2014-01-23 11:53:35

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ለዓለም አቀፍ የዳቮስ የኤኮኖሚ ጉባኤ መልእክት


ለፕሮፎሰር ክላውስ ሽዋብ
ለዓለም አቀፍ የኤኮኖሚ ጉባኤ አስፈጻሚ ምክር ቤት ሊቀ መንበር
በየዓመቱ እ.ኤ.አ. በጥር ወር ማገባደጃ ሳምንት በዳቮስ ኮስተርስ በሚካሄደው ዓለም አቀፍ የኤኮኖሚ ጉባኤ ዘንድሮ በ2014 ዓ.ም. በሚካሄደው ስብሰባ ተገኝቼ ንግግር አሰማ ዘንድ የጉባኤው አስፈጻሚ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ላቀረቡልኝ ጥሪ ከልብ ሕያው ምስጋናዮን አቀርባለሁኝ። በነዚህ ባለፉት ከመጨረሻዎች ዓመታት ወዲህ መላ ዓለምን የነካው ተከስቶ ያለው የኤኮኖሚ ቀውስ መንስኤው ለይቶ በጥልቀት ለማስተንተን የሚካሄደው ስብሰባ ጥሩ አጋጣሚ እንደሚሆን እተማመናለሁ። ስለዚሁ ለሚካሄደው ውይይትና እጅግ አስፈላጊነት ላለው ክንዋኔዎቹ ሊያጎለብት በተስፋ አንዳንድ አስፈላጊ ትክረት ሊሰጥበት ይችላል ብየ እማምንበት ሃሳብ ለማቅረብ እሻለሁ።
የምንኖርበት ጊዜ እጅግ ዓቢይ ግምት ሊሰጥበት በሚገባው በተለያዩ ዘርፎች እድገት የሚያሰጥ በሰው ልጅ ሕይወት አቢይ ተጽእኖ በሚኖረው ጎልተው በሚታዩት ለውጦች ባህርይ የሚለይ ነው። እርግጥ ነው ለሰው ልጅ መልካምነት ለምሳሌ “በጤና ጥበቃ በሕንጸትና በመገናኛ ብዙኃን ዘርፍ እድገትና የተደረሰው ብልጽግና ሊመሰገን ይገባዋል” (ወንጌላዊ ሃሴት, 52) በሌላው ረገድ የሰው ልጅ ተግባራዊ ዘርፍ ያስገኘው እድገት ጭምር ሊጠቀስ የሚቻል ነው። ስለዚህ ወቅታዊው የኤኮኖሚ አውታሮች የሚከሰቱት መዋዕለ ለውጦች ዘንድ ሰፊና ጥልቅ ሃብት ለሆነው የሰው ልጅ ብልሃተኛነትና አስተዋይነትን በማነቃቃት ለእድገት ያለው መሠረታዊ ሚና እውቅና መስጠት ያስፈላጋል።
እስካሁን ድረስ ብዛት ያላቸው ሰዎች ከድኽነት ለማላቀቅ መቻሉ የሚያመለክቱ የተረጋገጡና የተጨበጡ ግቦች እንዳሉ የማይታበል ቢሆንም ቅሉ እየተስፋፋ ላለው ማኅበራዊ ልዩነት ማጋለጡ በቀላሉ የሚገመት አይደለም። ለዚህም ነው ብዛት ላለው ለዘመኑ ሕዝብ እጅግ ለከፋ ፍጻሜ የማጋለጥ ምክንያት በመሆን እጅግ ባልተረጋገጠ ኑሮ እንዲኖር እያደረገ ያለው።
በዚህ ጉባኤ የሰው ልጅ ሰብአዊ መብትና ክብር ብሎም ለማሕበራዊ የጋራ ጥቅም ለይቶ አቢይ ግምት ሊሰጥ የሚችል አቀራረብ ላይ ትኵረት እንዲደረግ እንዲሁም የተለያዩ የፖለቲካና የኤኮኖሚ ዘርፎች በዚሁ ጉዳይ ላይ እንዲያተኩር ያለኝን ምኞት አገልጣለሁ። ስለዚህ እማስተላልፈው መልእክት የኤኮኖሚውና የፖለቲካው ጉዳይ የሚከተለው ምርጫዎች ላይ ምልክት ጥሎ የሚያልፍ እንዲሆን ያለው አንገብጋቢነት በአልፎ አልፎ ሌሎች የሚቀርቡት ንግግሮችን የሚያሟላ ተጨማሪ ንግግር ሆኖ የሚቀር ተመስሎ ሊታይ ይችል ይሆናል። በዚህ ዘርፍ አቢይ ሥልጣን ያላቸው ሁሉ በሌሎች ላይ በተለይ ደግሞ በቀላሉ ሊጎዱ ለሚችሉ ጠበቃና ተከላካይ በሌላቸው የኅብረተስብ ክፍል ፊት አቢይ ኃላፊነት አላቸው። ብዙውን ጊዜ በክኖ የሚቀር የተትረፈረፈ በቂ የምግብ ሃብት እያለ ነገር ግን በየዕለቱ በእርሃብ በብዙ ሺሕ የሚገመት ሕዝብ ለሞት ሲዳረግ ታግሶ ማለፉና ዝም ብሎ ማየቱ የማይቻል ነው። በተመሳሳይ መልኩም በመጠኑ ከሰው ልጅ ሕይወት ክብር ጋር የተስተካከለ ሁኔታ ለመሻት ኢሰብአዊነት በተሞላው በስደት ጉዞ ሞት እንደሚያጋጥማቸው ግብዛቤው እያላቸው የሚሰደዱት በቁጥር እጅግ ብዙ የሆኑት ተፈናቃይና ስደተኞች መስተንግዶ የማያግኙ በቸልተኝነት