2014-01-24 16:11:12

ብፁዕ አቡነ ማምበርቲ፦ ቅድስት መንበርና የተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት በዓለም ለፍትሕና ሰላም መስፋፋት ትብብራቸውን እንዲያጎለብቱ


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. ጥር 10 ቀን 30ኛውን ዓመቱን ያከበረውው የቅድስት መንበርና የተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ክሌአዊ ግኑኝነት ምክንያት በቅድስት መንበር የተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ሉኡከ መንግሥት በካንቸለሪያ ሕንፃ የሁለቱ አገሮች ግኑኝነት የሚያወሳ የስእላዊ መግለጫ ትርኢት ማሰናዳታቸው ሲገለጥ፣ ትርኢቱ መርቆ ለመክፈት በተካሄደው ሥነ ሥርዓት የቅድስት መንበር የውጭ ግኑኝነት ጉዳይ ዋና ጸሓፊ ብፁዕ አቡነ ዶመኒክ ማምበርቲ መሳተፋቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጂሶቲ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችለዋል።
የሁለቱ አገሮች ግኑኝነት የሚያወሳው ስዕላዊ ትርኢት የር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሓንስ 23ኛ የርእሰ ብሔር አይዘንሀውር ግኑኝነት፣ ር.ሊ.ጳ. ጳውሎስ ስድስተስኛ ለመጀመሪያ ጊዜ አገረ ቫቲካን እንዲጎበኙ ጥሪ ካቀረቡላቸው ከርእሰ ብሔር ከነዲ፣ የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ብፁዕ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ከርእሰ ብሔር ሮናልድ ሬጋን ጋር ያካሄዱት ግኑኝነት ያጠቃለለ ሲሆን፣ የቅዱስነታቸው ልሂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ከርእሰ ብሔር ቡሽና እንዲሁም ከርእሰ ብሔር ኦባማ ጋር የተካሄደው ግኑኘንት ያካተተ መሆኑ ጂሶቲ ገልጠው፣ በቅድስት መንበር ለተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ልኡከ መንግሥት ከንዝ ሃከት በመክፈቻው ሥነ ሥርዓት ባሰሙት ንግግር፦ የሁለቱ አገሮች የጋራው ግኑኝነት ጅማሬ ዝክረ 30ኛው ዓመት ማክበር በሁለቱ አገሮች መካከል ያለው የጠበቀው ወዳጅነት መመስከር ማለት ነው። የወቅቱ የተባበሩት መንግሥታት አመሪካ የውጭ ግኑኝነት ዋና ጸሓፍ ከርይ በቅርቡ በቅድስት መንበር ይፋዊ ጉብኝት ፈጽመው ከቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ አቡነ ፓሮሊኒ ጋር መገናኘታቸውና እ.ኤ.አ. መጋቢት 27 ቀን 2014 ዓ.ም. የርእሰ ብሔር ብራክ ኦባማ በቅድስት መንበር ጉብኝት በማካሄድ ከር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ጋር ለመገናኘት የተወሰነው መርሃ ግብር አለ። ይኽ ደግሞ የሁለቱ አገሮች ግኑኝነት ቀጣይና ጥብቅ መሆኑ የሚመስክር ነው” ሲሉ ብፁዕ አቡነ ማምበርቲ በበኵላቸው ባስደመጡት ንግግር፦ “የሁለቱ አገሮች ወዳጅነትና ግኑኝነት እንዲሁም ትብብር በአገሮች መካከል ያለው ግኑኝነት ቤተሰብአዊነት መልእክት እንዲኖረው በማድረግ ጥረት ይኽም የዓለም ሕዝብ አንድ ቤተሰብ መሆኑ የሚመሰክር ለማድረግና በዓለም ሰላም ፍትህ ወድማማችነት በማነጽ ረገድ ያላቸው ትብብር ሊጎለብት ይገባዋል” እንዳሉ ልኡክ ጋዜጠኛ ጂሶቲ አስታወቁ።
በመጨረሻም በቅድስት መንበር ለተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ልኡከ መንግሥት ተልእኮ በአገረ ቫቲካን ለሚከታተለው ጉዳይ ተጠሪ ማሪዮ መስኵይታ፦ “የሁለቱ አገሮች ግኑኝነት ዝክረ 30ኛው ዓመት ማክበር የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን ሚና በዓለም አቢይ መሆኑ የሚመሰክርና በቀረበው ስዕላዊ ትርኢት፣ ሮሳ ፓርክ ማርቲን ሉተር ኪንግ የተለያዩ የተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት የባህል አካላት ሊቃውንት የሚያስታውስ ባለፉት ዓመታት የሁለቱ አገሮች ግኑኝነት ይፋዊ ጉብኝቶች የሚተርክ ነው። ባጠቃላይ ቅድስት መንበርና ኵላዊት ቤተ ክርስቲያን በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ያላት ሚና የሚተርክ ነው” እንዳሉ ልኡክ ጋዜጠኛ ጂሶቲ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.