2014-01-27 14:20:40

የቅዱስ ጳውሎስ መለወጥ ዓመታዊ በዓል


RealAudioMP3 ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ጥር 25 ቀን 2013 ዓ.ም. በላቲን ሥርዓ ለሚከበረው የቅዱስ ጳውሎስ መለወጥ ዓመታዊ በዓልና እንዲሁ ከዚሁ በዓል ጋር ተያይዞ የሚጠናቀቀው ዘንድሮ “ክርስቶስ የተከፋፈለ ነበርን?” ሲል ጳውሎስ ለቆሮንጦስ ማኅበረ ክርስቲያን ያቀረበው ጥያቄ ሥር ተመርቶ ስለ ክርስቲያኖች አንድነት የተካሄደው የጸሎት ሳምንት ምክንያት ሮማ ክፍለ ከተማ ፎሪ ለ ሙራ በሚገኘው የቅዱስ ጳውሎስ ቅዱስ አጽም ባረፈበት በቅዱስ ጳውሎስ ባሲሊካ የመጀመሪያ ጸሎት ዘ ሠርክ መምራታቸው ሲገለጥ፣ ቀኑን ምክንያት በማድረግ በቅዱስ ጳውሎስ ፎሪ ለ ሚራ የበነዲክቶስ ገዳም አበ እምኒየት አባ ኤድሙንድ ፖውር ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ ዘንድሮ የተካሄደው የክርስቲያኖች አንድነት የጸሎት ሳምንት መርህ ቃል ቅዱስ ጳውሎስ በቆሮንጦስ ማኅበረ ክርስቲያን መካከል ተከስቶ የነበረው የመከፋፈል ጉዳይ ማእከል በማድረግ ክርስቶስ የተከፋፈለ ነውን? በማለት ያቀረበው ጥያቄ ዛሬም መልስ የሚያሻው ጥያቄ ነው። የውሁድ አካል አንድነት ከሚያምነው ልብ ዘንድ የሚቀርብ ጥያቄ ነው። ስለዚህ ይኽ የክርስቶስ አንድነት በሚያምነው ልብ ካለ መከፋፈል ለማስወገድ መንቃት እንዳለበት የሚያሳስብ እምነት ነው። ዘንድሮ በዚህ ዓይነት መልእክት ሥር የክርስቲያኖች አንደት የጸሎት ሳምንት መከናወኑ ደስ የሚያሰኝ ነው ብለዋል።
ጳውሎስ ቀዳሚ ክርስቲያን የቲዮሎጊያ ሊቅ ነው። እርሱ ነው የመጀመሪያ የአንዲስ ኪዳን መጻሕፍት ጸሓፊ፣ በግብረ ሐዋርያት እንደ ተመለከተውም ጳውሎስ የክርስትና እምነት እንዲመሰክር በክርስቶስ የተጠራ ነው። ጳውሎስ የመጀመሪያው ክርስቲያን የቲዮሎጊያ ሊቅ ክርስቶስ ተቀብሎ የተለወጠበት ዓመታዊ በዓል በሚከበርበት ቀን ስለ ክርስቲያኖች አንድነት የሚደረገው የጸሎት ሳምንት እንዲጠናቀቅ ማድረጉ አለ ምክንያት አይደለም፣ ይኽ የለውጥ በዓል የጳውሎስ የግል መለወጥ በዓል የምናከብርበት ዕለት ብቻ ሳይሆን የእግዚአብሔር ቃል የምናከብርበት ይኽ ማለት ደግሞ የእግዚአብሔር ቃል ማክበር ማለት ሥጋ የሆነው ቃለ እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ማክበር ማለት ነው። የስቁል እየሱስና የተንሣው ክርስቶስ የሁሉም መሠረት ነው
በዚህ አጋጣሚም ይኽ በሮማ ፎሪ ለ ሙራ ቅዱስ ጳውሎስ ባዚሊካ የሚገኘው የበነዲክታውያን ገዳም ምሥረታ አንድ ሺሕ ሦስት መቶ ዓመት ማስቆጠሩንም ገልጠው፣ ስለ ክርስቲያኖች አንድነት ዘወትር የሚጸለይበት ቅድሱ ሥፍራ ነው በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.