መመልከቱ የማይቻል ነው። ይኸንን ሁኔታ ለመግለጥ የተጠቀምኩበት ቃል ኃይለኛ ከባድ መከራ የሚያወሳ መሆኑ ይገባኛል፣ ያም ሆኖ ይህ ግን ተጋርጦ ብቻ ሳይሆን ተገቢ ተደማጭነትና መስተንግዶ እንዲያገኙ የማነቃቃት ብቃት ያላቸውና ሁኔታው ተጋርጦ መሆኑም ጭምር ለማበከር ያለሙ ቃላት ናቸው። በርግጥ እነዚህ በጥበባቸውና በግብረአዊ ሞያ ብቃታቸው አማካኝነት ሕዳኤ ለማረጋገጥና የብዙ ሰዎች የተደልደለ ኑሮ ለማመቻቸት የቻሉ ሁሉ ብቃታቸው በድኽነት ጫንቃ ሥር ለሚገኙት አገልግሎት በማዋል ረገድም አቢይ አስተዋጽኦ ሊያበረክቱ ይችላሉ።
በጥልቀት የታደሰ የሚስፋፋ የኃላፊነት ስሜት በሁሉም ዘንድ እንዲኖር ያስፈላጋል። “የኤኮኖሚ ባለ ሃብት መሆን ክቡር ምያ ነው፣ በመሆኑም የአንድ የኤኮኖሚ ባለ ሃብት ጥሪ በአንድ አቢይና ሰፊ በሆነው በሕይወት ትርጉም ይጠየቅ ዘንድ መፍቀድ ነው” (ወንጌላዊ ሃሴት, 203)። ይኽ ደግሞ ብዙ ወንዶችና ሴቶች ለማኅበራዊ ጥቅምና የዓለም ሃብት ለሁሉም ሰዎች ጥቅም እንዲውል በሚያደርግ እጅግ ውጤታማ በሆነው መንገድ እንዲያገለግሉ የሚያግዝ ነው። ያም ሆኖ ይህ የተስተካከለ እኵልነት ያስከተለ እድገት የኤኮኖሚ እድገት ብቻ የሚመለከት ሳይሆን ለገዛ እርሱ የኤኮኖሚ እድገትንም የሚያቅፍ በመሆኑም ከዛም በላይ ነው። ስለዚህ የተስተካከለ የእድገት እኵልነት “የሰው ልጅ መሆናዊ ባሻገር ያለው አድማስ የሚጠይቀው ነው። (በነዲክቶስ 16ኛ ‘ፍቅር በሓቅ’, 11) ምክንያቱም አለ የዘለዓለማዊ ሕይወት አስተያየት በዚህ ዓለም ሰብአዊ እድገት እስትንፋስ የሌለው ሆኖ ነው የሚቀረው (ፍቅር በሓቅ…)። በተመሳሳይ መልኩም እኵል የተስተካከለ የሃብት ክፍፍልና የሥራ ዕድል መፍጠር ድኾችን በተረጂነት ከመደገፍ የሚያላቅቅ የተሟላ እድገት የሚያነቃቃ ውሳኔ የሚጠይቀውም ነው።
ከመሆን ባሻገር፣ ከወደር ባሻገር ክፍት መሆን በኤኮኖሚ ተግባሮችና በቁጠባ ላይ በሰብአዊነት እይታ መሠረት አስተያየትና ፍርድ ለመስጠት የሚችል አዲስ ፖለቲካዊና የኤኮኖሚ አውታር ባለ ሃብት መሆን ቅርጽ እንዲይዝ የሚያደርግ እንደሚሆንም አልጠራጠርም። ዓለም አቀፍ የኤኮኖሚ ባለ ሃብቶች ማኅበረሰብ ቅንነነት ሰብአዊ ምሉእነት በተካኑ ተግባርና ሥራቸው ሁሉ በላቁ አበይት ክብሮች ዘንድ የተመራና የተነቃቃ እርሱም ፍትህ ለጋስነት የሰብአዊ ቤተሰብ እውነተኛ እድገት እጅግ ግድ በሚላቸው ሰዎች ላይ እማኔ ሊኖረው ይገባል። በዚህ አቢይ ግብረ ገባዊና ሰብአዊ ሃብት መሠረት በቆራጥነትና በአርቆ አስተዋይነት ተጋርጦ የሆነውን ሁሉ ትጋፈጡ ዘንድ አደራ እላለሁ። ሁነኛው ልዩ የሥነ ምርምርና የማንኛውም የግብረአዊ ሞያ ሁነት ካለ መዘንጋትና ችላ ካለ ማለት ሃብት ለሚያስተዳድረው ሳይሆን ለሰብአዊ አገልግሎት እንዲውል ታደርጉ ዘንድ አጠይቃለሁ።
ክብሩ ሊቀ መንበርና ውድ ጓደኞች
ይህ አጭር መልእክቴ ሐዋርያዊ ተልእኮየ በሚገባ የሚመለከተው ተግባር ምን መሆኑ የሚያስገነዝብ ምልክት እንድታስተውሉ የሚያግዝ እንደሚሆን እተማመናለሁ፣ አገልግሎታችሁ ሁሌ ክቡርና ውጤታማና ገንቢ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው በመተማመን ስብሰባው ደስተኛና ውጤታማ ግኑኝነት እንዲሆን መልካም ምኞቴንም ዳግም በማደስ በእርስዎና በተጋባእያኑ ሁሉ ለቤተሰቦቻችሁና ለአገልግሎታችሁ መልኮታዊ ቡራኬ እማጸናለሁ።
ቫቲካን, እ.ኤ.አ. ጥር 17 ቀን 2014 ዓ.ም.







All the contents on this site are copyrighted ©.