2014-01-24 15:57:51

የመገናኛ ብዙሃን ለግኑኝነት ባህል አገልግሎት


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. ጥር 23 ቀን 2014 ዓ.ም. በቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ሕንጻ በሚገኘው የጉባኤ አዳራሽ እ.ኤ.አ. ሰነ 1 ቀን 2014 ዓ.ም. ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኃን ቀን ምክንያት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የሚያስተላልፉት መልእክት የመገናኛ ብዙኃን ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ክላውዲዮ ማሪያ ቸሊ፣ በሚላኖ ካቶሊካዊ መንበረ ጥበብ የሥነ ድርሰትና ሥነ ጽሑፍ እንዲሁም የፍልስፍና መምህር ኪያራ ጃካርዲና የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ ንግግር ባስደመጡበት መድረክ በይፋ ለንባብ መብቃቱ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ጃዳ አኵይላኒ አመለከቱ።
ይኽ ዘንድሮ ሰኔ 1 ቀን 2014 ዓ.ም. “የመገናኛ ብዙኃን ለግኑኝነት ባህል አገልግሎት” በሚል ርእስ ሥር ተመርቶ ለሚካሄደው ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኃን ቀን ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የሚያስተላልፉት ቀዳሜ መልእክት፣ ቅዱስነታቸው በብራዚል በተካሄደው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ምክንያት ተገኝተው በዚያኑ አጋጣሚ ከመላ ላቲን አመሪካና ካራይቢ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ጋር ተገናኝተው ከሰጡት ሥልጣናዊ ምዕዳን እንዲሁም ወንጌላዊ ሃሴት ሐዋርያዊ ምዕዳን ላይ ያተኮረ መሆኑ ብፁዕ አቡና ቸሊ ባሰሙት ንግግር ጠቅሰው፣ “የመገናኛ ብዙኃን መረጃ ወይንም የማስታወቂያ ግኑኝነት ብቻ የሚል ሳይሆን ጥልቅ ሰብአዊነት የተካነው እርሱም መቀራረብ የሚል እሴት የሚኖርበት መሆን እዳለበት ማለትም በመገናኛ ብዙኃን አማካኝነት ለሌላው ቅርብ ለመሆን የሚያነቃቃ ያለው ተገቢነት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ባስተላለፉት መልእክት የሉቃስ ወንጌል የመልካም ሳምራዊው አብነት ጠቅሰው በመተንተን፣ ቅርብ መሆን ብቻ ሳይሆን የሌላው ስቃይና ችግር የገዛ እራስ ማድረግ ማለት መሆኑ በማስረዳት፣ የመገናኛ ብዙኃን ለመቀራረብና ሰዎች የአንድ እግዚአብሔር ልጆች መሆናቸው ወንድማማችነታችን የሚረጋገጥበት መሆኑ አንዳሰመሩበት” ብፁዕነታቸው ባሰሙት ንግግር ገልጠው፣ በዚሁ አጋጣሚም ቅዱስነታቸው ልሂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛን በማስታወስም “ችግሩ ተዛማችነት ባህል ያመጣው እንዳሻኝ መኖር ከሚለው አስተሳሰብና ልምዶች ርቆ የመገናኛ ብዙኃን በዕደ ጥበብ የተካነ ብቻ ሳይሆን ሰብአዊነት አድማስ ያለው ከሌላው ጋር ለመወያየት የሚደገፍ መሆን አለበት፣ መወያየት ማለት መግባባት፣ ሌላውን ለማዳመጥ ገዛ እራስ ክፍት ማድረግ፣ በገዛ እራስ ሃሳብ ላይ ግትር ብሎ መቅረት ሳይሆን የሌላውን አስተሳሰብና ባህል ማዳመጥ ማለት ነው። በመሆኑም ተዛማጅ ባህል እርሱም ወንጌል ወይንም እምነት በተዛማጅ ባህል መግለጥ ማለት ሳይሆን እኔ ወንጌልና እምነት እንዴት መኖር እንዳለብኝ ያለውን ጥሪ ላደጋ የሚያጋልጥ መሆኑ ቅዱስ አባታችን በሚያስትላልፉት መልእክት አብራርተዉታል” ሲሉ፣ ፕሮፈሰር ኪያራ ጃካርዲ በበኩላቸውም፦ “ድረ ገጽ የመገናኘት እርሱም ፊት ለፊት ከሌላው ጋር የመገናኘት የሰው ልጅ ተገናኝ ባህርዩን የሚተካ ማለት ሳይሆን፣ በድረ ገጽ አማካኝነት ሰብአዊው ተገናኝነት ባህርይ የሚከበርበት መሆን እድነሚገባው ቅዱስ አባታችን አስምረዉበታል፣ ስለዚህ ሥነ ሰብእ አድማስ ማእክል የሚያደርግ ማለት ነው። በሁለተኛ ደረጃም የመገናኛ ብዙኃን የተጨባጭ ሁነት ይዞታ የሚተላለፍበት ብቻ ሳይሆን በሰዎች መካከል ያለው መራራቅ የሚያስወግድ ሰዎችን የሚያቀራርብ መሆን አለበት ስለዚህ ጉርብትና የሚያረጋግጥ መሆን እንዳለበት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በመልእክታቸው አስምረዉበታል፣ ክስተቶችን ቀድሞ ማሳወቅ የመገናኝ ብዙኃን ውደራ ሳይሆን ቀድሞ ዜናውን የሰጠ ያስተላለፈ ተብሎ በዋቢነት ለመጠቀስ ሳይሆን፣ ቀድሞ ማወቅ ቀድሞ ለሌላው ቅርብ የመሆን ኃላፊነት የሚል መሆኑ በመልክቱ በጥልቀት ተብራርቶ ይገኛል” እንዳሉ ልእክት ጋዜጠኛ አኵይላኒ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.