2014-01-15 16:00:51

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ ወደ ሌላው እቅንቶ የሚራመድ ሰላምን የማነጽ ብቃት አለው


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. ጥር 14 ቀን 2014 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በቅድስት መንበር ለተለያዩ አገሮች ልኡካነ መንግሥታት ተቀብለው “የግኑኝነት ባህል ለይቶ ቅድሚያ ለመስጠት የሚያግዝ የጋራ ጥረት አስፈላጊ ነው። ምክንያቱም ወደ ለሌላው ከእርሱ ወደ ተለየው አቅንቶ የሚራመድ ሰላም የማነጽ ብቃት አለውና” የሚል ጥልቅ ሃሳብ ያካተተ ንግግር ማሰማታቸው ሲገለጥ፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ባሰሙት ንግግር ዙሪያ የቲዮሎጊያ ሊቅ በሎፒያኖ ሶፊያ መንበረ ጥበብ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፒየሮ ኮዳ ከቫቲካ ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ሰዎችን ለተለያየ አደጋ የሚያጋልጠው ለስቃይ የሚዳረገው በተለያዩ ምክንያት የሚሰቃዩትን ሁሉ በተለይ ደግሞ ተነጥለው ለገዛ እራሳቸው የተተዉትን በድኽነት የሚገኙት ወንድሞችና እህቶች የሚኖሩት ስቃይ ምንኛ ለልባቸው ቅርብ መሆኑ በተለያየ ወቅት ከሚያስተላልፉት መልእክት ከሚፈጽሙት ተግባር ለመረዳቱ አያዳግትም፣ ሆኖም ይኽ በጥላቻ መንፈስ በአመጽ በማኅበራዊ ችግር ሌላውን በሚያገል ባህል ምክንያት የሚሰቃየውን የማሰቡ የመደገፉ ፍላጎትና ተግባር እግዚአብሔር በታሪክ የሚፈጽመው ተግባር ነው። ቅዱስ አባታችን ይኽንን ነው የሚመሰክሩት ስለዚህ ለልኡካነ መንግሥታት ያስተላልፉት መልእክትም እንዲህ ባለ መልክ መተንተን ይቻላል ብለዋል።
ቅዱስ አባታችን ለልኡካነ መንግሥታት ባሰሙት ንግግር ላምፔዱዛ ተገኝተው ባሰሙት ንግግር ያሰመሩበት ሃሳብ እርሱም “ወድማዊ ኃላፊነት” የሚለው ቃል ደግመው በማስተጋባት ትንተና የሰጡበት ማንም ሌላውን በግደ የለሽነት ሊመለከት እንደማይገባው ብቻ ሳይሆን እንደማይችል የሚያሳስብ ነው በማለት ገልጠዉታል።
ማንም በተለይ ደግሞ መንግሥታትና በዓለም የሚከሰተው ኢሰብአዊነት የተሞላው ተግባር እንደ ማይመለከተው ሆኖው ለመኖር አይቻላቸውም፣ ስለዚህ ሕይወት ከመጸነስ እስከ ባህርያዊ ሞት ተከብሮ ታቅቦ እንዲኖር የሕይወት ባህል የማስፋፋቱና የመከላከሉ ጉዳይ የሁሉም ኃላፊነት መሆኑ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ባሰሙት ንግግር በቀጥታ ገልጠዉታል፣ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ሃሴትና ተስፋ በተሰኘው ውሳኔው ግለኝነት እኔባይነት የሚያረጋግጥ ሥነ ምግባር ያስከተለ አስተሳሰብና አኗኗር ሊቀረፍ እንደሚገባውና ይኽ ደግሞ የሰው ልጅ መብትና ክብር ጥበቃ የተጎሳቆሉትን በስቃይ የሚገኘው ለተለያየ ችግር የሚጋለጠው የኅብረተሰብ ክፍል ቅድሚያ መስጠት ያለው አስፈላጊነትና ኃላፊነት ተብራርቶ ይገኛል። የሰው ልጅ ስበአዊ መብትና ክብር ማእከል ሊሆን እንደሚገባው የሚያሳስብ ንግግር ነው በማለት ከተነተኑ በኋላ ከዚሁ ጋር በማያያዝ ሕዝባዊ እድገት በተሰኘው ዓዋዲ መልእክት ሥር ቤተ ክርስቲያን በነቢያዊ እድማስ ወንጌላዊ ሥነ ምግባር ዓለምን የመለወጥ ኃይል እንዳለውና ይኽ ደግሞ ፍትህ እንዲረጋገጥ የሚያበቃ መሆኑ መብራራቱንም ገልጠው፣ የፍትህና የፍቅር ደንብ ብቻ ነው የዓለምና የሕዝቦች ሰላም ለማረጋገጥ የሚቻለው በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.