2014-01-27 14:14:34

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ለክርስቲያኖች አንድነት የጸሎት ሳምንት መዝጊያ
“መከፋፈል እንቅፋት ነው። አብሮ መጓዝ ከወዲሁ አንድነት እንደ ማድረግ ነው”


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. ከጥር 18 ቀን እስከ ጥር 26 ቀን 2014 ዓ.ም. የላቲን ሥርዓት የምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የቅዱስ ጳውሎስ መለወጥ ዓመታዊ በዓል ከምታከብርበት ቀን ጋር ተያይዞ የሚጠናቀቀው የክርስቲያኖች አንድነት የጾሎት ሳምንት ምክንያት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ አንደኛው ጸሎተ ሠርክ መርተው፦ አብሮ መጓዝ ከገዛ እራሱ ከወዲሁ አንድነት ማረግ ይሆናል፣ ክርስቲያኖች በመካከላቸው ያለውን መከፋፈል ለማሸነፍ እንደሚችሉና በመንፈስ ቅዱስ ኃይል አማካኝነት አንድ እንዲሆኑ” በሚል ሃሳብ ዙሪያ ስብከት ማሰማቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ፓውሎ ኦንዳርዛ አስታወቁ።
የቅዱስ ጳውሎስ መለወጥ በዓል ምክንያት ቅዱስነታቸው በመሩት አንደኛው ጸሎት ሠርክ የተለያዩ አቢያተ ክርስቲያን ልኡካንና መንፈሳዊ መሪዎች መሳተፋቸው የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ኦንዳርዛ አያይዘው፣ ይኽ ክርስቶስ ሊከፋፈል አይችልም፣ በክርስቲያኖች መካከል ያለው ልዩነት እንቀፋትና በዚሁ መከፋፈልም ሁሉም ማኅበረ ክርስቲያን የተጎዳ መሆኑ ቅዱስ አባታችን በማብራራት አንድነት ዘወትር በወድማማችነት መንፈስ በመመራት ወደ አንድነት መጓዝ ማለት መሆኑና ለአንድነት ታልሞ የሚካሄደው የጋራው ጉዞ ለገዛ እራሱ አንድነት ሲሆን፣ ግጭት አለ መግባባት ማሸነፍና የታረቀ ብዙኅነትና ልዩነት የመንፈስ ቅዱስ ስጦት መሆኑ ቅዱስ አባታችን ገልጠው፦ “እኛ በጋራ አብረን እስካልተጓዝን ድረስ፣ እርስ በእርሳችን በጸሎት እስካልተሳሰብን ድረስ፣ ለሕዝበ እግዚአብሔር የሚያስፈልገው ለማረጋገጥ በመተባበር በጋራ እስካልተጓዝን ድረስ አንድነት ፈጽሞ ይረጋገጣል ብሎ ማሰብና መናገር አይቻልም። በዚህ ለአድነት በሚደረገው ጉዞ ጌታ ሁላችንን ነው የሚጠብቀን ሁላችንንም ነው የሚሸኘው። አብሮን ነው የሚጓዘው” እንዳሉ አስታውቀዋል።
በቤተ ክርስቲያን የተከስተው መከፋፈል እንደ ባህርያዊና አልቀሬ ነው ብሎ መመልከቱ በእውነቱ ስህተት መሆኑ ቅዱስ አባታችን ሲያስረዱ፦ “እዚህ በጋራ ተገናኘተን አብረን ስንጸልይ ክርስቶስ ሊከፋፈል እንደማይችል እንገነዘባለን፣ እርሱ ወደ ገዛ እራሱ ሊማርከን ወደ እርሱ የልብ ፍላጎትና ስሜት ሊስበን እርሱ በአባቱ እጅ ዘንድ አለ ምንም መጠራጠር በሙላት ወደ ኖረው መተማመን ይማርከናል። ለሰብአዊ ፍቅር አለ ምንም ማመንታት ሁለ መናውን ስለ ፍቅር ብሎ ወደ ሰዋበት እውነት ይስበናል። እርሱ ብቻ ነው የአንድነት መሠረት ምክንያት እና አንቀሳቃሽ። ስለዚህ እዚህ ስለ አቢያተ ክርስቲያን አንድነት ለመጸለይ አብረን መገናኘታችን መከፋፈልና ልዩነት ለማንኛውም ማሕበራዊ ሕይወት እንደ ባህርያዊ አልቀሬ ክስተት እድርጎ መመልከት አይገባም። በውስጣችን ያለው መከፋፈል ምስክርነት ልሰጥበት ለተጠራንበት የጌታ አካልን እንጎዳለን እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ኦንዳርዛ አስታወቁ።
ቅዱስ ጳውሎስ ለቆሮንጦስ ማኅበርሰብ በመመልከት እኔ የጳውሎስ እኔ የኬፋ እኔ የአፖሎ ነኝ እኔ የክርስቶስ ነኝ በማለት ተከስቶ የነበረው መከፋፈል በመግለጥ ክርስቶስ የተከፋፈለ እንዳልሆነ መሠረት በማድረግ፦ ለአንድነት በማሰብ የፈጸምነውን የጋራ ጉዞ እውን እንዲሆን ላደረገው ጌታ ምስጋና ይገባዋል። ዛሬ ለአንድነት የምናደርገው ጉዞ አለ ምንም ችግርና ልዩነት የሚካሄድ እንዳልሆነ ለሁሉም ግልጽ ነው፣ ስለዚህ ሁላችን ክርስቶስ በፈለገው በአንድነት ጎዳና ለመራመድ እንድንችል በእርሱ ስሜትና ፍላጎት የተሞላን እንድንሆን ይደግፈን ዘንድ እንለምነው” ካሉ በኋላ የተለያዩ አቢያተ ክርስቲያን ለአንድነት የሚያደርጉት ጎዞ በማነቃቃት ሐዋርያዊ አገልግሎት ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ 23ኛ ር.ሊ.ጳ. ጳውሎስ ስድስተኛ ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሓንስ ጳውሎስ ሁለተኛን በማስታወስ፦ “እነዚህ አርእስተ ሊቃነ ጳጳሳት ስለ አንድነት የሚድረገው የጋራው ጉዞ ያለው አስፍፈላጊነት እጅግ በማሳሰብ እንዲነቃቃት በማድረግ የፈጸሙት ተግባር በማስታወስ፣ ይኽ ተግባር የሮማ ጳጳስ ተቀዳሚ መሆኑና መሆንም እንዳለበት በማስታወስ፣ ስለዚህ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሐዋርያዊ ተልእኮ በሁሉም ክርስቲያኖች መካከል የሚደረገው የአንድነት ጉዞ ውጭ ለመረዳት የሚቻል ብቻ ሳይሆን ተልእኮው ትርጉም ያጣል” ብለው ለአንድነት የሚደረገው ጉዞ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ጥሪ በሁሉም ዘንድ ግንዛቤ እንዲያገኝ ማድረጉንም አስታውሰው፣ ለአንድነት በሚደረገው ጉዞ ዘወትር ካለ መታከት አብረን እንራድመድ በማሳሰብ ያስደትመጡት ስብከት እንዳጠቃለሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ኦንዳርዛ አመለከቱ።








All the contents on this site are copyrighted ©.