2014-01-10 16:14:15

የአባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ ቃለ መጠይቅ ለብፁዕ ካርዲናል ቨላሲዮ ደ ፓውሊስ፦ የለጀናሪዮም ክርስቲ ጠቅላይ ጉባኤ በቤተ ክርስቲያን ሕይወት አወንታዊ እርምጃ ነው


RealAudioMP3 በቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እ.ኤ.አ. በ 2010 ዓ.ም. ውሳኔ መሠረት በፁዕ ካርዲናል ቨላሲዮ ደ ፓውሊስ በለጀናሪዮም ክሪስቲ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ልዩ ልኡክና ተጠሪ በመሆን ለኅዳሴ በመንጻት ጎዳና ማኅበሩን በመምራት ማኅበሩ በገዛ እራሱ ችሎ በገዛ እራሱ የአመራር አካላት ሥር እንዲመራ ወደ ሚያበቃው ጠቅላይ ጉባኤ በጸሎትና በጥበብ በቤተ ክርስቲያን ከቤተ ክርስቲያን ጋር በመሆን የመሩ መሆናቸው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ በማስታወስ ስለተፈጸመው ጉዞ ምን ይላሉ በማለት ላቀርቡላቸው መጠይቅ ብፁዕነታቸው ሲመልሱ፦ ጉዞው የመጀመሪያ እርምጃ ነው። ሰዎች ስለ ሆን ደርሻለሁ ብለን ልንቆም አይገባንም። የመጀመሪያው እርምጃ የማኅበሩ መሥራች ጉዳይ ነበር ከዚህ ጋር በማያያዝም ቅድስት ቤተ ክስርቲያን በሳቸው የሚመራው የአምስት ብፁዓን ጳጳሳት ጉባኤ ተመልምሎ በማኅበሩ የቅዱስ ጴጥሮት ልኡክ በመሆን ማኅበሩ ወደ ኅዳሴና መንጻት በመምራቱ ያገለገለ ነው። የብፁዓን ጳጳሳት ጉባኤ ማኅበሩ እንዲያስተነትን የሆነውን የተፈጸመው እንቅፋት ሁሉ በመለየት ታድሶና ነጽቶ መጻኢ በተስፋ እንዲመለከት ድጋፍ የሰጠ ጉባኤ ነው። እንደሚታወቀውም ቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የውሳኔው ሰነድ የመለመለው የብፁዓን ጳጳሳት ጉባኤ ለቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ልኡክ የማኅበሩ አባላት ለመኮነን ለማውገዝ ሳይሆን በውሳኔው ሰነድ፦ “ከእናንተ የማኅበሩ አባላት ውስጥ እጅግ በቁጥር ከፍ ያለው አብላጫው በቅንአት መንፈስ በቅድስና ጎዳና የሚጓዙ ናቸው” ያሉትን አስታውሰው ካብራሩ በኋላ፣ ስለዚህ ቤተ ክርስቲያን ይህ አይነት እማኔ ስለ ነበራት ማኅበሩ ለኅዳሴና ለመንጻት እንዲመራ አድርጋለች፣ የሚገባ ሁሉ ጥናትና ክትትል በማድረግ የተደረሰ የማኅበሩ ጠቅላይ ጉባኤው ነው ብለዋል።
የውሳኔው ሰነድ አንዱ የማኅበሩ ደንብ እንዲከለስና አዲስ ደንብ እንዲጸድቅ የሚጠይቅ መሆኑም ብፁዕ ካርዲናል ደ ፓውሊስ በማስታወስ፣ ይኽ ደግሞ በሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ መንፈስ ሥር እንዲመራ ማድረግ የሚል ውሳኔ ነው። ስለዚህ የማኅበሩ ደንብ ሰፊ አንዳንዴም የማኅበሩን መንፈሳዊ መርሆ የሚያደበዝዝ ተመስሎ የነበረ በመሆኑም የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ በለጀናሪዮ ክርስቲ ማኅበር ሌላ ሐዋርያዊ ክንዋኔው ይኸንን የነበረውን ደብን እንዲጤንና ተጢኖም በአዲስ መንፈስ አዲስ ደምብ እንዲረቅ ፈር ማስያዝ የሚል እንደነበርም ገልጠዋል።
