2014-01-31 16:06:00

የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ጉዳይ ለሮሊንግ ስቶን መጽሔት ምላሽ


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. ጥር 30 ቀን 2014 ዓ.ም. በቅድስት መንበር የዜናን ኅትመት ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ በቅርቡ በተባበሩት የአመሪካ መንግስታት የሚታተመው ሮሊንግ ስቶን የተሰየመው መጽሔት በቀዳሜ ገጹ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ምስል በማኖር በመጽሔቱ ስለ ቅዱስነታቸው ያሠፈረው ጽሑፍ በተመለከተ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፦ መጽሔቱ ስለ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ያሰፈረው ሓተታ በርግጥ በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃት ቅዱስነታቸው የሚሰጣቸው ትኵረት አቢይ መሆኑ የሚመስከር ነው፣ ሆኖም ግን መጽሔት በተለያዩ ጋዜጦችና መጽሔቶች በጠቅላላ በመገናኛ ብዙኃን ስለ ቅዱስ አባታችን እንደሚቀርበው ሁሉ ጥልቀት የሌለው ነው፣ ምክንያቱም እሳቸውን በመግለጥ እሳቸው ለሌሎች ብፁዓን ጳጳሳት ላለፉት አርእስተ ሊቃነ ጳጳሳት ሚዛን አድርጎ በመጠቀም ፍርድ ለመስጠት የተከተለው አሠራር ተቀባይነት የሌለው ነው። ስለዚህ ስለ ቅዱነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ያሠፈረው አሉታዊ ሓተታ ከእውነት የራቀ ነው፣ ይኽ ደግሞ መልካምና የተዋጣለት የመገናኛ ብዙኃን አገልግሎት ሊከተለው ከሚገባው አሠራርት ውጭ ሆኖ ነው የተገኘው፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የሚፈጽሙት በሁሉም ተደናቂነት የሚያገኘው የቅዱስ ጴጥሮሳዊ ተከታይ ሐዋርያዊ አገልግሎታቸው ላለፉት አርእስተ ሊቃነ ጳጳሳት ምስጋናና እንጂ ፍርድ አይደለም፣ የቤተ ክርስቲያን መልካም አገልግሎት ያለፉት አርእስተ ሊቃነ ጳጳሳት የሰጡት የቅዱስ ጴጥሮሳዊ ተከታይ ሐዋርያዊ አገልግሎት መሠረት ያለው ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.