2014-01-15 16:04:49

ብፁዕ ካርዲናል ታውራን፦ ስለ ሶሪያ ሰላም በአገሪቱ ያለው አመጽ አለ ምንም ቅድመ ሁነት እንዲቆም ማድረግ


RealAudioMP3 የሶሪያ ግጭት ማእከል ያደረገ ጳጳሳዊ የሥነ ምርምር ተቋም የጠራው ዝግ ጉባኤ እ.ኤ.አ. ጥር 13 ቀን 2014 ዓ.ም. በአገረ ቫቲካን መካሄዱ ሲገለጥ ከጉባኤው ፍጻሜ የተሰጠው መግለጫ እንደሚያመለክተውም፣ በሶሪያ ሰላም ለማረጋገጥ አለ ምንም ቅድመ ሁነት በክልሉ ያለው ግጭት እንዲቆም ማድረግ ወሳኝ መሆኑ ሲያመለክት፣ ስለዚሁ ጉዳይ በማስደገፍ ከተለያዩ ሃይማኖቶች ጋር የሚካሄደው ግኑኝነት ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ዣን ልዊስ ታውራን ከቫቲክን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ የተካሄደው ስብሰባ ተቀዳሚ ዓላማው በሶሪያ ሰላም እንዲረጋገጥ በሚካሄዱት ዓለም አቀፍ የውይይት መድረኮች ስለ ሶሪያ ሰላም የሚመክረው ሁለተኛው የጀነቭ ጉባኤ አስፍላጊ መሆኑና በነዚህ ዓለም አቀፍ መድረኮች የቅድስት መንበር አመለካከት ምን መሆኑ በመለየት ሰነዱ ለቅዱስ አባታችን ለማቅረብ በሳቸው ውሳኔ ሥር ለይቶ የቅድስት መንበር አመለካከት ግልጽ ለማረግ ነው። ስለዚህ የቅድስት መንበር አመለካከት ምን እንዴት መሆን እንዳለበት የሥነ ምርምር ተቋም ባካሄደው ዝግ ውይይት የተሳተፉት የዓለም አቀፍ የሥነ ግኑኝነት ጉዳይ ሊቃውንት በማሳተፍ ጥልቅ ውይይት በማካሄድ ያጠናቀረው ሰነድ በማጤን ውሳኔው የቅዱስ አባታችን ይሆናል። ስለዚህ በቅድሚያ ሰላም እንዲረጋገጥ ማለትም ወደ ሰላም ለሚመራው መንገድ እድል ለመስጠት አለ ምንም ቅድመ ሁኔታ የቶስክ አቁም ስምምነት መረጋገጥ መሠረት መሆኑ ጉባኤው እንዳሰመረበት ገልጠው፣ ለሰብአዊ እርዳታ ነጻ የመተላለፊያ መንገድ እንዲለይና እንዲፈቀድም በግጭቱ ተወናያን አካላት ሁሉ የሚከበር ውሳኔ አስፈላጊ ነው። የግጭቱ ሰለባ የሆነው የአገሪቱ ሕዝብ የሰብአዊ እርዳታ ያስፈልገዋል፣ ይኽ ደግሞ የሁሉም ግብረ ገባዊ ግዴታ መሆኑ አብራርተው፣ ሰላም ለማረጋገጥ የተለያዩ ባህሎችና ሃይማኖቶች መካከል የጋራው ውይይት ያለው አስፈላጊነትም የጉባኤው ሰነድ እንዳሰመረበት ገልጠዋል።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላቸው ተወዳጅነት ተደማጭነት ቀላል አይደለም ስለዚህ በጦርነት ምክንያት ሁሉም ወድሟል ይወድማልም በሰላም ግን የወደመ ምንም ነገር የለም አይኖርም የሚል ሰላም ያለው ጥልቅ ክብር እ.ኤ.አ. ነሓሰ 24 ቀን 1939 ዓ.,ም. ር.ሊ.ጳ. ፒዮስ አስራ አንደኛ የሰጡት አገላለጥ ዘክረው፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ይኽ እውነት እንዲኖር በተለያየ መልክ የሚያስተላልፉት ጥሪ ይመሰክረዋል በማለት አክለው ይህ አመለካከትም ለተባበሩት መንግሥታት ያለው አስፈላጊነት የላቀ ነው። ሆኖም ግን በዓለማችን የሚታየው ውጥረት ግጭት ድኽነት ወዘተ የሁሉም መንግሥታት የፖሊቲካ አካላት የተባበሩት መንግሥታት ኃላፊነት ጭምርም ነው። የተባበሩት መንግሥታት ደንብ አንቀጽ ስድስትና ሰባት ሰላም ለአደጋ ሲጋለጥ ምን መደረገ እንዳለበት ግልጥ ባለ አነጋገር ይገልጣል፣ ስለዚህ የተባበሩት መንግሥታት ደንብ ሁሉም አገሮች ተስማምተው የፈረሙበት ሰነድ ነው ስለዚህ ሰነዱን እግብር ላይ የማዋል ኃላፊነት አለባችው፣ ትውልድ ለጦርነት አደጋ ላለ ማጋልጥ ምን መደረገ አለበት ከሚለው ጥልቅ የሰላም ፍላጎት ሃሳብ የመነጨው የተባበሩት መንግሥታት ሰነድ ይኸው ከ 70 ዓመት በኃላ ውይይት የሚያስቀድም ባህል ሳይሆን የተስፋፋው በቅድሚያ ግጭትና ጦርነት ከዛ በኋላ ለውይይት መቅረብ የሚለው አመለካከት ነግሦ ማየቱ ያሳዝናል ብለው በመጨረሻ የተካሄደው ጉባኤ ውይይት ብቸኛው የሰላም መንገድ መሆኑ በተለያየ መልኩ ተጋባእያኑ ያሰመሩበት ሃሳብ ነው በማለት የሰጡን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.