2014-01-29 16:50:06

ስብከተ ር.ሊ.ጳ. ፍራንሲስ ፡


ቅዱስ አባትችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ እንደ ዘውትር ትናንትና ጥዋት በቫቲካን በቅድስት ማርታ በሚገኘው ቤተ ጸሎት ሥርዓተ ቅዳሴ ባሳረጉበት ግዜ እና ባሰሙት ስብከት ከልብ የምናደርገው የምስጋና ጸሎት እምነታችንን ያጐለምሳል ሲሉ ሰብከዋል ። በዘተለምዶ የሚደረገው ጸሎት ፍረ አልባ ሆኖ ይቀራል ያለት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ስብከታቸው በማያዝ መፅሀፍ ቅዱስ ተትንተርሰው ጽላተ ሙሴ ወደ ቤቱ በተመለሰበት ግዜ ህዝበ እግዚአብሔር በደስታ መፈንደቁ እና መደነሱ አስታውሰዋል።ዳዊት በጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፊት ተደስቶ በሙሉ ኀይሉ ደስታውን መግለጹ ያመለኩቱት ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስስብሃት ለእግዚአብሔር ስንደግም ከልባችን የፈለቀ መሆን አለበት ደስታችን የመግለጽ ተክህሎችን ግዙፍ መሆን አለበት ብለዋል።የዳዊት ሚስት ሳራ ኢሳቅን እንደወለደች ዳዊት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደስታ አስደነሰኝ ሲል ሳራን መንገሩ ቅድስነታቸው መጽሐፍ ቅዱስን በመሞርኮስ አስገንዝበዋል።ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በርካታ ውሉደ ክህነት መነኲስያት እና መነኮሳን ተሳታፊ በሆኑበት በቅድስት ማርታ ቤተ ጸሎት ባሰሙት ስብከት በማያያዝ እንደሰበኩት ፡ ይህ በመንፈስ ቅዱስ ለሚታደሱ ነው እንጂ ክርስትያን ሁሉ አይመልከትም ይባል ይሆናል ያሉት ፓፓ ፍራንሲስ አይደለም የምስጋና ጸሎት ለሁሉም ክርስትያን ክርስትያናዊ ጸሎት ነው መልሱ ብለዋል።የእግዚአብሔር ትልቅነት ማመጐስ ማድነቅ አለብን ያሉት ፓፓ ፍራንሲስ እሱም ያዳምጠናል በእምነት እና ከልብ የተደረደ ሁሉ ይደርሰዋል ብለዋል። ጥያቄው የምስጋና ጸሎት ለማደረግ ያለንን መንፈሳዊ አቅም ምን ያህል ነው ፈጣሪያችን እግዚአብሔርን ከልብ እናመሰግናለን እንወድሳለን እናደንቃለን ነው ያሉት ፓፓ ፍራንሲስ ጸሎት ከቤተ ሰብ እንደሚጀምር እና ዘወትር መደረግ ያለበት የእምነታችን መሳርያ እንደሆነ አስገንዝበዋል ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ።








All the contents on this site are copyrighted ©.