በሮማ የማኅበሩ አባላት ማለት ካህናትና ተማሪዎች በጠቅላላ 4 ሺሕ አምስት መቶ እንደነበሩ ገልጠው፣ ስለዚህ በሮማ ያሉትን የማኅበሩ አባላት ጋር መገናኘት በሌላ አገር ከሚገኙ የማኅበሩ ቤቶች የሚገኙት እንዲሁም በማኅበሩ መንፈሳዊ መርሆ ሥር የተቋቋሙት የተለያዩ የዓለማውያን ምእመናን ማኅበራትና የደናግል ማኅበራት ጋር መገናኘት የሚጠይቅ ተልእኮ እንደነበርም ገልጠው፣ ከዚህ አንጻር ሲታይ ሰፊና አድካሚ ነበር፣ ነገር ግን በጌታ ድጋፍ ሁሉ ይቻላል፣ ያጋጠመው ችግር በአወንታዊ የተመለከቱት በአሉታዊ የተመለከቱት ነበሩ። አጋጣሚው በአወንታዊ የሚመለከቱ እጅግ በቁጥር ከፍ ያሉ አብላጫ መሆናቸውም ጠቅሰው ማኅበሩ በቅርብ ለማወቅ የደገፈ በጥበብ የተመራው የቤተ ክርስቲያን ውሳኔ ማኅበሩ እንዲታደስ አብቅተዋል በማለትም ገልጠዋል።
አባ ሎምባርዲ በመካሄድ ላይ ያለው ጠቅላይ ስብሰባ የማኅበሩ የአመራር አካላት የሚመርጥና አዲስ የማኅበሩ ደንብ የሚያጸድቅ ይሆናል፣ የማኅበሩ አዲስ ሕግ ረቆ ከወዲሁ የቀረበ ከሆነ የሚካሄደው ስብሰባ እንዴት ባለ መልኩ ነው ውሳኔ የሚሰጥበት በማለት ላቀረቡት ጥያቄ ብፁዕ ካርዲናል ደ ፓውሊስ ሲመልሱ፦ በመካሄድ ላይ ያለው ጠቅላይ ስብሰባ በቅድሚያ የሦስት ዓመት ከስድስት ወር ክንዋኔ የሚያጤን እርሱም የኅሊና ምርመራ የሚል መጠሪያ የተሰጠው ነው። ቀጥሎ የማኅበሩ ጠቅላይ አለቃና የመማክርት አባላት ምርጫ ነው። ሦስተኛው ደረጃ የነበረው የማኅበሩ ደንብ መከለስ የሚል ነው። ከዚህ ጋር በማያያዝ በተካሄደው የሦስት ዓመት ከስድስ ወር ጥናት ላይ የጸና የረቀቀ ደንብ ለጉባኤው በማቅረብ ውይይት ይደረገበታል፣ ጉባኤው የሚያጸድቀው የጠቅላይ ስብሰባው የፍጻሜ ሰነድ የሚጸድቀው በቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ናቸው በሚል አገላልጥ ምላሽ ሰጥተውበታል።
የማኅበሩ መሥራችና ማኅበር በማደባለቅ የተመለከተ ሂደት እንዳልሆነም ብፁዕነታቸው ገልጠው፣ ለዚህም ነው ማኅበሩ መቀጠል እንዳለበት ቤተ ክርስቲያን የምታምንበት። የማኅበሩ መንፈሳዊ መርሆ የእግዚአብሄር መንግሥት የሚል ነው። ይኸንን መንፈዊነት የሚከተሉ ዓለማውያን ምእመናን አሉ አነርሱ የጌታን መንግሥት በዕለታዊ ሕይወት ማወጅ በሚል ዓላማ ይከታተሉታል፣ የማርያማዊ መንፈስ የተካነ የመስቀል ድል አድራጊነት የሚያበስር መርህ ነው። በማኅበሩም ይሁን የማኅበሩ መንፈሳዊነት የሚከተሉ የተለያዩ ማኅበራት ይኸንን መንፈሳዊነት እንዲኖሩ የተጠሩ ናቸው። እንዲህ ባለ መልኩ የማኅበሩ መንፈሳዊ መርሆ ግንዛቤ እንዲያገኝ መደረጉንም ከገለጡ በኋላ ማኅበሩ ወደ ጠቅላይ ጉባኤ ለመጥራት የፈጀው ዓመት ቀድሞ የተወሰነ አለ መሆኑ ገልጠው የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.