2014-01-24 16:08:03

ዳቮስ
ብፁዕ ካርዲናል ኦናየካን፦ ቅዱስ አባትችን የኤኮኖሚ ማእከል የሰው ልጅ ክብር መሆን እንዳለበት ያሳስባሉ


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. ጥር 25 ቀን 2014 ዓ.ም. ለሚጠናቀቀው በስዊዘርላንድ ዳቮስ ከተማ የተለያዩ አገሮች መራሔ መንግሥታት ርእሰ ብሔሮችና ልኡካንና የኤኮኖሚ ሊቃውንት የኤክኖሚ ባለ ሃብቶች የተለያዩ ሃይማኖት መሪዎች በጠቅላላ 2,500 ልኡካን በማሳተፍ በመካሄድ ላይ ወዳለው ዓለም አቀፍ የኤክኖሚ ጉባኤ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ያስተላለፉት መልእክት በማስደገፍ በጉባኤ በመሳትፍ ላይ የሚገኙት የናይጀሪያ ርእሰ ከተማ አቡጃን ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ጆን ኦናየካን በስልክ ከቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኛ ደቦራ ዶኒኒ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ በቅድሚያ የዚህ ዓለም አቀፍ የኤኮኖሚ ጉባኤ መሥራችና የጉባኤው ጠቅላይ ዝግጅት ዋና አስተዳዳሪ ክላውስ ሽዋብ በጳጳሳዊ የፍትህና ሰላም ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ቱርክሶን የተነበበው የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ መልእክት በጉባኤው መክፈቻ እንዲነበብ ማድረጋቸው በእውነቱ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በዓለም ያላቸው ተደማጭነት የሚመሰክር መሆኑ ገልጠጠው፣ መልእክቱ ተነቦ ከመጀመሪያው ቀን ስብሰባ ፍጻሜ በኋላ ብዙ የኤኮኖሚ ሊቃውንት የተለያዩ አገር መሪዎች የተደመጠው የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. መልእክት ምክንያት ምስጋናቸውን እንደገለጡላቸውና የዓለም ሃብት በመቆጣጠር ገዢ ከመሆን ለሰው ልጅ አገልግሎት መዋል እንዳለበት የሚል ቅዱስ አባታችን ያሰመሩበት ሃሳብ በተለያዩ አካላት በተለያዩ የዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኃን ክፍ ብሎ እየተስተጋባ ነው ብለዋል።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በመልእክታቸው በቅድሚያ ድኻ ሃብታ ጥቁር ነጭ የሚለው የእጋጣሚ ልዩነት ግምት ሳይሰጠው የስው ልጅ በሰብአዊ ክብርና መብት እኩል መሆኑ በማበከር። ስለዚህ የሰው ልጅ በእግዚአብሔር አርአያና አምሳያ ተፈጥረዋል በሚለው እውነት ላይ የጸና እኩልነት የሚያሳስብ መልእክት ነው። በሁለተኛ ደረጃ የሰው ልጅ የጋራ ጥቅም የሚመለከት ነው። ስለዚህ በርሃብና በጤና ጥበቃ አገልግሎት እጦት በጦርነት ወዘተ ምክንያት የሚከሰተው ስቃይ ዝም ብሎ መታየት የሌለበት ጉዳይ መሆኑ የሚገልጥ ነው። ይኽ ማለት ደግሞ የሰብአዊ መብትና ክብር ጥበቃ በሁሉም ሥፍራ በሁሉም ደረጃ መከበር እንዳለበት የሚያሳስብ፣ መልእክት ነው ካሉ በኋላ ይኽ ጉባኤ የሰው ልጅ የተሟላ አድማስ እርሱም ሰብአዊው መንፈሳዊው ባህርይ የሚያነቃቃ እንዲሆን ተስፋ አደርጋለሁ በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.