2014-01-24 16:15:59

ብፁዕ አቡነ ቶማሲ፦ የግጭትና ጦርነት ብቸኛው መፍትሔ ውይይት ነው


RealAudioMP3 በሶሪያ ያለው ግጭት ሰላማዊ መፍትሔ እንዲያገኝ ለማድረግ ታልሞ በተካሄደበት ዓለም አቀፍ የሰላም የድርድር መድረክ የተሳተፉት የቅድስት መንበር ልኡካንን የመሩት በተባበሩት መንግሥታት የቅድስት መንበር ቋሚ ታዛቢ ብፁዕ አቡነ ሲልቫኖ ማሪያ ቶማሲ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር በስልክ ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ በስዊዘርላንድ ጀነቭ ሁለተኛ በሚል መጠሪያ የተካሄደው ስለ ሶሪያ ሰላም የተደራደረው ጉባኤ በሶሪያ ብቻ ሳይሆን ለመካከለኛው ምስራቅ አቢይ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ገልጠው የተካሄደው የሰላም ድርድር አወንታዊ ነበር በማለት ገልጠዉታል።
በዚህ ሁለተኛ ጂነቭ የሚል መጠሪያ በተሰጠው በሶሪያ ያለው ግጭት ሰላማዊ ዕልባት እንዲያገኝ ብሎም በመካከለኛው ምስራቅ ሰላም ለማረጋገጥ አልሞ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላይ ዋና ጸሃፊ ባን ኪ ሙን መሪነት ሥር አርባ አገሮች የተባበሩት መንግሥታት የውጭ ጉዳይ ዋና ጸሓፊ ከርዪና የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒ. ላቭሮቭ ያካተተ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቻቸው አማካኝነት በማሳተፍ በተካሄደው የሰላም ጉባኤ ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ባንድ ተግባራዊና በቀጥታ እግብር ላይ መዋል የሚችል መፍትሄ እንዲከወን የሚል የጽኑ ጥሪ መልእክት በቀጥታ ለአሳድ መንግሥት ተጠሪና ለተቃዋሚው ኃይል ልኡካን የቀረበበት መድረክ መሆኑ ገልጠው፣ ምንም’ኳ የተለያዩ አገሮች የሶሪያ ጉዳይ በተመለከተ የተለያየ ሃሳብ ያላቸው ቢሆንም ቅሉ ግጭቱ አስቸኳይ መፍትሔ የሚያሻው መሆኑ የተመሰከረበት የሰላም ውይይት ነበር ብለዋል።
የሶሪያ መንግሥትና ተቃዋሚው ኃይል እፊታችን አርብ ፊት ለፊት ተገናኝተው ለመወያየት ያላቸው መልካም ፍላጎት ያረጋገጠ በእውነቱ አቢይ ውጤት የተረጋገጠበት ጉባኤ ነበር ለማለት ይቻላል በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.