነው። ስለዚህ ይኽ በአገራቸው ያጋጠማቸው ችግር የተሻለ የሚያደርገውም በገቡበት የስደት አገር ያለው የስደተኛው ተዋህዶ ለመኖር ያስችላል የተባለው መመሪያ ብቃታ የሌለው መሆኑ የሚመሰክር ነው” ብለዋል።
የኢጣሊያ የውኅደት ጉዳይ ሚኒ. ሰሲሊየ ክየንገ በበኩላቸውም ባሰሙት ንግግር በሚቀጥሉት ቀናት በኢጣሊያ የዜግነት ጉዳይ የሚመለከተው ሕግ እንደሚታደስ አረጋግጠዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.