2014-01-31 15:57:20

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ.፦ ክርስቶስን አለ ቤተ ክርስቲያን ማፍቅር ብሎ ለሁለት መከፋፈል ትርጉም አልቦ ተግባር ነው


RealAudioMP3 እንደ ተመለመደው ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ጥር 30 ቀን 2014 ዓ.ም. በአገረ ቫቲካን ቅድስት ማርታ ሕንጻ በሚገኘው ቤተ ጸሎት መሥዋዕተ ቅዳሴ አሳርገው፦ “ክርስቶስን አለ ቤተ ክርስቲያን ማፍቅር ብሎ ለሁለት መከፋፈል ትርጉም አልቦ ተግባር ነው” በሚል ሃሳብ ላይ ያነጣጠረ ስብከት ማሰማታቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
ቅዱስነታቸው የዕለቱ አንደኛ ምንባብ ላይ ተንተርሰው ከንጉሥ ዳዊት ተክለ ሰውነት በመንደርደር ንጉሥ ዳዊት አንድ ልጅ ከአባቱ እንደሚነጋገር ሁሉ እንዲህ ባለ መልኩ ከእግዚአብሔር ጋር ይናገራል፣ ምንም’ኳ ለሚያቀርበው ጥያቄ ከጌታ አሉታዊ መልስ ቢያገኝም የተሰጠው መልስ አሉታዊ ቢሆንም ቅሉ በደስታ ይቀበል ነበር፣ ይኽንን ሁነት ከዕለታዊ ሕይወት ጋር በማጣመር ከቤተ ክርስቲያን ጋር ያለን ግኑኝነት በቤተ ክርስቲያንና ከቤተ ክርስቲያን ጋር መሆናችን የሚያስተጋባ ተግባር መሆን እንዳለበት ሲያብራሩ፦ “ክርስቲያን በቤተ ክርስቲያን ጸጋ ጥምቀት ከተቀበለ በኋላ በገዛ እራሱ መንገድ የሚጓዝ አይደለም፣ ምክንያቱም ጸጋ ጥምቀት የቤተ ክርስቲያን አባል የሚያደርግ ነውና። ስለዚህ አንድ ክርስቲያን አለ ቤተ ክርስቲያን ለመረዳቱ ያዳግታል፣ ፈጽሞ የሚቻልም አይደለም፣ ር.ሊ.ጳ. ጳውሎስ ስድስተኛ ባንድ ወቅት እንዳሉት ክርስቶስ አለ ቤተ ክርስቲያን ማፍቅር ብሎ መከፋፈል ትርጉ አልቦ ተግባር ነው። ቤተ ክርስቲያን ሳይሆን ክርስቶስን ማዳመጥ ብሎ መናገር፣ ከክርስቶስ ጋር መሆን ነገር ግን ከቤተ ክርስቲያን ውጭ መሆን ተያይዞ የሚሄድ ምርጫ አይደለም፣ ክርስቶስ ከቤተ ክርስቲያን መነጠል የሚቻል አይደለም፣ እኛ ወንጌላዊው መልእክት የምንቀበለው በቤተ ክርስቲያን ከቤተ ክርስቲያን ነው። ቅድስናችን የምንከውነው በቤተ ክርስቲያን ነው፣ መንገዳችን በቤተ ክርስቲያን ነው፣ ከዚህ ውጭ ሁሉም ሕልም ነው፣ ስለዚህ ይህ አይነት ከፋፍሎ መኖርና መመልከት ትርጉም አልቦ ነው” እንዳሉ የገለጠው የቅድስት መንበር መግለጫ አክሎ፦ “ትህትና የሌለው ሰው የቤተ ክርስቲያን መሆኑ ሊሰማው አይችልም፣ ምክንያቱም በግሉ ለግሉ ደስ የሚያሰኘውን የሚሻ ነው። ዳዊት ጌታ ሆይ እኔ ማን ነኝ? ቤቴ ምንድር ነው? የመዳን እቅድ በእኔ የተጀመረ እኔ ከዚህ ዓለም በሞት ስለይ የሚደመደም ታሪክ አይደለም፣ እርሱ ይፈጥረናል የመራናል….ታሪክ ይቀጥላል፣ የቤት ክርስቲያን ታሪክ ከእኛ በፊት የጀመረ ነው፣ ከእኛ በኋላም ቀጣይነት ያለው ታሪክ ነው፣ እኛ የአንድ በጌታ መንገድ የሚራመድ አቢይ ሕዝብ ክፍል ነን” እንዳሉ አስታውቀዋል።
ቀጥለውም ታማኝነትና ተአዝዞ ባጣመረ ሃሳብ ላይ በመመርኮዝ ስብከታቸውን ሲቀጥሉ፦ “አዎ ታማኝነት ለቤተ ክርስቲያን፣ ለትምህርትዋ ታማኝ፣ ለተአምኖተ እምነት ታማኝ፣ ለመሠረተ ትምህርቷ ታማኝ፣ ለትምህርትዋ ለተአምኖተ እምነት ለመሠረታዊ ትምህርቷ ታማኝ መሆን ማለት አቅቦ መኖር ማለት ሲሆን፣ ስለዚህ ትህትናና ታማኝነት ይጠይቃል፣ ር.ሊ.ጳ. ጳውሎስ ስድስተኛ ወንጌላዊ መልእክት የምንቀበለው ጸጋ ነው በመሆኑ ጸጋውን ማስተላለፍ እንዳለብን የሚጠራ ጸጋ ነው፣ ጸጋ ለግል ጥቅም አይደለም፣ በታማኝነትና በትህትናን ማስተላለፍ፣ የእኛ ያልሆነውን እርሱም የኢየሱስ የሆነውን የተቀበልነው ወንጌል ማስተላለፍ ይጠበቅብናል፣ ደስ እንደሚያሰኘን ለመጠቀም ለተቀበልነው ወንጌል ገዢዎች የቤተ ክርስቲያን መሠረታዊ ትምህርት ገዢዎች አይደለንም” ካሉ በኋላ ከዚሁ ጋር በማያያዝ ሁሉም ስለ ቤተ ክርስቲያን እንዲጸልይ ክርስቲያናዊ በቤተ ክርስቲያን ኃላፊነት ተቀብለዋል። ለመላ ቤተ ክርስቲያን እንጸልይ፣ የቤተ ክርስቲያን አባላት መሆናችንን የቤተ ክርስቲያን መሆናችንን በጥልቅ ለመረዳት በምናደርገው ጉዞ ጌታ ይደግፈን በማለት ያስደመጡት ስብከት እንዳጠቃለሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።







All the contents on this site are copyrighted ©.